>

ሕወሃት ሲመቸው የሚረማመድበት ሲጨንቀው ቆሜለታለሁ የሚለው ሕገ-መንግሥት !!! (ሰውነት ባንትይርጋ)

ሕወሃት ሲመቸው የሚረማመድበት ሲጨንቀው ቆሜለታለሁ የሚለው ሕገ-መንግሥት !!!
ሰውነት ባንትይርጋ
*ሕገመንግሥቱ ሕዝብ የራሱን መሪ መምረጥና እራሱን በራሱ ማስተዳደር መብት ይሰጣል።የሱማሌ ክልል መቼ ነው የራሱን መሪ የመረጠው? አብዲ ኢሌን ማን መሪ አድርጎ ሾመው? የሱማሌ ሕዝብ መርጦታል??የሱማሌ ሕዝብ እኮ አብዲ ኢሌ በቃን ሲል ገዳይ ስኳድ ድጋፍ ሰጭ  የሚላክለት ከሕወሃት ነበር
ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ስለ መቐሌ ሰላማዊ ሰልፍ መግለጫ አሰሙን።እሳቸው መግለጫ ሳይሰጡን ሰላማዊ ሰልፉ እራሱ መግለጫ አወጣ።ሰላማዊ ሰልፍ ያወጣው መግለጫ የሚለውና የዶ/ር ተብየው ዶ/ር ደብረጽዮን የነገሩን መግለጫ የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃሉ።ሰላማዊ ሰልፉ የሰጠው መግለጭ የሚለው እኛ ትግሬዎች ፤ከሆኑ ማለቴ ነው፤ እኛን የማያከብረንን ሁሉ እንዋጋዋለን።ካልሆነ ደግሞ እንበታተናለን ነው።በሰልፉ ላይ አዛውንት እናቶች ያነገቧቸው ምስሎች ሁሉ የሞቱ፤ ታግለው ያለፉ ሲሆኑ በተጨማሪ በበሽታ ከኢትዯጵያ ምድር ለመልካም የተሰናበቱትን የመለስ ዜናዊ ከሁሉም ምስሎች በገዘፈ መልክ ተሸክመው ነው።እያሉን ያሉት ሰልፈኞች እኛ የምናውቀው እነዚህን ነው።የምንከትለው እነዚህን ነው ።በተለይ የምንከተለው ታላቁን መሪያችንን እንጂ ሌላ አንቀበልም የሚል ነው።ለዚህም መረጃ የሚሆነው የኢህአዴግ ጠቅላይ ሚኒቴር፤ አሁን ደግሞ ሕዝብ እልቡ ያስገባቸው፤የዶ/ር አቢይ አህመድን ምስል በምንም መልኩ ማየት አንፈልግም ያለ ሰልፍ ነው።ይህ ሰልፍ የካድሬና የሕወሃት የእንጀራል ልጆች ሰልፍ እንደሆነ በዚህ ልንረዳ እንችላለን።ሕገ መንግሥት አፍራሽ ሰልፍ ማለት ይህ ነው።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤በዓለም ዙሪያ ሕወሃት ያሰደደው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እልቡ ያስገባውን ዶ/ር አቢይ አህመድን አልቀበልም ያለችው መቐለና የትግሬ አመራር በሰልፉ በመሪያቸው በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል አፍ ሕገመንግሥቱን እናስጠብቃለን እያሉን ነው።የትኛው ሕገመንግሥት?የኢትዮጵያ ሕዝብ የማያውቀውን፤ሕዝብን በባርነት አንድ ለአምስት ጠርንፎ ሃያ ሰባት ዓመት ያሰቃየውን የኢህአዴግ ሕወሃት ሕገመንግሥት ከሆነ ከፈረሰ ሃያሰባት ዓመት ሆኖታል።በሰላማዊ ሰልፉ ግን ሕገመንግሥቱ ይከበር እያለ ነው በሰልፉ የታደመው የመቐለ ሕዝብ።ሕገመንግሥቱ እኮ አሳብን መግለጽ፤ሕዝብ የራሱን መሪ መምረጥና እራሱን በራሱ ማስተዳደር መብት ይሰጣል።የሱማሌ ክልል መቼ ነው የራሱን መሪ የመረጠው?የሕወሃት ጀኔራሎች የመሣሪያና የኮንትሮባንድ ሥራቸውን እንዲያካሂዱ መብት የሚሰጥና  ትዕዛዛቸውን የሚያስፈጽም አብዲ ኢሌን ማን መሪ አድርጎ ሾመው?የሱማሌ ሕዝብ መርጦታል እንዳትሉኝ።የሱማሌ ሕዝብ እኮ አብዲ ኢሌ በቃን ሲል ድጋፍ የሚላክለት ከሕወሃት ነበር።የአማራና የኦሮሞ፤የጋምቤላና የቤንሻንጉል፤የአፋር አመራሮች ማን ነበር የሚጎልታቸው?ማን ነበር ካልተስማሙት በተለያየ መንገድ የሚያስወግዳቸው?ሕወሃት እራሱ ምስክር ነው።በአሁኑ የለውጥ ጊዜ አብዲ ኢሌን በመደገፍ መግለጫ የሰጠው ማን ነው?
