>
5:13 pm - Friday April 18, 3704

የሐበሻ ምንነት. . .  (አቻየለህ ታምሩ)

የሐበሻ ምንነት. . . 
አቻየለህ ታምሩ
ኢትዮጵያን  በተለይም የሰሜኑን ክፍለ ሕዝብ ፈረንጆች በሚጠሩት ስም «አቢሲኒያ» ብለው ካልጠራን ሞተን እንገኛለን የሚሉንና ይህንንም ካላደረጉ ፖለቲካ የሰሩ የማይመስላቸው  ኦነጋውያን «ኦሮሞ ሐበሻ አይደለም!» ሲሉ በውጭ ኃይል  ቅኝ ተገዝቶ ነበር ማለታቸው ይሆን? ነው ወደ ቅኝ ግዛት እንመልሰው እያሉን ይሆን?
—-
አዲሱ የOBN  ኃላፊ መሐመድ አዴሞ በወንበሩ  ላይ ፊጥ እንዳለ ለመጀመሪያ ጊዜ በትዊተር ገጹ  ለደጋፊዎቹ የጻፈው ዘረኛ ጽሑፍ  Fear not, Habesha twitter የሚል ነበር።  ኦነግ ኦሮሞን ከሌላው በተለይ ከአማራው ለመለየት ሲል  ከተጠቀማቸው  ትርክቶች አንዱ  ኢትዮጵያን  ፈረንጆቹ  በሚጠሩበት ስያሜ  «አቢሲኒያ» እያለ የሚጠራበት ፕሮፓጋንዳው ነው። በቤተ ኦነግ ኦሮሞ  ከአማራ መለየት ስላለበት ኦሮሞ አቢሲኒያዊ አይደለም።  ኦሮሞ ኦሮሞ እንጂ ሐበሻ አይደለም የሚለው ትርክት የሚወለደው ከዚህ ነው። ኦነጋውያን ራሱን አቢሲኒያዊ ብሎ የሚጠራ  አማራም ሆነ ሌላ ኢትዮጵያዊ እንደሌላ ያውቃሉ። ሆኖም ግን  ፈረንጆቹ  ለመለያየት  እንደሚጠቅም ስላስተማሯቸው   አማራንና በተለይም የሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ሕዝብ  ራሱን በማይጠራበት ስያሜ  አቢሲኒያውያን እያሉ ይጠሩታል። ይህን ተከትሎም   በተለይ ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ «ኦሮሞ ነኝ፤ ሐበሻ አይደለሁም» የሚል  ሐሳብ የሌለው ቡድንተኛነት ተፈጥሯል።
ለመሆኑ ኦነጋውያን ፈረንጆች ኦሮሞን በተለይም ከአማራው ለመለየት ሲሉ ያስተማሯቸውን  «አቢሲኒያዊ አይደላችሁም» በሚለውን ሴራ ውስጥ ያለውን «አቢሲኒያ» የሚለውን  የፈረንጆቹ  ስያሜ  ትርጉምና ታሪክ  ያውቁታል? መሐመድ አዴሞ ሐመሻ የሚለውን ቃል ትርጉም ቢያውቀው ይወደው ነበር፤ ግን የኦነግ ተማሪ ስለሆነ  ቃሉንና በቃሉ የሚጠራቸውን በደፈናው መጥላትን መርጧል።
 አቢሲኒያ የሚለውን ቃል ለፈረንጆቹ ያስተማረው  Friar Luis de Urreta የሚባል የዶምኒክ ቄስ ነው።  Friar Luis de Urreta በአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጽሐፈ ሔኖክ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝ  በላቲን ቋንቋ  «Historia eclesiastica, politica, natvral, y moral, de los grandes y remotos reynos de la Etiopia, monarchia del emperador, llamado Preste Iuan de las Indias» ሲል በጻፈው  መጽሐፍ ውስጥ ሐበሻ የሚለውን ቃል  በደቡብም ሆነ በሰሜን የኢትዮጵያ ምድር የሚኖሩ  ነገዶች ሁሉ  ራሳቸውን የሚጠሩበት ቃል እንደሆነ ይገልጻል።
