>

አሁን ላይ ጠ/ሚ አቢይ ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ ነው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

አሁን ላይ ጠ/ሚ አቢይ ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
በ1889 አፄ ዮሀንስ መተማ ላይ አርፈው የመንግስታዊ ስልጣኑን አፄ ምኒልክ ሲረከቡ ስልጣናችንን ተነጥቀናል ያሉት የትግራይ መኳንንት ለመአከላዊው መንግስት አንገዛም በማለት መቀሌ ውስጥ መሽገው ነበር።
አፄ ምኒልክ ይሄን ጉዳይ ለመቋጨት ብዙ ድፕሎማሲያዊ ጥረት ካደረጉ በኋላ ምእራፉን የዘጉት በልኡል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል የሚመራ ጦር ወደ ትግራይ በመላክና በማንበርከክ ነበር ። ዛሬ በአስደናቂ ሁኔታ  ከ 170 አመታት በኋላ  በተመሳሳይ የታሪክ ምእራፍ ላይ እንገኛለን።
የዛሬው የመቀሌው ሰልፍ ለአቢይ አህመድ መንግስት እውቅና የነፈገ ፣ በመንግስት ላይ ጦርነት የታወጀበትና ፣ትግራይ ክልል ለአቢይ አህመድ የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ የሰጠበት ነው።
አሁን ላይ ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ ነው።
1~ እንደ አፄ ምኒልክ  ማንበርከክ ወይም
2~ መንበርከክ ።
ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ ሶስተኛ አማራጭ በፍፁም የለውም።
ትዝብተ-መቀሌ
አምደ ማርያም
  የመቀሌውን ሰልፍ እየተከታተልኩ ነበር።ይህን ሰልፍ በመነጠርም፣ያለመነጠርም፣አተኩሬ ብመነጥር፣የዶ/ር አቢይ ፎቶ የለም።የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም እንዲሁ።አለመኖሩን ካረጋገጥኩ በኋላ፣ወዲያውኑ የሰልፉ ዋንኛ አላማ ወደ አይምሮዬ ከች አለ።
የሰልፉ ዋንኛ አላማ የኢትዮ-ኤርትራን የሰላም ስምምነት ስለመደገፍ መሆኑን ነግረውናል።በሰልፉ ላይም ብዙ ጊዜ ደጋግመውልናል።እናም ዛሬ ተሰለፍነለት ያሉት ስምምተት እንዲሰምር ደግሞ የሁለቱ አገራት መሪዎች ብርቱ ጥረት ባይኖር ኖሮ አይታሰብም ነበር።በተለይ የዶ/ር አቢይ ቆራጥ ውሳኔ።ቢሆንም ግን መቀሌ መዳፉን አሻክሮ፣እንቅልፍ አጥቶ ተግቶ የሰራላትን አመድ አፋሽ አድርጋለች።
 ይሁን እንጂ የመቀሌው ሰልፍ የኤርትራን እና የኢትዮጵያን ህዝብ መጋዝ ሆኖ በቆረጠው፣ በጭራቁ መለስ ዜናዊ እና ታላቋን ትግራይ ለመመስረት፣ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዓላማ አንግበው ሲዋጉ የሞቱትን ” ሰማዕታት” በሚሏቸው ፎቶዎች አጨልሟል።በተጨማሪም ዛሬም ልክ እንደጦርነቱ ወቅት ድንፋታ የበዛበት ሰልፍ ሆኗል።
“መቼም ጊዜም ቢሆን አንሸነፍም!!”  ይላል የመቀሌው ሰልፍ መፈክር!!
እኛም አልን “ከወደቁ በኋላ አጉል መፈራገጥ!! ትርፉ ጀርባ መምለጥ!! ነው።” የሚሆነው።
Filed in: Amharic