>

"ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ ስህተት ነው" (የኦ.ክ.ር.መ አቶ ለማ መገርሳ) 

ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ ስህተት ነው”
የኦ.ክ.ር.መ አቶ ለማ መገርሳ 
ምዕራባዊ ኦሮሚያ ክልል በሚገኙት አከባቢዎች የኦሮሞ ነፃ አዉጭ ግንባር /ኦነግ/ ስራዊት ናቸዉ በተባሉና በኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት መካከል ላለፉት ቀናቶች ግጭት መታየቱን የአከባቢዉ የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬሌ ገልጹ።
ግጭቱን ተከትሎ የክልሉ ፕሬስዳንት አቶ ለማ መገርሳ በትላንትናዉ እለት እንደተናገሩት ሁኔታዉ በጣም እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል። ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ዘመናዊ መሳርያ ከታጠቀዉ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ ስህተት መሆኑን እና ትክክለኛ የትግል ስልት አለመሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ተችተዋል። አከባቢዉ ላይ ባለዉ የፀጥታ አለመረጋጋት ምክንያት የሰዎች እንቅስቃሴን እና የንግድ ሂደቱን ማገቱንም ገልፀዋል።
ጫካ የገቡት እነዚህ ወጣቶች ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ ከሽማግሌዎች ጋር በመሆን እንደሚሞክሩ እንዲሁም ማህበረሰቡ በጠረጴዛ ዙርያ መወያያት እንዳለበት አቶ ለማ አሳስበዋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ለተከሰተዉና ለሚከሰተዉ ችግር መፍትሄ መስጠት እንደሚያስቸግር ገልፀዋል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ
በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች «መንግስት የኦነግ ስራዊት ለማጥቃት ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ» በመቃወም ወጣቶች ሰላማዊ ሰልፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
Source:  DWAmharic
Filed in: Amharic