>

ጠ/ሚ ዶ/ር  አብይ በኢሕአዴግ  ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ  ሕወሓትን ክፉኛ አስጠነቀቁ!!! (ሰለሞን አንጋሼ)

ጠ/ሚ ዶ/ር  አብይ በኢሕአዴግ  ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ  ሕወሓትን ክፉኛ አስጠነቀቁ!!!
ሰለሞን አንጋሼ
ዛሬ በተጀመረው 36 አባላትን ብቻ በያዘው የኢሕአዴግ  ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ  ላይ ሕወሓትን ከዚህ በኋላ በአገራችን ላይ እየተሠራ ያለው አገርን የማተራመስ ድራማ ሊቀጥል አይገባውም ሲሉ  አስጠነቅቀዋል።
እየተሠራ ያለው አገርን የማተራመስ ድራማ በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ ሕዝብንና አገርን ለማዳን ሲባል መንግስት የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ  የሚገደድ መሆኑን በማለት ጠንካራ ቃላቶችን በመጠቀም  ተናግረዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር  አብይ በኢትዮ-ሱማሌ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በድሬዳዋ  እንዲሁም ከአገር አልፎ በጎረቤት  አገር በጅቡቲ  በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየተደረገ ባለው ማፈናቀልና ጭፍጨፋ እነማን እንዳሉበት መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል፣ አስፈላጊም ከሆነ  በስም ጠርቶ  መናገር  ይቻላል። ሲሉ ቁጣ በተሞላበት ቃል  የሕወሓትን ገመና አንድ በአንድ በስራ አስፈፃሚው ፊት ሲዘረግፉት አንድም  የሕወሓት  ባለስልጣናት ማስተባበያ ለመስጠት የደፈረ አልነበረም።
ጠ/ሚ ዶ/ር  አብይ “… መንግስት እስካሁን  የታገሰው ለሚፈሰው ደምና መፈናቀል ባለማሰብ ሳይሆን ይህን አስነዋሪ ስራ ተደራጅተው የሚሰሩ ሠዎች ከድርጊታቸው ተፀፅተው ይመለሳሉ በሚል ትዕግስት እንጅ ማንም ስለተፈራ አይደለም። እንደዚህ አስበው ከሆነ ተሳስተዋል፣ አሁንም ከድርጊታቸው ለመመለስ አልመሸባቸውም፤ ግን መንግስት ዜጎችን  ለመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ ስላለበት ሕግንና ስርዓትን የማስከበሩን ስራ ይሠራል” ብለዋል።
በዛሬዋ ቀን የኢህአዴግ ም/ ሊቀመንበሩና ም/ጠ/ሚነስትሩ አቶ ደመቀ መኮንንም  ንግግር ተዋጦለት እንደዋለም እየተነገረለት ነው።
አቶ ደመቀም ሲናገሩ “… አሁን እየታየ ያለውን  ለውጥ ሕዝብ  እንጂ ኢሕአዴግ አላመጣውም በመሆኑም  ለውጡ ይቀለበሳል ብሎ የሚያስብ ካለ ያ ሰው  ወቅቱን መረዳት የማይችል የአእምሮ በሽተኛ መሆን አለበት…” ሲሉ በሕወሓቶች ሰፈር አስደንጋጭ የሆነ ሚሳኤል ጥለውባቸዋል።
አቶ ደመቀ በዚህ አላቆሙም “…ለውጡ ከዚህ በኋላ ትክክለኛውን መንገድ ስለያዘ አንዳችም ኃይል ሊያሰቆመውና ሊያደናቅፈው አይችልም ይልቁን ከዚሁ ለውጥና ከሕዝቡ ጋር መቆም ያዋጣናል…” ሲሉ ሕወሓትን ሸንቁጠዋየዋል።
በዚህ ስብሰባ  የብአዴኑ አቶ ገዱም ቢሆን ወልቃይትን፣ ራያን፣ ኮረምና ሌሎች አወዛጋቢ ቦታዎችን በተመለከተ የተዋጣለት ታሪካዊ ንግግር   አድርገዋል።
Filed in: Amharic