>

ይሄ መቸም በአለም አቀፍ ድንቃ ድንቅ መመዝገብ ያለበት ተአምር ነዉ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ይሄ መቸም በአለም አቀፍ ድንቃ ድንቅ መመዝገብ ያለበት ተአምር ነዉ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ምሁሩ ስፒከር ነገር የለውም፣ መሀይሙ ግን ባለ አምፕሊፋየር ነው፤፤ ይሄ ክፉ እርግማን ነው፡
፡ኦነግ  ከንግግር ከውይይት ይልቅ ጦር መነቅነቅ ቀንቶታል  (Not the word but the sword እንደሚሉት ነው ፈረንጆቹ!!!
ታላቁ የምድራችን ሳይንቲስት የነበረዉ አልበርት አነስታይን በአንድ ወቅት ‹‹ ሳይንቲስት ከመሆን ሰአት ሰሪ ብሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ ንደት አይደርስብኝም ነበር ›› በማለት እንደተናገረ ይጠቀሳል ፤፤ በሌላ በኩል ታላቁ ፈላስፋ ሾፐን ሃወር “The one who is gifted with genius suffers most” (ሰው ባወቀና በነቃ ጊዜ መከራው ይበዛል፡፡) በማለት ጽፏል ፤፤ሁለቱም ታላላቅ ሰዎች የአለማወቅንና የመሀይምነትን ጸጋና በረከት በምሬት ተናግረዋል፤፤ ሌሎቹም የአለማችን ታላላቅ ሰዎች ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል ነገር ግን ለዛሬ ጽሁፌ መግቢያ ይሆን ዘንድ የሌሎቹን አባባል ማባከን ሳያስፈልግ  የሁለቱ ታላላቅ ሰዎች ጥቅስ በቂ  ነዉ፤፤
..
ሰሞኑን  እዚህ ፌስቡክ ላይ ከኦነግ አክቲቪስቶች  የሚሰነዘረዉ የመሀይምነት አስተያየት እኔንም እንደ አልበርት አንስታይንና ሾፐን ሀወር ‹‹ምነዉ እነዲዚህ ከምበሳጭ እንደነሱ አላዋቂ በሆንኩና ሰላሜን ባስከበርኩ›› የሚል ስሜት ሽዉ ሲልብኝ ከረመ፤፤  ፤ እነዚህ አላዋቂነት ጭንቅላታቸዉ ላይ ፎቅ የሰራችባቸዉ ሰዎች ‹‹ የኦነግ ሰራዊት ትጥቅ መፍታት አለበት ›. በማለት አለም አቀፍ መንግስታት የሚከተሉትንና በየትኛዉም አገር የሚሰራበትን ህግ እየጠቀስንነ ስንጽፍ እነሱ ደሞ  ‹‹የአማራ አርሶአደርም ትጥቁን ይፍታ›› በማለት እጅግ ከባህር ጠለል በታች የወረደና የማይገናኝ  አመክንዮ ይሰጣሉ፤፤
..
 አንድን የታጠቀ ግለሰብ፤ አርሶ አደርንና አርብቶ አደር የሆነን ሰዉ  አገር ለመመስረት ከሚታገል የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ለማነጻጸር ሲንደፋደፉ ስመለከት ‹‹ እዉነት እስካሁን ከዚህ አይነቱ መንጋ ጋር ነዉ እኩል ተደምሬ አክቲቪስት የተባልኩት ›. የሚል ሀሳብ መጣብኝና ከእነዚህ ጋር እኩል አድርጎ ስም የሰጠኝን ማህበራዊ ሚድያ ጠላሁት ፤፤
በመሰረቱ የአማራ አርሶ አደር ነፍጥ መታጠቅ የጀመረዉ ከ500 መቶ አመታት በፊት ጀምሮ ነዉ፤፤ነፍጥ ለአፋር አርብቶ አደር ባህሉ ነዉ፤፤የቦረና ኦሮሞም ነፍጥ ከታጠቀ አመታትን አስቆጥሯል ፤ የትግራይ ገበሬም ባለክላሽ ነዉ፤፤ እነዚህ ሁሉ ግን  መሳሪያቸዉን የሚጠቀሙበት ራሳቸዉን ለመከላከል እንጅ  አገር አፍርሶ ሌላ አገር ለመመስረት የፖለቲካ አላማ አንግበዉ አይደለም ፤፤
..
