>

ፊት አልባው የወያኔው የደህንነት ሹም ወዴት ገባ?!? (እስራኤል ሰቦቃ)

ፊት አልባው የወያኔው የደህንነት ሹም  ወዴት ገባ?!?
እስራኤል ሰቦቃ
በከፈተኛ ወንጀል ሊፈለጉ የሚችሉ ግለሰቦች እንዲህ በቀላሉ የትም ሄደው መኖር እንደማይችሉ ስለሚያዉቁ የመደበቂያ ጉድጓዳቸዉን የሚቆፍሩት እዚሁ ሀገር ዉስጥ እንደሚሆን ይገመታል!
የ95 አመቱ የቀድሞው የናዚ የእስር ቤት ዋርዲያ ለበርካታ አመታት ከተደበቀባት አሜሪካ ተይዞ ወደ ጀርመን መወርወሩን CNN ላይ እያዳመጥኩ በስልኬ ላይ ደግሞ ለብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን መገደል፤ ታስሮ መጥፋት፤ ቶርች መደረግና የኣካል መጉደል ተጠያቂ የሆነው የፋሺስቱ የወያኔ የድህንነት መስሪያ ቤት ሹም ጌታቸዉ አሰፋ ከመቀሌ ከተማ በመዉጣት ወደ ዉጪ ሃገር የመኮብለሉን እና የእስርም ማዘዣ እንደወጣበት የሚያትት ዜና ሰማን አነበብን ።
አሮጌው የናዚ ወታደር ዛሬ ከምድረ አሜሪካ ዲፖርት ይደረግ እንጂ ብዙዎቹ የናዚ ወንጀለኞች የሃሰት ዜግነት ገዝተው ተደብቀው ከኖሩበት የላቲን አሜሪካ ሀገሮች በተለይም (ከአርጀንቲና፤ ኮሎምቢያ፤ ፔሩ ቦሊቪያ፤ ቺሊና የመሳሰሉት) እየታደኑ ለፈጸሙት ጥፋት ቅጣታቸውን ተቀብለዋል።
ይዋል ይደር እንጂ ጌታቸዉ አሰፋና ሌሎቹን የወያኔ ፋሽስት ወንጀለኞችን ያስመለጡ፤ የሸሸጉና የወንጀለኛ ታባባሪዎች በህግ ፍት ከመጠየቅ አያመልጡም። ወንጀላቸዉን የከፋ የሚያደርግባቸው ግን ዛሬ ሀገሪቷ የጀመረቺዉን የሰላም ጉዞ ለማደናቀፍ በህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ወንጀል ነው።
ይህ ግለሰብ ቀደም ሲል ቤተሰቦቹን ከሃገር ማሸሹ ከመነገሩ ውጪ ይህ የቀድሞ የወያኔ ባለስልጣን በትክክል ከሀገር ይዉጣ አይውጣ የታወቀ ነገር የለም።
እንደ በርካታ ታዛቢዎች ኣስተያየት እንደዚ ህ ያሉ በከፈተኛ ወንጀል ሊፈለጉ የሚችሉ ግለሰቦች እንዲህ በቀላሉ የትም ሄደው መኖር እንደማይችሉ ስለሚያዉቁ የመደበቂያ ጉድጓዳቸዉን የሚቆፍሩት እዚሁ ሀገር ዉስጥ እንደሚሆን ይገምታሉ። .https://www.nytimes.com/2018/08/21/world/europe/nazi-guard-deported.html
Filed in: Amharic