በመጽሐፉ ገጽ 4 ላይ  ኢትዮጵያውያንን  ሐበሻ ከሚለው ቃል ላይ  ተነስቶ በላቲን ፊደል  corrupt አድርጎ በመጻፍ  Abissinois  ሲል ይጽፍና  ምድሩን ደግሞ Abissia ይለዋል። ከዚህ በመነሳት ነው እንግዲህ  Friar Luis Urreta በላቲን Abissinois  ሲል  corrupt አድርጎ የጻፈውን እንግሊዞች ቃሉን anglisized  ሲያደርጉ   ምድሩን ወደ Abyssinia፤ ሕዝቡን ደግሞ Abyssinians ወደሚል ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በማይገልጹበት ቃል የቀየሩት።
Friar Luis Urreta ሐበ ሻ የሚለውን ቃል corrupt አድርጎ ቢጽፈውና እንግሊዞቹ  Abyssinia እና  Abyssinians የሚለውን ስያሜ እንዲፈጥሩ ምክንያት ቢሆንም የቃሉን ትርጉም  ግን  ከውስጥም ከውጭም  አገኘሁትን ያለው አስቀምጧል። Friar Luis Urreta እንደነገረን ሐበሻ  ወይንም እሱ corrupt አድርጎ የጻፈው Abissinois  የሚለውን ቃል ኢትዮጵያውያንም፣ አረቦችም፣ ቱርኮችም  ይጠቀሙበት  ነበር። ኢትዮጵያውያንንም ሆነ አረቦቹንና  ቱርኮችን ጠይቄ  አገኘሁት  ባለው  የቃሉ ፍቺ  መሠረት  ሐበሻ  ወይንም እሱ corrupt አድርጎ የጻፈውን Abissinois  የሚለውን ቃል ከግብጽ በታች ያለ አገር መጠሪያ ያደርግና  ትርጉሙን  ሲገልጽ «It means a free and independent people who have never served a foreign masters or a recognized forign king» ይለዋል። እንግዲህ ሐበሻ የሚለው ቃል ትርጉም  «a free and independent people who have never served a foreign masters or a recognized forign king» ከሆነ ኢትዮጵያን  በተለይም የሰሜኑን ክፍለ ሕዝብ ፈረንጆች በሚጠሩት ስም «አቢሲኒያ» ብለው ካልጠራን ሞተን እንገኛለን የሚሉንና ይህንንም ካላደረጉ ፖለቲካ የሰሩ የማይመስላቸው  ኦነጋውያን «ኦሮሞ ሐበሻ አይደለም!» ሲሉ በውጭ ኃይል  ቅኝ ተገዝቶ ነበር ማለታቸው ይሆን? ነው ወደ ቅኝ ግዛት እንመልሰው እያሉን ይሆን?
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች  ተደርገው  በያ ትውልድ የቀረቡት የፈጠራ ትርክቶች  እውቀት ያከሉት በትርክቶቹ ዙሪያ በእንግሊዝኛው አጠራር  «WH questions» ከሚባሉት ሰባቱ ጥያቄዎች መካከል ቢያንስ  ሶስቱን  «WH» ጥያቄዎች ብቻ የሚጠቀው  ቀለም ቀመስ ቁጥር እምብም በመሆኑ ነው። ወያኔ የዘረጋው የትምህርት ሥርዓት እያፈራው ያለው ባለ ዲግሪ ምሩቅ የሚመረምር ሳይሆን በየአካባቢው ሲነገር የሰማውን እቶፈንቶ አጠናክሮ የሚወጣና  ከጋዜጣ headline በላይ የማያነብ second level illiterate ነው። «ሌሎችን አትስሟቸው» የሚል ድንቁር የእውቀት ጾመኛነት የትምህርት  መመሪያ ሆኗል። ይህንን ድንቁርና  እያስተማሩ  የብሔር፣ ብሔረሰብ ልሂቃን  በሙሉ የተማረ እየተባለ  ሲባል የሰማውን ሳይመረምር በሚደግም ካድሬ ሆነ! መሐመድ አዴሞ የሚባለው የኦነግ ካድሬም  በሐበሻ መሬት እየኖረ ስለ ሐበሻ ጥላቻ  በየቀኑ የሚጽፈው ኦነጋውያን ልዩ ዘር ለመፍጠር የደረቱትን  ድንቁርና  እየደገመና fact matter ስለማያደርገው  እንጂ በማይዋሽበት ዘመን እየኖረ  የሐበሻን  ምንነት አጣርቶ አውቆ አይደለም!
Filed in: Amharic