>

ወይ ወያኔ! አምታትታ ሾለከች ማለት ነው??? (አምሳሉ ገ/ኪዳን)

ወይ ወያኔ! አምታትታ ሾለከች ማለት ነው???
አምሳሉ ገ/ኪዳን
ድሮም ቢሆን ዐቢይ በኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠ ስላልነበረና ይሄ ጠቅላላ ጉባኤ የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጠ/ሚ አድርጎ የመረጠውን የዐቢይን ጠቅላይ ሚንስትርነት ማጽደቅ ስላለበት ነው እንጅ ኢሕአዴግ ዐቢይንና ደመቀን የመለወጥ አቅድ፣ ዓለማም ሆነ አስገዳጅ ሁኔታ አልነበረውምኮ ወገኖቸ ለምንድን ነው የወያኔ አጀንዳ መቀለጃ የምትሆኑት???
አገዛዙ የነ ዐቢይን ጉዳይ እንዲህ ያጮኸበትና ዋና ጉዳይ አድርጎ እንዲታይ ያደረገበት ምክንያት ጉባኤው መፍትሔ እንዲሰጥባቸው፣ ውሳኔ እንዲያሳልፍባቸው የሚጠበቅባቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዲዘነጉና የሕዝቡ ትኩረት ሙሉ ለሙሉ እዚህ ላይ እንዲሆን በማድረግ ከአንገብጋቢ ውሳኔ ከሚፈልጉ ጉዳዮች ማምለጥ ሽል ማለት ነበረ የተፈለገው እሱንም በሚገባ አሳክተዋል፡፡ አቅጣጫ አስቀምጧል አቅጣጫ አስቀምጧል በማለት ብቻ አላግጦ አንድ ውሳኔ ሳያሳልፍ ተጠናቋል፡፡
እንጅ ኢሕአዴግ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት ከነ ዐቢይ የተሻለ ሰው ኖሮት እነሱን ለመተካት ጨርሶ አላሰበም አላቀረበምም፡፡ እንደሰማቹህትም አቶ ገዱ ደብረጽዮንን ጠቆመ፣ አቶ ሚሊዮን የተባለ የደኢሕዴን ሰው ዐቢይን ጠቆመ፣ አቶ ለማ አቶ ደመቀን ጠቆመ ምርጫው በሦስቱ መሀከል ተከናወነ ተባለና ዐቢይ ድምፅ ከሰጡ 177 ሰዎች 176 ድምፅ በማግኘት አንዷ የጎደለችው የራሱ ድምፅ ናት በመሆኑም በሙሉ ድምፅ ተመረጠ ተባለ፣ አቶ ደመቀ 149 ድምፅ አገኘ ተባለና ለምክትልነት ተመረጠ ተባለ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን 15 ድምፅ ነው አገኘ ተባለና ወደቀ፡፡ የመሸወጃ ድራማውም በዚሁ ተጠናቀቀ፡፡
አዳሜ ለካ የምርም እነ ዐቢይ ይሻራሉ ብሎ አስቦ ተጨንቆ ኖሮ ተመረጡ ሲባል ጮቤ ይረግጥ ያዘ! አየ የኛ ነገር በቃ እንዲህ ሆነን ቀረን??? ኧረ ተው ንቁ??? እስከመቸ ወያኔ ይጫወትባቹህ???

Filed in: Amharic