>

ዶ/ር ደብረፂዮን እና  የህዳሴው ግድብ ሰራተኞች ጥያቄ (በምስጋናው ዘ-ጊዮን)

ዶ/ር ደብረፂዮን እና  የህዳሴው ግድብ ሰራተኞች ጥያቄ
በምስጋናው ዘ-ጊዮን
በዚህ ፅሑፍ የተካተቱት መረጃዎች በሙሉ ከ2 ሳምንት በፊት በህዳሴው ግድብ ከሚሠራ ሰራተኛ የተላከ ቢሆንም ለማጣራት ሲባል በወቅቱ አልተለጠፈም፡፡ ዛሬ ኢንጅነር ስመኘው አልፈዋል፤ እሳቸው ቢያልፉም በመረጃው ላይ መጠነኛ ማጣራት በማድረግ ለመለጠፍ ተገድጃለሁ፡፡
➡ከ3 ዓመት በፊት በህዳሴ ግድብ የሚሠሩ ሰራተኞች ደመወዝ አነሰን በማለት በፕሮጀክቱ ስፍራ አመፅ ያነሳሉ፡፡ አመፁን ለማረጋጋትና ከሰራተኞች ጋር ለመምከር ወደስፍራው ያመራው ዶ/ር ደብረፅዮን ከሰራተኞች ጋር ሳይግባባ በመሳደብና በማስፈራራት ያለመፍትሔ ተቋጨ፡፡ የዛኑ ዕለት ማታ 3:30 ላይ ፌደራል ፖሊስ ገብቶ ሰራተኛውን በመደብደብ ከግድቡ 8km ርቀት ባምዛ ከተባለ ቦታ እንዲሠፍሩ ተደርጎ ለ2 ቀን ያህል በርሃብ በመቅጣት ይዘቱ ያልታወቀ ወረቀት በግዳጅ እየፈረሙ ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
:
➡ ባለፈው ዶ/ር አብይ ወደ ግድቡ በማቅናት በፕሮጀክቱ ዙሪያ ከተነሱት ችግሮች ውስጥ የሰራተኞች ደመወዝና ከደን ምንጣሮ ጋር በተያያዘ የተዛባ መረጃ መገኘቱ ተነግሯል፡፡ ኢንጅነሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሰራተኞች ደመወዝ የሰጡት መረጃ ከትክክለኛው ደመወዝ የሚለይ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ማዘናቸውንና በአሶሳው ስብሰባ ወቅትም ኢንጅነሩ እንዳይሳተፉ መደረጉን ሰራተኞች ይገልፃሉ፡፡ ሰራተኞችም ቀደም ሲል ተገደው የፈረሙት payroll እንደሆነና በፕሮጀክቱ ሁለት አይነት payroll መኖሩን በማወቅ በስማችን ለምን ይነገዳል ያሉ ሰራተኞች በሜቴክ አፋኞች ጨለማ ቤት እንደሚሰቃዩ ይነገራል፡፡ ይህንን የሰራተኛ payroll በተመለከተ በፕሮጀክቱ የSaleni constuction ማናጀር Mr.Feraro አጋልጧል፡፡
[ ከዚህ የምንረዳው የሜቴክ ጀኔራሎች የ17,000  ሰራተኛ ደመወዝ በግማሽ ቀንሰው እየከፈሉ ሰራተኛውንም ህዝንም ራሱን ሜቴክንም ሲዘርፉ ኑረዋል ማለት ነው፡፡ የዚህ ዝርፊያ መረጃና የአፈፃፀም ሚስጥሩን የሚያውቁት ኢንጅነሩ ናቸው፡፡ በጥቅም መተሳሰርም ሊኖር ይችላል]
➡ሌላው ደግሞ የደን ምንጣሮው ለሜቴክ ያለጨረታ ተሰጥቷል፡፡ ሜቴከ ይህንን ስራ ሲወስድ መንጥሮ ለወረቀት ፋብሪካዎች ለማቅረብ በመስማማት ነው፡፡ ግድቡ ወደኋላ የሚተኛበት ቦታ እስከ አማራ ክልል የሚደርስና ከ200km በላይ ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል፡፡ ነገር ግን ሜቴክ ከንዑስ መንጣሪዎች ጋር በመመሳጠር ለወረቀት ፋብሪካ መዋል የነበረበትን እስከ 150Km የሚሸፍን የደን ጥሬ ዕቃ በእሳት በማቃጠል  ለወረቀት ፋብሪካ ለማቅረብ አንችልም በማለት ብሩን ውጠዋል፡፡
[ በዚህም መሠረት ምንም ስራ ሳይሰሩ ብዙ ቢሊየን ብሮች ዘርፈውናል የዚህንም ዝርዝር ሚስጥር የሚያውቁት ኢንጅነሩ ናቸው:: በእኔ እይታ በግድቡ የተሳተፉ አካላት እጃቸው በሙስና የተጨመላለቀ ነው፤ ኢንጅነሩ የተገደሉትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ መመላለስ ስላበዙ የዝርፊያ ሚስጥር እንዳይወጣና ከጥቅም ግጭት ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል ]
Filed in: Amharic