>

የአዋሳው ጉባኤ! ተስፋን እየተመጉቡ በመከራ ውስጥ መኖር!! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

የአዋሳው ጉባኤ!
ተስፋን እየተመጉቡ በመከራ ውስጥ መኖር!!
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
የአዋሳ የጉባኤ አባላት በአብዝዛኛው በግልና በጋራ  በወፍራም ጥላቻ ልባቸው የደነደነና ሁኔታው ቢመቻቸው ለመጠፋፋት የሚፈላለጉ ሰወች ናቸው።ግብራቸውን ለመገንዘብና እውነቱን ለማመን ከፈለግን እንመራዋለን በሚሉት ህዝብ ላይ ቀን በቀን የሚደርሰውን መከራ እያየን እየሰማን ነው። በሶማሌ ፣ በቡራዩ ፣ በጋንቤላ በቤንሻንጉል በወልቃይትና በአዲስ አበባ በቅርቡ የደረሰውን ግፍ  በቂ ማሳያ ነው።
ነገርግን እንደ ማህበረሰብ ከተጣባን ተስፋን እየተመገቡ በመከራ ውስጥ የመኖር በሽታ በቀላሉ መውጣት ስለማንችል መሬት ላይ ካለው የዜጎች መከራ ይልቅ የመድረክ ተውኔቱን እየተመገብን ማንቀላፋታችን ይቀጥላል።ከእንቅልፋችን ላለመንቃት ከኔ ቢጤ ተራ ዜግች ጀምሮ አዋቂ ነን በሚሉ ሰወች ጭምር የሚዘመር መዝሙር አለ “አሁን  በሃገራችን እየተከሰተ ያለው ችግር በማንኛውም በለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ሃገር የሚጠበቅ ነው።” ስለሆነም ትእግስት ያስፈልጋል የሚል ማጭበርበሪያ ነው።
በጣም የሚገርመው ደግሞ በዚህ አይነቱ እንቅልፍ እራስን የማዘናጋቱ በሽታ እንደ ትልቅ የአውቀት ጥግ በመመፃደቅ የሚገለፅ መሆኑ ነው።በሃገራችን እየሆነ ያለውን ነገር አይቶ እውነቱን ለመገንዘብ ለሚፈልግ ኢህአዴግ ከጊዜ በተቃራኒ አቅጣጫ ስለሚሄድ ጊዜ በሄደ ቁጥር ችግሮች እየተወሳሰቡና እየተባባሱ ለመፍታት የነበረን እድል እየመነመነ መምጣቱን ነው።
በአዋሳው ጉባኤ የቀረችን አንድ የተስፋ ጭላንጭል ዶ/ር አብይን ከኢህአዴግ ለይቶ የማየት ቅዠት ሊያበቃ የሚችልበት እድል አለ።በዚያም ተባለ በዚህ እራሱን ለማታለል ለተዘጋጀ ስበብ ስለማይጠፋ በቅርብ የምንነቃ አይመስለኝም።
Filed in: Amharic