>

የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ምደባን በተመለከተ  ሶስት አማራጭ ቀርቦላታል !! (ሀብታሙ አያሌው)

የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ምደባን በተመለከተ  ሶስት አማራጭ ቀርቦላታል !!
ሀብታሙ አያሌው
ተወዳጇ ፖለቲከኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ከቀናት በኋላ ወደ አገር ቤት እንደምትሄድ ከሰማሁ በኋላ ለቤተ መንግስቱ ከቀረቡ ሰዎች መካከል አንዱን ብርቱካንን በየትኛው ኃላፊነት እንጠብቃት ? ስል የማጣሪያ ጥያቄ አቀረብኩ።  ቁርጥ ያለ መልስ ባይሆንም ከሰፊው የድርድር ሂደት እና ውይይት በኋላ ብርቱካን ከተከታዬቹ ዘርፎች አንዱን ለመቀበል መወሰኗን ከማረጋገጥ በቀር የትኛው ቢሮ እንደተሰናዳላት እርግጡን ለመናገር ለጊዜዎ ቃላት አጥረዋል።
የቀረቡላት ሦስት  አማራጮች 
1. የኢትዬጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
2. የእንባ ጠባቂ ተቋም
3. የኢትዬጵያ ምርጫ ቦርድ
በበኩሌ  እንደ ብርቱካን አይነት አቅምና በህዝብ ተቀባይነት ያለው ምርጥ ፖለቲከኛ ቦታው እነዚህ ተቋማት አካባቢ ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር። ምርጫዋና አማራጩ ይህ ብቻ ከሆነ ግን የምርጫ ቦርድ ተቋምን መርታ አንድ ቁልፍ የአገራችንን የፖለቲካ ሳንካ ብታስተካክል ጥሩ ይመስለኛል። እንባ ጠባቂ እና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ግን ፈፅሞ ቦታዋ እንዳልሆኑ ይሰማኛል
ስለ ብርቱካን እውነቱን ተቀበል!!!
ወንድ የተሰራው ከሴቶች ጡብ ነው።  ስብዕናውን ብንከፋፍለው እናት፣ እህት፣ አክስት፣ እጮኛ፣ የከንፈር ወዳጅ፣ ሚስት…የሚባሉ ፍርስራሽ ጡቦችን ነው የምናገኘው።
የሳይኮ አናሊስት (psychoanalises) አጋፋሪ ሲግመንድ ፍሮይድ ይሄንኑ ይነግረናል።  ለወንድ ልጅ እናት የሚስት መክተቻ የዕድሜ ማለዳ ስልቻ ናት። ሚስት ደግሞ እንደተራገፈ ጆንያ ምንም ያልያዘች እናት።  እናም ወንድን የሴት እጅ እንደተቀበለው መጨረሻ የመቃብር አፍ ተከፍቶ ያጠናቅቀዋል።  የሴት እጅ ቅብብሎሹ በግማሽ መንገድ ቢቋረጥስ ? ማለቴ አንድን ወንድ ከእናቱ እጅ የምትቀበለው ሌላ ሴት (ፍቅረኛ፣ የከንፈር ወዳጅ፣ ሚስት…) ቢያጣ ወንድ ህይወቱ የጎፈነነ ይሆናል።
እናማ ምን ለማለት ፈልጌ ነው፤ የጎፈነነ ፖለቲካችን ለዛ እንዲኖረውም የሴቶች መኖር የምርጫ ጉዳይ አይደለም።  ከዚህም በላይ ላቅ አድርገን እንየው ካልን ደግሞ እንግሊዛዊው ደራሲ ማክስዌልስ ሪስ ያለውን በመጥቀስ የሴቶችን ከፍታ ማሳየት እንችላለን። ማክስዌልስ…”የማፈቅራት  እዛ ከሌለች ገነት (መንግስተ ሰማይ) ለኔ ምኔ ናት?”  በማለት ይደመድማል። ይሄ ሰው እጅግ ተዳፈረ ያሰኛል። ግን እንዳያያዙ ተይዞ ነውና ምን ይደረጋል። ዓለምን ያለሴት አይቷት ወና ሆናበታለችና ገነትን ቢንቅ አይፈረድበትም።
ሴት ሲባል እንደው ሴት ሁሉ አይደለምና እንደየ አገባቡ ሲተረጎም ሲስማማ ቡርቴ ብርቷችን (ብርቱካን ሚደቅሳ) ወደ አልጫው ፖለቲካችን ጨው ሆነሽ ልትመጪ ጊዜው ከሆነ ልባችን በሃሴት ይሞላል።  ጨው ስላልኩሽ ጨው እኮ ጎምዛዛ ነው የሚሉ  አይጠፉምና ፍሬደሪክ ኒቼ ከኑሮ ወጪት ጨልፎ ባቀበለን አባባል ልቋጭ።  “…በጦረኞች ዘንድ እጅግ ጣፋጭ ፍሬዎች ተመራጭ አይደሉም። ስለዚህም እነዚህ ጦረኞች ሴቶችን አጥብቀው ይወዳሉ። ምክንያቱም እጅግ ጣፋጭ ከተባለችው ሴት እንኳ የሚገኘው ውጤት መሪር ነው።”  ጨረቃን ለማየት ጨለማ አልጫን ለማጣፈጥ ጨው እንደሚባለው መሆኑ ነው።
         ሰሞኑን አለማየሁ ገላጋይን ሙጥኝ ብያለሁ !
Filed in: Amharic