>
4:02 am - Wednesday May 18, 2022

በእጅ አዙር ለሲኖዶስ የቀረበው የኦነግ ቤተክርስቲያንን የመገንጠል ጥያቄ!!! (ዲ/ን አብርሃም ወርቁ)

በእጅ አዙር ለሲኖዶስ የቀረበው የኦነግ ቤተክርስቲያንን የመገንጠል ጥያቄ!!!
ዲ/ን አብርሃም ወርቁ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ቤተክህነት ጥያቄ ለሲኖዶስ ቀረበ። የዘንድሮው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓም ተጀምሮአል።
በመጀመሪያው ቀን ውሎም የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን ሪፖርት አፅድቆ ቃለ ጉባኤ ያዥ ሰይሞ እነሆ 31 አጀንዳዎችን ለመመልከት ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 13 አንድ በማለት ጀምሮአል።
 ከሁሉም አጀንዳዎች ትኩረቴን የሳበው ደግሞ  አጀንዳ ተራ ቁጥር 11 “የአባገዳ” ጥያቄ በተመለከ የምትለዋ ናት የበለጠ ደግሞ ጉዳዩን ትኩረት እድሰጠው ያደረገኝ ደግሞ ጉዳዩ ወይም አጀንዳው “የኦሮሚያ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን ስለማቋቋም ” የሚል በመሆኑ ነው ።
ይሄ ጉዳይ ድንገት እደን እንግዳ ደራሽ የተነሳ አጀንዳ አይደለም ለብዙ አመታት ሲብላላና ሲሰራበት የቆየና ያልተሳካ ዛሬ ምቹ ጊዜ ጠብቆ ብቅ ያለ በመሆኑ ነው።
እኔ ጉዳዩን በወፍ በረር ወይም በወሬ ሳይሆን በወርሃ መጋቢት 1998 ዓም ቁጭ ብዬ ከፈረሱ አፍ በመስማቴ ነው ።
ዛሬ ላይ የዚህ አጀንዳ ዋና አቀንቃኞች በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተለያየ የኃላፊነት ቦታ ላይ ሠርተው ደካማ የሚባል የሥራ አፈፃፀም ያሳዩና እንዲሁም በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥራአስኪጅነት በቆዩበት ወቅት በሙስና ተጨማልቀው በውርደት ከቦታው የተነሱ በቀጣይ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ ኃላፊነት የታጩ ሁሌም ኢሬቻ በመጣ ቁጥር ከቢሾፍቱ ሆረ አርሰዴ የማናጣቸውና የፓርላማ አባልም የነበሩ በአጣሪ ኮሚሽንነታቸው ጊዜ ምርጫ 97 ፍትሃዊና ነፃ ነበር ብለው ያሉን ትልቁ ሰውዬ የአጀንዳው ነዳጅ መስጫ ሲሆኑ :-
 እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ሌላኛው ሰው ደግሞ   በደብር እልቅና እንኳን ሳይሰሩ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ችሮታ በብሔር ስብጥር ሰበብ በኮታ ስም ለጵጵስና በበቁና ለኦሮሚያ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራአስኪያጅነት የታጩ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስና ደግሞ የዚህ አጀንዳ አቀጣጣይና ሲኖዶሱንም አሳማኝ ምክንያቶችን እዲደረድሩና የኮሚቴው አባላት ያስታጠቁዋቸውን የመከፋፈልና የመለያየት ትጥቅ በስብሰባ እዲያስተጋቡ ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው ናቸው።
 ከወለጋ እስከ አዲስ አበባ በመደራጀት በህቡዕ ሲንቀሳቀስ የነበረው የኦነግ መንፈሳዊ ክንፍ ቡድን አማካኝነት የሚዘወር በተራጀ ቡድን በኮሚቴ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ዋና አላማውም  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንንን ማዕከላዊነቱን መናድና የኦሮሚያ ክልልን ከቅዱስ ሲኖዶስ ለይቶ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን አዲስ አበባ አምስት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ካለው መንበረ ፓትርያርክ   ለመገንጠል አልሞ የሚንቀሳቀስ አደገኛ ስብስብ ነው ።
 አሁን ለጊዜው ስማቸው የማይጠቀሱ በተለይ 16 በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት እየሰሩ ያሉ የአጀንዳው  ተባባሪዎች አማካኝነት በተቻለ ፍጥነት ወደ ተግባር እንዲቀየር እየሰሩ ይገኛል በተለይ ጉዳዩ ሕዝባዊ ለማድረግ የሐሰት የድጋፍ  ፊርማዎች 85% ኦርቶዶክስ ካልሆኑት በማሰባሰብና አጀንዳው የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖረው በአባ ገዳዎች አማከኝነት እዲቀርብ ተደርጎ ቅዱስ ሲኖዶስን ለማጥመድና አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት ሆን ተብሎ የተሸረበ የሴራ አጀንዳ ነው ።
ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በማር ለተለወሰ መርዝ ምን ምላሽ ይሰጥ ይሆን?
አጀንዳው ተራ የአስተዳደር ጥያቄና በክልሉ  ቋንቋ የመስራት አለመስራት ጉዳይ እዳይመስለን ጉዳዩ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይቋቋም ብሎ ይጀምርና ግቡ ግን የኦሮሚያ ፓትርያርክና የኦሮሚ ሲኖዶስ እስከሚለው ድረስ መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ ትኩረት እንድንሰጠውና ቤተ ክርስቲያናችንን ከአደጋና ከመከፋፈል እንድንታደጋት  ለአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ህልውና በጋራ ልንቆም ይገባል ጊዜውም ደግሞ አሁን ነው! !!  ይቆየን። 
በቀጣይ የኮሚቴው አባላት ስም ዝርዝርና የተሰሩ አደገኛ ሥራዎች ይጋለጣል።
ይቀጥላል
Filed in: Amharic