>

የመቐለው ሰልፍና የደብረጺሆን ድንፋታ የቀን ጅቦች ጩኸት (ምንሊክ ሳልሳዊ) 

የመቐለው ሰልፍና የደብረጺሆን ድንፋታ የቀን ጅቦች ጩኸት
ምንሊክ ሳልሳዊ
ተከባብሮ መኖር ካልተቻለ መበታተን ግድ ነው”
ዶ/ር ደብረጽዮን
 
ዛሬ መቐለ ላይ በተደረገው ሰልፍ ላይ ደብረጺሆን የሚባል ጉቶ አፍ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስፈራራልኛል ብሎ ያሰበውን ድንፋታ ሲናገር ነበር። ሃያ ሰባት አመት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨዋነት አክብሮ ዝም ብሏል። አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ትእግስቱ አልቋል። መገደል እና መዘረፍ ፤ መሰደድና መታሰር ሰልችቶታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያገኘው የነጻነት ተስፋ እንዳይቀለበስ ከሕወሃት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ ለድል እንደሚበቃ ደብረጺሆን ሊያውቀው ይገባል።ተከባብሮ መኖርን የመሰለ ታላቅ ነገር የለም ። ገዳይ ተከብሮ ዘራፊ ተከብሮ ተገዳይና ተዘራፊ ተንቆ ዝም ብሎ ማለፍና መኖር እንዴት ይቻላል ይህ መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው።
መበታተን የሕወሓት ከመነሻዋ ጀምሮ ያለ አላማዋ ስለሆነ ምንም አይደንቅም። አዲስም ነገር የለውም። መጀመሪያ ስለመከባበር ሊያወራ የሚችለው ሰው መከባበርን የሚያውቅና ሕዝብን የሚያከብር እንጂ በሴሰኝነት ሃገር ሲዘርፍና ሲገድል የነበረ ሰው ስለመከባበር መናገር አይችልም። ስለመበታተን ደግሞ ለተባለው ሃያ ሰባት አመት በዘረጋቹት መዋቅራቹ የሕዝብን ሰላም ለጊዜው ልታደፈርሱ ትችላላቹህ እንጂ አገርን መበታተን አትችሉም። የሕወሓት ጅቦች በትግራይ ተደብቀው መግቢያ ቀዳዳ ስታጡ ዛቻና ማስፈራራት ብታደርጉም ማንም የማይፈራ መሆኑን አስረግጠን ለመናገር እንወዳለን። ሕወሓት አንድነትና ፍቅር አይዋጥለትም። ዲሞክራሲና ነጻነት ያመዋል። ይህ የታወቀ ሐቅ ነው።
ሕገ መንግስት ይከበር የሚለው መፈክር የጻፈው ሕወሓት ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የትኛውን ሕግ አክብሮ ያውቃል ፤ ሕገመንግስቱ እኮ ጥፍር ንቀሉ ፣ ብልት አኮላሹ ፣ ግደሉ ፣ ዝረፉ ወዘተ አይልም። መጀመሪያ ሕገመንግስቱን የራሳቸው የፓርቲ መርሃ ግብር ግልባጭ ስለሆነ ራሳቸው ሕወሓቶች ማክበር ይገባቸዋል።
የኢትዮ ኤርትራን ስምምነት እንደግፋለን መባሉ ጥሩ ሲሆና ከወር በፊት ግን የሰላም ስምምነቱን በማውገዝ ከኢሮብ እስከ መቐለ ሰልፍ መካሔዱን ማስታወስ ይበጃል። የ አልጀርሱ ስምምነት ኢሕአዴግ ለምን ተቀበለ ብሎ ሕዝብ ሰልፍ ተራ ተባለ ሕወሓት ይህንን ስምምነት ለመቀበል በጋራ በኢሕአዴግ ውስጥ ሆኖ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። የማምታታት ፖለቲካ ሕዝብንም ወደ ነፈሰበት እያላጋው ነው።
ዘራፊዎችና ገዳዮች በጊዜያዊነት በትግራይ ቢመሽጉም ዋና መገኛቸው እስር ቤት መሆኑን መርሳት የለባቸውም፤ ይህን ሁሉ ግፍ ሰርቶ የትም ማምለጥ አይቻልም ለጊዜው ሊመስላቸው ይችላል። መቀሌ የመሸግከው የገዳይና የዘራፊዎች ቡድን ማንም አይፈራህም። ካለፈ ታሪክ ለመማር ባይዘጋጁም የድሮ ግፈኛ ባለስልጣናት ታሪኮች በሕወሓት ባለስልጣናት ላይ ይደገማሉ።
Filed in: Amharic