ኦነግ 50 አመታትን ያስቆጠረና በጠመንጃ ሀይል መንግስትን ገልብጦ ኦሮሚያ የሚባል አገር ለመመስረት አላማ አድርጎ ይንቀሳቀስ የነበረ ድርጅት ነዉ ፤፤ ይሄ ፓርቲ ሁለት አማራጭ ነዉ ያለዉ ፤፤አንደኛ/ በሰላማዊ ትግል በምርጫ ካርድ እታገላለሁ ብሎ ካመነ ጠመንጃዉን ለመንግስት ገቢ አድርጎ ሰራዊቱን በትኖ በሰላም መታገል ነዉ ፤፤
 ሌላዉ አማራጭ ሰላማዊ ዉድድሩን ትቶ  ጫካ ገብቶ ከመንግስት ወታደር ጋር እየተዋጋ ከአሸነፈ  አላማዉን በጦርነት ድል አድርጎ ማሳካት ነዉ ፤፤ ኦነግ ከሁለት አንዱን መምረጥ ግደታዉ ነዉ፤፤ ይሔ በየትኛዉም አገር የሚሰራበት ነዉ፤፤
በየትም መንግስት ባለበት አገር  ሰራዊት ማደራጀት የሚችለዉ መንግስትና መንግስት ብቻ ነዉ፤፤ አሁን በተጨባጭ እየተመለከትን ያለነዉ ግን አዲስ አበባ Five star Hotel መንግስት እየከፈለለት ቁጭ ብሎ  የአራት ኪሎዉን ህጋዊ መንግሰት በትጥቅ ትግል ለመገንደስ ሰራዊቱን የሚመራ የጦር መሪ ነዉ ፤፤ ይሄ መቸም በአለም አቀፍ ድንቃ ድንቅ መመዝገብ ያለበት ተአምር ነዉ፤፤
አሁን በተጨባጭ እንደምንታዘበዉ በሀገራችን ቦታውን የሳተ ብዙ ነገር አለ፡፡ ዲሞክራሲ ቦታውን ስቷል፡፡ ዲሞክራቱ አፉን ዘግቶ ተቀምጦ  እንደ ኦነግ ያለዉ ከጣራ በላይ ይጮሃል፡፡ ህዝቡ ፀጥ ብሎ እነጃዋርና ዳዉድ  ኢብሳ ‹‹ያለኛ  ማን አለ? ›. ይላሉ፡፡ ዛሬ ስርአቱ እየተቀየረ ፣ ዘመኑ ጤና እያጣ መጥቷል፡፡ ምሁሩ ስፒከር ነገር የለውም፣ መሀይሙ ግን ባለ አምፕሊፋየር ነው፤፤ ይሄ ክፉ እርግማን ነው፡
፡ኦነግ  ከንግግር ከውይይት ይልቅ ጦር መነቅነቅ ቀንቶታል  (Not the word but the sword እንደሚሉት ነው ፈረንጆቹ፡፡እነዚህ  ቡድኖች ጠላታቸው የገዛ ሃሳባቸው መሆኑን ሳይረዱ ሌላ ቦታ እየመሰላቸው ለጦርነት ሲዘጋጁ ጦርነቱ ሳይጀመር እያበቃባቸዉ ቢሆንም አገርን ግን ጤና እየነሷት ነዉ፤፤
በመጨራሻ አገሬ ሆይ ኦነግ  ወደ መሬትሽ ከገባ ጀምሮ በጥኑ ታመሻልና እግዜር ይማርሽ እላለሁ፤፤
Filed in: Amharic