>

የአይን ምስክር :- የኦሮሚያ ፖሊስ ቆሞ ያሰቀለውን ወጣት አስክሬን በአይሱዙ ከመጎተት አድኖታል!!! (አለምነህ አበረ)

የአይን ምስክር እንዲህ ብሏል :- 
* የኦሮሚያ ፖሊስ ቆሞ ያሰቀለውን ወጣት አስክሬን በአይሱዙ ከመጎተት አድኖታል!!!
አለምነህ አበረ
* እግር በመጋዝ የሚቆርጥ ብልት የሚያኮላሽ ሰው ዘቅዝቆ ለቀናት የሚያከርም እስር ቤት ዘግቶ በእሳት የሚያነድ መንግስትን ተገላገልን ስንል በየሰፈሩ በዘረኝነት አብደው ብልት የሚቆርጡ  ሰው በእሳት የሚያነዱ ቆዳ የሚገፉ ዘቅዝቀው ሰቅለው የሚገሉ ጉዶች እየተበራከቱ ነው። 
“ዛሬ ተዘቅዝቆ የሞተውን ልጅ ቦታው ተገኝቼ ተመልክቸዋለው እንባ እየተናነቀኝ ነው ወደቤቴ የገባሁት እስካሁንም ከአእምሮዬ አልጠፋም፡፡ ፖሊስም ሆነ ኦሮሚያ ፖሊስ ቆሞ የተሰቀለውን አስክሬን ቆሞ ይመለከት ነበር ከዛም ውሳኔ ሳይሰጡበት ካካባቢው ሄዱ በኃላ አስከሬኑን ከሰቀሉበት አውርደው በካባቢው ከቆመች አይሱዙ ጋር ከኋላ አስረውት ሊያስጎትቱት ሲሉ ሹፌሩን አልጎትትም ጎትት ግብ ግብ ተፈጠረ በዚህ መሀል ካካባቢው ሄዶ ነበር ያልኩህ የፀጥታ ሀይል መጥቶ ተኩስ ከፍቶ ከበተናቸው በኋላ እሬሳውን ጭነው ወሰዱት ልብ በሉ ወዲያውኑ የልጁን ማንነት ስናጣራ ልብስ እያዞረ የሚሸጥ ከርታታ የደቡብ ልጅ መሆኑን አውቀናል፡፡ልጁ ግር ግር ሲፈጠር አራሱን ለማዳን ሲሮጥ ነው ቦንብ የያዘ ነው ብለው የያዙት ፡፡”
Filed in: Amharic