>

ኮማንደር አለማየሁ ሐይሉ ማን ነው? (አግባው ሰጠኝ)

ኮማንደር አለማየሁ ሐይሉ ማን ነው ?
አግባው ሰጠኝ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽኑ አረመኔ ጥፍር ነቃይ የስመኘውን ጉዳይ አጣሪ ሆኖ ቀረበ
 የአመቱ ታላቅ ፌዝ
 
  በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት የትግራይ ተወላጅ በሆኑት የማረሚያ ቤት ሀላፊዎች በርካታ ወንድሞቻችን በግፍ ተገለው አስከሬናቸው በሳት እንዲቃጠል የተደረገው በጥይት የተመቱት እንዳይታወቅ ሲሆን የነዚህን አረመኔ የማረሚያ ቤት ሀላፊዎች ወንጀል ለመሸፈን እኛን በዘራችን በፖለቲካ አቋማችን እና በአመለካከታችን መርጠው በሽዋሮቢት ማረሚያ ቤት ቶርች ያስገለበጠን  ሰው ነው። የተለያዩ ዘግናኝ ግርፋቶች እና ማሰቃየት የፈፀሙብንን አረመኔ ቡድኖች መሪ የነበረ  ነው። በቂሊንጦ ቃጠሎ መጠየቅ የነበረባቸው ወንጀለኞች ተቀምጠው እኛን በግፍ ያስከሰሰ አረመኔ በሰዉ ደም የሚቀልድ ፖሊስ ነው።
ዛሬ ደግሞ የኢንጅነር ስመኘውን ያማሙዋት ጉዳይ ካጣሩት አንዱ እሡ ነው አሉ። ይሄ ቀልድ ነው። ጎበዝ ምን እየተደረገ ነው? ፍትህ ዛሬም አፈር ድሜ እንደበላች ነው።
ይሄ ሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽኑ ጥፍር ነቃይ ነው። ብዙ ወጣቶች ስለዚህ ሰው አውርተውኝ ነበር።  በአጣና ጥፍር ከሚያወልቁት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አባላት መከከል አንዱ መሆኑን በሀና ማርያም  ጉዳይ ተከስሰው የታሰሩት መካከል የወለቀ ጥፍራቸውን እያሳዩ ስለዚህ ፖሊስ አጫውተውኛል። አሁን የስመኘውን ሊያጣራ መጣ።
Filed in: Amharic