>
9:29 pm - Sunday January 23, 2022

የጸረ ለውጡ ሀይል የመንግስት ስልጣን በሀይል ለመንጠቅ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው!!! (ህብር ራዲዮ)

የጸረ ለውጡ ሀይል የመንግስት ስልጣን በሀይል ለመንጠቅ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው!!!
ህብር ራዲዮ
* አ.አበባ ካላት ግዛት 34 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በኦሮምያ ልዩ ዞን እንዲካተት ጠይቋል!
ከነዶክተር አብይና ለማ መገርሳ ስልጣን ለመንጠቅ ከሕወሐት ጋር ግንባር የፈጠሩት አንዳንድ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች እንዳሉ ተገለፀ።
መንግስት አስቀድሞ መረጃው ቢደርሰውም እርምጃ አለመውሰዱ ለሰሞኑ ግጭት አስተዋፅኦ እንዳለው ተመልክቷል።
ፌዴራል መንግስቱን የሚመራው የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አስተዳደርም ሆነ የኦሮሚያ ክልልን የሚያስተዳድረው የኦሆዴድ ምክትል ሊቀ መንበር፥ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳና ቡድናቸው በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በምንፈልገው መንገድ እየወሰደን አይደለም በሚል ይፋና ስውር ቅስቀሳ ሲያደርጉ የቆዩ አንዳንድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባለስልጣናት፥ በሐገር ውስጥ የቆዩ አንዳንድ ፓለቲከኞች እና አክትቪስቶች ላለፉት ጥቂት ወራት የቻሉትን ሁሉ ዘመቻ ውስጥ ውስጡን ከማድረግ አልፎ የፌዴራሉን ስርዓት አደጋ ላይ ወድቋል ብሎ ለውጡን “ለመቀልበስ” ሲንቀሳቀስ ከነበረው የሕወሐት አመራር ጋር ግንባር መፍጠራቸውንና ይኽው መረጃ ደግሞ ለመንግስት መድረሱን የሕብር ሬድዮ ዘግቧል።
በተለይ በአዲስ አበባ ያለን ጥቅም አልተከበረም፥ የአዲስ አበባ መሬት ከሆነው ከ50 000 ሄክታር 37 000ሄክታሩ ወደ ኦሮሚያ ኦሆዴድ በአስቸኳይ ያካትት። ይህን ማስፈፀም ካልቻለና ልዩ ዞን ካላደረገ በተደራጀ መንገድ ከምርጫ በፊት ወይም ቀድሞ ስልጣኑን ለእኛ ማስረከብ አለበት፥ የፌዴራል መንግስት ማንኛውንም ነገር ከሕወሐት ጋር በድርድር ሊወስን ይገባል፥ ይህንንም እኛ ስልጣኑን ተቀብለን ተግባራዊ እናደርጋለን የሚል አቋም ይዘው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን፤ ይኽው ዘመቻ በመንግስት ፀጥታ ተቋም ውስጥ በተለይ በኦሮሚያ ፖሊስ ጭምር እንዲደርስ በልዩ ልዩ መንገድ ሲያካሄዱ መቆየታቸው ታውቋል።
የጠቅላይ ሚኒስተር አብይን አስተዳደርን ሆነ የኦሮሚያ ክልል ለማ መገርሳ አስተዳደር ላይ ከባድ ጫና ለመፍጠር ያለመ እንቅስቃሴ ታቅዶ የነበረ ሲሆን የኦነግ ወታደሮችን ስብሐት ነጋን ጭምር እንዲቀበል ማድረግ ፥ የአዲስ አበባን አቀባበል መሰረት አድርጎ ግጭት የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ከማድረግ ባለፈ አስቀድመው ለፀጥታ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ስልክ እንኳን ቢደወል ወደ ችግሩ ቦታ እንዳይሄዱ በማድረግ ከዛም አልፎ ችግር የፈጠሩ እና አደጋ ያደረሱ ወጣቶች እንዳይይጠየቁ እቅድ መውጣቱንና ይህንን የጠቆሙት ምንጮች በአዲስ አበባ የተፈፀሙት ግጭቶች ከመፈፀማቸው በፊት መረጃው የመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ጋር መድረሱንና የፀጥታ ሐይሉም ጉዳዩን በቸልታ ማለፉን እነዚሁ ምንጮች አመልክተዋል።
የሕወሐት መሪዎች ከፍተኛ ገንዘብ በአንዳንድ የኦነግ አመራሮች በኩል አስቀድሞ በአገር ቤት ካሉ ፓርቲዎች እንዲደርስ ያደረጉ ሲሆን የኦነግ ወታደሮችን ሕወሐት መጋበዝ እና  አቀባበሉን ተከትሎ የተነሱ ግጭቶች፣ ከጀርባ በማስተባበር እና በግርግር “” ስ.ል.ጣ.ን…እ.ስ.ከ.መ.ን.ጠ.ቅ እቅድ የወጣ እጅ እንዳለበት የህብር ራድዮ ምንጮች አመላክተዋል።
በአዲስ አበባ በኦነግ መሪዎች አቀባበል ስነስርዓት ላይ ከሕወሐት ገንዘብ ተቀብለው  የተለያዩ ተልዕኮ ለማስፈፀም ተመልለምው ከተላኩት ውስጥ አንዳንዱ በመያዛቸው እቅዱ ሲከሽፍ ሚስጥር እንዳይወጣ በተያዙት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡ መኖራቸውንና መንግስትም ችግሩን አውቆት ነገር ግን ነገሩን በሰከነ መንገድ ለግዜው ታግሶ ማለፉን እና የፀጥታ ክፍሉም በዚህ አይነት መንገድ መረጃው አስቀድሞ እጃቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ቡድን የአዲስ አበባን ከተማ ካላት ሕጋዊ ይዞታ 50 000 ሄክታር ላይ ቀንሶ 16 000 ሄክታር ብቻ እንዲሆንና ሌላውን በልዩ ዞን ኦሮሚያ ስር እንዲካለልና ከተማዋን በሚመለከት የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አስተዳደር ይህን ጥያቂያችንን ሊመልስ አልቻለም በሚል ከባድ ፈተና ውስጥ በመክተትና ጫና በመፍጠር ስልጣን ለመያዝ ትግል ላይ ስላሉ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በውስጥም በውጭም ያላችሁ፤  አንዲት ኢትዮጵያን ስለሰበከ ብቻ ብቻውን ከባድ ፈተና ላይ ላለው ከ ዶክተር አብይ ጎን እንድቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ሕብር ራድዮ!
አንድ ሕዝብ አንድ ኢትዮጵያ
Filed in: Amharic