>

 ያ ሁሉ የኤፍ ቢ አይ ጋጋታ ለዚሁ ነበር??? (ይድነቃቸው ከበደ)

ያ ሁሉ የኤፍ ቢ አይ ጋጋታ ለዚሁ ነበር???
ዛሬም ያልለቀቅን አባዜ ግንዱን መቁረጥ ሲቻል ቅርንጫፉን መጨፍጨፍ!!!
ሰኔ 16 ቦንብ ጥቃት
በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰረት መሆኑን ኢቲቪ ነግሮናል።
በሰኔ 16ቱ ህዝባዊ መድረክ ላይ የቦንብ ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው በሚል በተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በስም ተጥቅሰዋል።
ተጠርጣሪዎቹ አብዲሳ ቀነኒ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ ፣ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው።
እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ከሆነ አንደኛ ተጠርጣሪ አብዲሳ ቀነዒ በዕለቱ በወንጀሉ ተጠርጥረው የህክምና ዕርዳታ እየተሰጣቸው የነበሩትን ሰዎች ለማስመለጥ ሙከራ ያረገ ሲሆን ሶስተኛው ተጠርጣሪ ጌቱ ግርማ ደግሞ የቦንብ ጥቃቱን በማስተባበር ወንጀል ነው የተጠረጠረው።
ተጠርጣሪው ከዚህ በፊት በወንጀል ተጠርጥሮ ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በምህረት የተለቀቀ መሆኑን የፖሊስ ማስረጃ ያስረዳል።
አራተኛዋ ተጠርጣሪ ህይወት ገዳ በዕለቱ የአእምሮ ህመምተኛ በመምሰል በወንጀሉ የሳተፈች ስትሆን አሁንም በአማኑኤል ሆስፒታል ህክምናዋን እየተከታተለች መሆኗን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።
የምርመራ ቡድኑ የምርመራ ስራውን አጠናቆ መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ አስረክቧል።
ዓቃቢ ህግም በህጉ መሰረት ክሱን አደራጅቶ ለመመስረት ችሎቱን የ15 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።
ተጠርጣሪዎች ጨለማ ቤት ውሰጥ ተቆልፎብናል፣ ህገመንግስታዊ መብታችንም ተጥሷል በሚል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።
መርማሪ ቡድኑ ግን የአያያዝ ችግር እንደሌለ እና ይህንንም በቪዲዮ አስደግፎ ለፍርድቤቱ ማቅረብ እንደሚችል ገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ከፈለገም ገለልተኛ አጣሪ ቡድን በመመደብ ሊያጣራ እንደሚችልም አስታውቋል።
ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ከአያያዝ ጋር በደል እንዳይደርስባቸው፣ ክትትል እንዲደረግላቸውና በቀጣዩ የቀጠሮ ቀን ነሐሴ 12፣ 2010 በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተጠርጣሪዎች ማረፊያ የስራ ኃላፊ ቀርበው ስለአያያዛቸው ማብራሪያ እንዲሰጡም አዟል።
Filed in: Amharic