>
9:23 am - Saturday December 10, 2022

የቀድሞዉ  OPDO የአሁኑ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) ዉሳኔዎችና አንደምታቸዉ!! ቹቹ አለባቸው

የቀድሞዉ  OPDO የአሁኑ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ(ODP  ) ዉሳኔዎችና አንደምታቸዉ!!
ቹቹ አለባቸው
የቀድሞዉ OPDO  የአሁኑ ODP ገና ከወዲሁ ጠቃሚ እርምጃወችን ወስዷል። ከነዚህም መካከል:
1.የድርጅቱ ስያሜ እጅግ ታስቦበት የወጣ ስያሜ ነዉ ። ካሁን በሁዋላ የዚህ ድርጅት አባል ለመሆን ወሳኙ መስፈርት ኦሮሞነት ነዉ። ክልል አይገድበዉም።
2. ሁለተኛዉ የ ODP ወሳኝ ዉሳኔ ; ነባር አመራሮቹን በክብር ማሰናበቱ ነዉ። ይሄኛዉ እርምጃ ሌላም መልእክት አለዉ; ይሄዉም የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ዋነኛ ጠበቆች ገለል በመደረጋቸዉ; ዶ/ር አብይ እና ጓዶቻቸዉ ይሄን ርእዮት ለመቀየር ቢፈልጉ ነገሩ ቀለላቸዉ ማለት ነዉ።
እኔ አሁን ነገሮችን ዝም ብየ ሳያቸዉ; ODP እና ANDM; ደኢህዴንን እንደማባበል አድርገዉ; አድብተዉ TPLFን ጉድ ሳይሰሯት አይቀርም።  TPLF ባለችበት ቁማ ታላዝናለች; አሁንም አብዮታዊ ዲሞክራሲ ትላለች። ስሜንም አልቀይርም ብላለች; አይ ሞኟ በቁሟ ስትሞት አልገባትም።
አሁን አየመጣልኝ ያለ ነገር; የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፖርቲና ብአዴን አድፍጠዉ ወደ ኢህአዴግ ጉባኤ በመግባት; የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ነገር እንተወዉ የሚል አጀንዳ አንስተዉ; የፈለግክ ከኛ ጋር ቀጥል ያልተመቸህ ተወዉ ሊሉ ይችላሉ። የሁለቱ ድርጅቶች መናበብ የጉድ ነዉ; ደኢህዴንም ሲያሸኝ ጢስ ወጋኝ ነዉ። ህወሀት ግን አሳዘነችኝ; ብቻዋን መቅረቷ ነዉ። ለሁሉም ህወሀት በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤ ባልጠበቀችዉ መንገድ በሰለበቻ ሳትዘረር አትቀርም።
ብአዴን ከ ODP ምን ይማራል?
 የODP ጉባኤ ቀድሞ መካሄዱ ለብአዴን ጥሩ ነገር ሳይሆን አይቀርም። በተለይም ሁሉንም  ነባር አመራሮች እንዲሁም በህዝብ ቅሬታ የሚነሳባቸዉን አንዳንድ አመራሮች በክብር ለማሰናበት መንገዱ ተቀዶለታል። ስለሆነም ብአዴን ይሄን መንገድ ማስፋት አለበት። ይሄ ሁኔታ እዛዉ እንዳለ ; በብአዴን ዉስጥ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጠበቃወችን ቁጥር ስለሚቀንሰዉ ; ብአዴን ዉስጥ ያለዉ የለዉጥ ሀይል  አብዮታዊ ዴሞክራሲን ለመጣል/ ለማሻሻል እድሉን ያሰፋሐታል ማለት ነዉ። ስሐሆነም ብአዴን ይችን እድል ተጠቀምባት።
——
ነገር ግን ; ምንም እንኳን ODP የወሰዳየዉ ዉሳኔወች ለብአዴንም እንደ ጥሩ አጋጣሚ የሚወሰዱ ቢሆንም;  አልፎ አልፎ የምሰማቸዉ ነገሮች ግን ይሄነን የብአዴንን ጥሩ አጋጣሚ እንዳያበላሹበት እፈራለሁ። ይሄዉም አሁን ለጉባኤ ተሳታፊነት የሚመረጡት አባላት ላይ ሁሉም የለዉጥ ሀይሉ ደጋፊ የመሆናቸዉ ጉዳይ አልፎ አልፎ ነገሩ አልጣመኝም።
