>

ዶ/ር አብይ የቀን ጅቦች ስጋት ላለባቸው ሰዎች ምንም ጥበቃ ሳይደረግ ማነቂያ ገመዳቸውን መሳብ አልነበረበትም (ኣወት አስመራ ኪዳኔ)

ዶክተር አብይ የቀን ጅቦች ስጋት ላለባቸው ሰዎች ምንም ጥበቃ ሳይደረግ ማነቂያ ገመዳቸውን መሳብ አልነበረበትም 
ኣወት አስመራ ኪዳኔ
ዶክተር አብይ አህመድ እንደተሾመ ሁለት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ባለስልጣናት “እሱማ አያዘንም” ብለው ቀድመው ስልጣን ለቀቁ!
1) የ INSA ዳይሬክተር ጀኔራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ነው። ጀኔራል ተክለብርሃን ወዲያውኑ መቀሌ መሸገ። አዲስ አበባ የተገኘው ምክትሉ ቢኒያም ከፈንጁ ፍንዳታ ማግስት በ”ሙስና” ታሰረ። ጀኔራል ተክለ ብርሃን መቀሌ ሆኖ ዶክተር አብይ አህመድን በትግራይ ቲቪ ሲያብጠለጥል ይውላል። ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ትዕዛዝ ወጥቶበት “አሻፈረኝ” አለ ተብሎም ያልተጣራ ወሬ ሲወራበት ነበር።
2) የብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኃላፊ የነበረው ክንፈ ዳኘው ከኢንሳው ዳይሬክተር ጋር “አብይማ አያዘኝም” ብሎ በአንድ ቀን ስራ ለቅቀዋል። ብረታብረትና ኢንጅነሪንግ የግድቡንና የስኳር ፋብሪካዎችን ስራ ይዞ አክስሯቸዋል።
የአብይ ስህተት!
ዶክተር አብይ አህመድ ለራሱም ጥንቃቄ ባለማድረግ ሰኔ 16/2010 ዓም ትልቅ ችግር ተፈጥሮ ነበር። ሰሞኑን ከመምህራን ጋር በነበረው ምክክር ደግሞ አንድ የእነ ክንፈን ጉዳይ መዘዘ። እነ ክንፈ የተጫወቱበት ግድብ በ5 አመት ይጠናቀቃል ሲባል ሌላ የአስር አመት እድሜ ገመተለት። ያም ሆነ አይጠናቀቅም አለ። ለ5 አመት የተባለው 20 አመት ሊወስድ ነው ማለቱ ነው።
እነ ክንፈ አብይ በዚህ ደረጃ ይመጣል ብለው አያስቡም። እያድበሰበሰ ፕሮጀክቱን በደረሰ ጊዜ ይድረስ ብሎ የሚጠብቅ መስሏቸዋል። ለፖለቲካም ይጠቀምበታል ብለው ይሆናል። በቀደም ባሳየው አቋም ግን የሚተውላቸው ምንም ነገር እንደሌለ ማሰባቸው አይቀርም። ስለ ፕሮጀክቶቹ ዝርዝር መረጃ የሚጠይቀው ደግሞ ከኢንጅነር ስመኘው ነው። ሚስጥርም ቢሆን!
ለአብይ አልታዘዝም ብሎ ስልጣን ቀድሞ የለቀቀው የኢንሳው ዳይሬክተር መቀሌ ከትሞ አልመጣም ብሏል ሲባል ነበር። እሱ ባይገኝም በፍንዳታው ማግስት ምክትሉ ተያዘ። ኢንሳ ደህንነት ጉዳይ ላይ ነው የሚሰራው። ፈንጅ በፈነዳ ማግስትም ምክትል ዳይሬክተሩ ተያዘ። ክሱ ሌላ ቢሆንም ቅሉ!
ከአባይ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ሲመጣ ከተክለ ብርሃን ጋር ሆኖ “አብይም አያዘኝም” ብሎ ቀድሞ ስልጣን የለቀቀው ክንፈ ዳኘው የአብይ ቅጣት እንደማይቀርለት ያውቃል!
ዶክተር አብይ የቀን ጅቦች ስጋት ላለባቸው ሰዎች ምንም ጥበቃ ሳይደረግ ማነቂያ ገመዳቸውን መሳብ አልነበረበትም። አሁንም ሌሎች የግድቡ ሰራተኞች አሉ። የእነ ሜቴክን፣ የትህነግን ጉድ የሚያውቁ!
ግብፅም ሻዕቢያም አረቦችም የዶ/ር አብይም የለውጥ ኃይሎች በኢንጂነር ስመኝ በቀለ መወገድ የሚጠቀሙት ቅንጣት ታክል ጥቅም የለም #ምክንያቱም ኢንጂነር ስመኝ ቢወገድ የህዳሴውን ግድብ በምንም መለኪያ ሊያስተጓጉለውም ሊያስቆመውም አይችልም ኢትዮጲያን የሚያክል የ100 ሚሊዮን አሕዛባት ሃገር ቦታውን ተክቶ ስራውን ማስፈፀም የሚችሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉምቱ ሙሁራን ኢንጂነሮች መተካት ትችላለች ከአለም-አቀፍም ሕብረተሰብ በመስኩ ትልቅ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱን ባለሞያዎች ቀጥራ ፕሮጀክቱ ለታሰበለት አላማ እንዲደርስ ማስቻል ትችላለች………
#ድምዳሜ = ከግድያው ጀርባ ሊኖሩ የሚችሉት ሴረኞች እስካሁን በግድቡ ዙሪያ ለተፈፀሙ #ዝርፊያዎች #ማጭበርበሮች #ስርቆቶች #ሸፍጦች #ሴራዎች ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ወገኖች ናቸው ምክንያቱም ፕሮጀክቱ ተጀምሮ እስካሁን እስከተደረሰበት ደረጃ ያለውን ጠቅላላ ሚስጥር በጥልቀት የሚያውቀውና; የፕሮጀክቱ ማስፈፀማያ ገንዘብ በነማን እንደሚዘወር ፣ ማን ምን እንዳደረገና ፣ የተኛው ባለስልጣን ምን ውሳኔ እንዳስተላለፈ ማስረዳትና እማኝ ምስክር መሆን የሚችለው ኢንጂነር ስመኝ በቀለ ነበር………#ቀደሙት
ከህዳሴው ግድብ ጀርባ እነማን እንደነበሩ ለማወቅ ነብይ ወይ ጠንቋይ መሆን አይጠበቅብህም…..ጅቦቹ ናቸው።
Filed in: Amharic