>

12,ኛው የብኣዴን ጉባኤ በ2 ጎራዎች መከፈሉ ተነገረ!!!  (ዘ ሚካኤል ጆርጅ)

12,ኛው የብኣዴን ጉባኤ በ2 ጎራዎች መከፈሉ ተነገረ!!!
 ዘ ሚካኤል ጆርጅ
* የክፍፍሉ መንስኤች 2 ኣበይት ምክንያቶች ናቸው።
1) ነባር የብአዴንአመራሮች ማለትም አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ጨምሮ እንደነ አቶ ህላዌ ዮሴፍ፣ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን፣ አቶ ከበደ ጫኔ፣ አቶ ጌታቸው አምባየና አቶ አለምነው መኮነን በጉባኤው ውስጥ አማራን አትወክሉም ከአሁን በፊትም የአማራን ጥቅም አሳልፋችሁ ለሌሎች ቡድን ሰጥታችኋል፣ አማራው በየቦታው ሲገድልና ሲፈናቀል የት ነበራችሁ፣ ስለዚህ ከዚህ በኃላ አማራውን ለአማራው ተውት በራሱ ሰዎች ይመራ ሲል በጥይቱ በአቶ ምግባሩ ልክ ልካቸው ሲነገራቸው፤ የበረከት ቁጥር 1 የጡት ልጅ የተባለው የሊቦ ከምከሙ አቶ ፈንታ ደጀን የአቶሙን ምግባሩን ሐሳብ በመቃወም ዛሬ ለመጣው ለውጥ ያበቁንና ብአዴንን ለዛሬው ቀን ያደረሱት ሕይወታቸውን በመገበር እነዚሁ ነባር የብአዴን አመራሮች ናቸው በማለት ንግግሩን ሲጀምር ጉባኤተኛው አዳራሹን በከፍተኛ ጩኸት ሲያነቃንቁት አቶ ፈንታ ደጀን ንግግሩን ሊያቋርጥ ተገዷል።
በመሆኑም በአቶ ፈንታ ደጀን አማካኝነት እንደተሾመ የሚወራው የደቡብ ጎንደር ዋና አስተዳዳሪ አካሄድ በማለት ንግግሩን እንዲጨርስ ቢጠይቅም ጉባኤው ተጨማሪ ጩኸት በማሰማቱ እድሉ ለአቶ አለምነው መኮንን በመስጠት አቶ አለምነው ለመጣው ለውጥ ነባሩ አመራር እንቅፋት ከሆነ ሁሉም ነባር የብአዴን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሆነ ማእከላዊ ኮሚቴው ሊለቅና በሙሉ ለአዲሱ አመራር ቦታውን ሊለቅ ይገባል የሚል ሐሳብ ሲሰነዝር ፤ የእነ አቶ ገዱና ቡድን ሳይሆን እንደማይቀር የተነገረለትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የ” peace & security” ት/ክፍል መምህሩ ዬሐንስ ቦያሌው በጭፍን እኔ የምለቅ ከሆነ ሁሉም አመራር ይልቀቅ ማለት ተገቢ አይደለም፤ ለመጣው አገራዊ ለውጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ ነባር አመራሮች አሉ እነዚህን ሰዎች ማስቀጠል ሲገባ ሙሉ በሙሉ ይልቀቁ የሚለውን ሐሳብ እስከመጨረሻው እቃወመዋለሁ ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ አዳራሹ በረዥም የድጋፍ ጩኸትና ጭብጨባ ቀለጠ።
ሌላው በጉባኤው ውስጥ ለውስጥ እየተነሳ ያለው ነጥብ አቶ ደመቀ መኮነን የድርጅቱን ኃላፊነት መልቀቅ እንደሚፈልግ የተናገረ ሲሆን አቶ ደመቀን ማን ይተካ የሚል ነጥብ ሲሆን ግማሹ አመራር በተለይ አቶ ደመቀና አቶ ገዱ የያዙት ቡድን ዶ/ር ኣምባቸውን የሚደግፍ ሲሆን ቀሪው ጥቂት የሚባሉት ደግሞ ለምሳሌ ከሊቦ ከምከም ወረዳ፣ ከፎገራ፣ ከእብናት፣ ፋርጣና ደ/ታቦር ከተማ፣ ከላሊበላ ቡግና ከቋሪት ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደርና ከመሳሰሉት የመጡ አመራሮች የነአቶ በረከትን የሚደግፍ መሆኑ ተረጋግጧል።
በነዚህ ሁለት ጉዳዮች በተፈጠረው ልዩነት ውጥረት የነገሰ ሲሆን በቲም ለማ ድጋፍ ያለው ዶ/ር አምባቸው የመመረጥ እድሉ ከፍተኛ ነው የሚሉ ግምቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። ልዩነቱ የሚካረር ከሆነ ግን ህወሓት መግቢያ በር እንዳያገኝ ለአጭር ጊዜም ቢሆን አቶ ደመቀ መኮነን በማሳመን ባሉበት ሊቆዩ እንደሚችሉ ለስብሰባው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ያስረዳሉ።
የዛሬው የውሎ ስብሰባ ቢጠናቀቅም 12ኛው ድርጅታዊ የብአዴን ጉባኤ በነቲም ገዱ አሸናፊነት አንደሚጠናቀቅ የጉባኤው ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።
Filed in: Amharic