OMN
ኦ.ኤም.ኤን ቴሌቪዥን በሰበር ዜናው እንዳስደመጠው በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኡመዩ ቡልቄ ወረዳ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል በትናንትናው እለት ባካሄደው ወረራ ቢያንስ ከ32 በላይ ሰዎች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ መፈጸሙ ታውቋል።
ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለጹልን የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል (ፖሊስ) በገበያ ቀን በሕዝብ ላይ በፈጸመው ወረራ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች ሳይቀሩ አሰቃቂ ግድያ እና የአካል መጉደል ደርሶባቸዋል።
ነዋሪዎቹ የሟቾቹን አስከሬን ለማንሳት ተቸግረው እንደነበረም ገልጸዋል።
የየሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወረራ መክፈቱንም ምንጮች ገልጸዋል።