 የጉባኤ አባላት ብአዴንን በማዳንና በመግደል በኩል የመጨረሻዉን ዉሳኔ የሚሰጡ ናቸዉ። የተከበራችሁ መላዉ  የብአዴን አባላት! የጉባኤ ተወካዮቻችሁን መርጣችሁ ጨርሳችሁዋል? ጨርሳችሁ ከሆነ; ምን አይነት አባላትን ወከላችሁ? የለዉጥ ሀይሉን የሚደግፉ ስለመሆናቸዉ አረጋግጣችሁዋል? ይሄን ሳታረጋግጡ ወኪሎቻችሁን መርጣችሁ ከሆነ ብአዴንን ጎዳችሁት; ጥሩ ወኪሎቻችሁን መርጣችሁ ከሆነ ደግሞ ብአዴንን አዳናችሁት ማለት ነዉ።
አሁን በተወሰነ መልኩ ባለኝ መረጃ መሰረት; የጉባኤ ተሳታፊ ምርጫ እየተጠናቀቀ መሰለኝ። ስለሆነም አሁን ቀሪዉ ሀላፊነት የተመረጡት አካላት መሆኑ ነዉ። እናንተ ለጉባኤ ተሳታፊነት የተመረጣችሁ ወድ የብአዴን አባላት አንዴ ምክሬን ስሙኝማ: አሁን ብአዴንን የማዳንና የአማራን ህዝብ ስሜት አዳምጦ ምላሽ የመስጠት ትልቁ አደራ አለባችሁ። የድርጅቱን ፕሮግራምና ህገ ደንብ በደንብ መፈተሽ እንዳለ ሁኖ; በተለይም  ድርጅቱን ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት የሚ የሚመመሩ አካላትን በመምረጥ በኩል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ።
ዛሬ ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነዉ። ስለሆነም በዚህ ጉባኤ ማን ምን አለ; ማን ማንን መረጠ; ወዘተ የሚሉ ነገሮች ወደ ህዝባችሁ ጀሮ መድረሱ አይቀርም። ስለሆነም እናንተ የምትወዷቸዉ ;ነገር ግን የአማራ ህዝብ ቅሬታ የሚያነሳባቸዉን ግለሰቦች ቢኖሩ እንኳን እነዚህን ግለሰቦች ከመምረጥና ከመጠቆም እንድትቆጠቡ ወንድማዊ ጥሪየን አቀርብላችሁዋለሁ። ይህ ዉሳኔያችሁ የሚጠቅመዉ ብአዴንንና የአማራን ህዝብ ብቻ ሳይሆን እናንተንም ጭምር ነዉ። ዛሬ እንደምታዩት በየወረዳዉ ህዝቡ አልፈልጋቸዉም ስላለ ብቻ ; ምርት ከግርድ ሳይለይ 40 አመራር በጀምላ በህዝብ ዉሳኔ ከስልጣን ሲነሳ እየተመለከትን ነዉ።
ስለሆነም;  ምንም እንኳን እናንተ የምትወዷቸዉና እንዲመረጡ የምትፈልጓቸዉ  አመራሮች እንደሚኖሩ ብናዉቅም; ነገር ግን ደግሞ ህዝቡ ካልተቀበላቸዉ ዉጤቱ ዜሮ ስለሚሆን እንድታስቡበት ብየ ነዉ። እነዚህ ሰወችስ ተመርጠዉ ከማን ጋር ሊሰበሰቡ ነዉ? ማንንስ ሊመሩ ነዉ? ችግር ነዉ። እናንተ የጉባኤ አባላትም ህዝብ የማይፈልገዉን ሰዉ መርጣችሁ ራሳችሁን ከህዝብ አትነጥሉ; የህዝብን ስሜት ማዳመጥ ይበልጣል።
በመጨረሻም; እንደለመድነዉ; ህዝበኝነት;የድርጅት መርህ; የድርጅት ዲስፕሊን ወዘተ እያላችሁ ; ህዝብ የማይፈለገዉን ሰዉ መርጣችሁ; ራሳችሁን ከህዝባችሁ እንዳትነጥሉ። እኔ እንደ አንድ ወንድም; ያለንበትን ወቅትና ለወደፊቱ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን ተንብየ ቢሆን ይሻላል ያልኩትን ምክር ለግሻችሁዋለሁ; የመጨረሻዉ ዉሳኔ የናንተ ነዉ።
መልካም ጉባኤ!!!
Filed in: Amharic