>
5:13 pm - Sunday April 18, 2765

ክቡር ጠ/ሚ አብይ ዲያስፖራውን በሚልንየም አዳራሽ ሰራዊቱን በቡሬ ግንባር አወያይተዋል!!! ፍጹም አረጋ

ክቡር ጠ/ሚ አብይ ዲያስፖራውን በሚልንየም አዳራሽ ሰራዊቱን በቡሬ ግንባር አወያይተዋል!!!
የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ቃል አቀባይ ፍጹም አረጋ
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአዲስ ዓመት ንግግራቸውን የጀመሩት ለብዙ ዓመታት ከእናት አገራቸው ተለይተው ለቆዩና በቅርቡ ወደ ውዷ አገራቸው ለመጡት:- ለፖለቲከኞች: ለአክቲቪስቶች እና ለሌሎች የዳያስፖራ ማህበረሰቦች በሙሉ ሲሆን: ለእነርሱ ሲባል በሚሊንየም አዳራሽ በተዘጋጀው የአዲስ ዓመት አቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ ስለተገኙ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል::
ቀጥለውም በንግግራቸው ላይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አዲስ አመትን በጋራ ሆነው በሁለቱ ድንበሮች መካከል እንደሚያከብሩ ገልጸዋል:: የአዲሱ ዓመት የጋራ ግባችን እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ህዝባችን ለጋራ ብልጽግና ተግቶ እንዲሰራ በማስቻል የተረጋጋና ለልማት የተሰለፈ የአፍሪካ ቀንድን ዕውን ማድረግ ይሆናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቡሬ ግንባር
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን እርቅ ተከትሎ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር መካከል ተገኝተው የቡሬ ግንባር ይባል በነበረው ቦታ በጋራ ሆነው ከሁለቱ አገራት የሀገር መከላከያ ሰራዊቶች ጋር የአዲስ አመትን እያሳፉ ይገኛሉ::
መልካም አዲስ ዓመት! 
Filed in: Amharic