እነዚህ ሁሉ መረጃዎች እፊቱ ተጎልተውለት ዶ/ር ተብየው ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሕገመንግሥቱን እናስጠብቃለን እያለን ነው።ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሆይ ያፈረስከውን ሕገመንግሥት አስጠብቃለሁ ስትል አታፍርም?ሕገመንግሥት እኮ የሕዝብን ጥቅም የሚያስጠብቅ እንጂ የሕዝብን መብት ጨፍልቆ አንድን ቋንቋ ተናጋሪና ዘር የሚጠቅም አይደለም።ሕገመንግሥት አለ ብንል እንኳ ሕዝብ አልበጀኝምና እለውጠዋለሁ፤አሻሽለዋለሁ ካለ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ምን ባይ ነው እኔ ብቻ ነኝ የሕገመንግሥቱ አባት እናት ኃላፊና ጠባቂ የሚለን?ሕገመንግሥት አለ ካለ የመቐለው አመራር ሕገመንግሥቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።ምነው መቐለ የመሸገው አመራር የሕገመንግሥት ተቆርቋሪ ሆኖ በየስልፉ የሚያቅራራብን?የሞተ ሕገመንግሥት አይገዛንም ብሎ የባህር ዳር፤የአርባ ምንጭ ሕዝብ ተናገረ። ዶ/ር ደብረጽዮንና አባታቸው መለስ ዜናዊ የለጠፈውን ኮከብ ሕዝቡ አስወግዶ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ሲያወጣ ምነው የመቐለ ሰልፍ አጋፋሪና አቀንቃኝ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሕገመንግሥት ተጣሰ እያለ ያለቅስብናል?የአዞ እንባ።
ይልቅስ ወደ ቁምነገሩ እንመለስ ።ኢህአዴግ በማዕከላዊ ዲሞክራሲ መርሆ መሠረት የተመረጠውን ጠ/ሚ አልቀበልም ያለ የመቐለ አመራር ሕገመንግሥቱን ስላፈረሰ ወንጀለኛ መሆን ብቻ ሳይሆን የራሱን ሕገመንግሥት ስላፈረሰ ሊፈረድበት የሚገባ ነው።አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተቀበለውና በሕገመንግሥቱ የተደገፈውን ጠ/ሚ አልቀበል የሚል የመቐሊ አመራርና የሰልፉ ተካፋዮች አለመቀበላቸው በሕገመንግሥቱ መሠረት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።ሕግመንግሥቱን ሽፋን አድርጎ ማቅራራት የሕገመንግሥቱ ደጋፊ አያደርግም።ሕገመንግሥቱ የሚለውን በተግባር ማሳየት ግን ደጋፊነትን ያሳያል።ማነኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በየትኛውም ሥፍራ ሄዶ መኖር፤መሥራት፤ንብረት ማፍራት መብቱ ነው ይላል ሕገመንግሥቱ።ለሃያ ሰባት ዓመት የአማራን ዘር እየጎተተና እያስጎተተ፤ትዕዛዝ እየሰጥ ሲያፈናቅል፤ሲገድል ፤ሲያስር የነበረ የሕወሃት አመራር አሁን ትግሬ ተባረረ እያለ ይጮኸል።ሕወሃት ሲያሳድድ፤ ሌላውን ዘር በፓርላማም፤ በተለይ የአማራን ሕዝብ፤ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ጠፋ እያለ በራሱ ሰው በመለስ ዜናዊ ሲያናግር ምነው ሕገመንግሥቱ አልተነሳም?ለሕዝብ ብየ አመጣሁት የሚለው ለጋሹ የሕወሃት መንግሥት ምነው በሃያ ሰባት ዓመት ሕገመንግሥቱ ተጣሰ ሲልና ሲያለቅስ አልሰማነውም?ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ማሃይም መረዳት የሚችለውን ሀቅ መመልከት የማይችል የትግሬ ዶ/ር ነው፤ ከሆነ ማለቴ ነው።ሃያ ሰባት ዓመት የጨለማ ዘመን ነበር ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ የመቐለው አመራር ግን የብርሃን ዘመን ነበር አለ።ጨለማ መሆኑን የሚያውቀው በጨለማ ዘመናት ያስቆጠረ ነው።በጨለማ ሲገድልና ሲዘርፍ የነበር ተጠቅሟልና ብርሃን ነው ሊል ይችላል።እውነቱን መወቅ ከፈለግህ የመቐለ አመራር ወረድ ብለህ የሕዝቡን የጨለማ ኑሮ ጠይቅ።ብርሃን የበራላቸው ሕወሃትና ተባባሪዎች ብቻ ነበሩ።እወቁ ያመጣችሁት ጨለማ ተወግዷል።ሕዝብ በብርሃን አሳቡን ያለፍርሃት እየገለጸ ነው።የእሥር ቤት ደጆች ተከፍተዋል።በብርሃን የሚመራ ለሕዝብ ተወልዶለታል።የጠላት ሠራዊት ተበትኗል፤ሞቷል።
Filed in: Amharic