>
5:13 pm - Thursday April 19, 3556

ከፍቅር መንደር ሐመር ጉዞ ወደ ደቡብ..... (አቢሴሎም)

ከፍቅር መንደር ሐመር ጉዞ ወደ ደቡብ ተከተሉኝ!!! 
መልእክት ለጠቅላይ ሚኒስትራችን እናደርሳለን
አቢሴሎም የሙልዬ ልጅ
ከመሀል አዲስ አበባ ተነስተው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲያቀኑ በሁለት አቅጣጫ ይጓዛሉ በደብረ ዘይትና በቡታጅራ
 
 ከአ/አ በስተምስራቅ አድርገው በደብረ ዘይት ሲወጡ ደ/ዘይት አየር ሀይልን አይተው : በተፈጥሮ የታደለች: በቢሾፍቱ ሀይቅ ዙሪያ:በከተማዋ የተሰሩ ዘመናዊ ሆቴል፣ በርካታ መዝናኛ ሎጅ ያላት አለም አቀፍ ሀብታምና የተለያዩ ሀገር መሪዎች የሚዝናኑባት ከተማ ደብረዘይትን  ለቀው  : ሞጆ ይደርሳሉ :ሞጆ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ሲጣጠፋ ወደ ሀረርና ናዝሬት ሲጓዙ…….
ሞጆ ላይ ወደ ግራ ሲታጠፋ ጉዞ ወደ ደቡብ…… ከሞጆ ወደ ዝዋይ ያቀናሉ ወደዝዋይ ሲያቀኑ አቢያታና ሻላ ሀይቅን መሠረት ያደረጉ ፓርኮችና የላጋኖ መዝናኛ የሀይቅ ዳርቻ ቢችና ሎጅ ያገኛሉ ።
ጉዞ ወደ ሐመሮችመንደር….. ዝዋይን ከተማ አልፈው ሲጓዙ የራስታዎችን መንደር ሻሸመኔ ደርሰው ከሻሸሜኔ ከተማ ወደ ግራ ከተጓዙ ከ25 ኪ.ሜ በሇላ ሀዋሳ ይደርሳሉ!! ወደ ምስራቅ ከተጓዙ ወደ ባሌ ያቀናሉ ። እርሶ ግን ወደ ቀኝ ከተጓዙ : ጉዞ ወደ ውቢቷ ደቡብ ሲሆን ከሻሸመኔ በሇላ በበርበሬ ምርት የምትታወቀው ሀላባን ያገኛሉ!! ከሀላባ ወጥተው ወላይታ ሶዶ ይደርሱና የሶዶን ከተማ ለቀው ሲወጡ ጉዞ ወደ አርባምንጭ……..
 አርባምንጭ እስኪደርሱ በስተግራ በኩል ከጎኖ የማይለየው : ከሀገራችን ሁለተኛ የሆነውን የአባያን ሀይቅ እያዩ…  ” በነገራችን ላይ በዚህ ሀይቅ ውስጥ ከአለም አንደኛ የሆነ  47 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ የጋዝ ክምችት ይገኝበታል ተብሎ በታሎ ነዳጅ አውጭ ኩባኒያ በጥናት ተረጋግጧል ይባላል። ከአለም አንደኛ የነበረችው ራሺያ 27ቢሊዮን የጋዝ ክምችት ነበራት።!!”: የሀገራችንን የፍራፍሬ ምርት የሚሸፍነው የሙዝ : የማንጎ ምሮቶችን እየገዙ እየበሉ እየተዝናኑ ከአርባምንጭ ከተማ ይደርሳሉ። ከአ/አ 496km ጉዞ በሇላ አርባምንጭ ሲደርሱ በአባያና ጫሞ ሀይቅ መሀል ያለው የግዜር ድልድይና ነጭሳር ፓርክ አለ : በሀይቆቹ  ዙሪያ የተሰሩ መዝናኛዎች ትልልቅ አለም አቀፍ ሎጆች ያገኛሉ !!  አርባምንጮችን:የአዞ እርባታ ጣቢያንና በጫሞ ዳር የሚገኘውን የአዞ ገበያ ጎብኝተው አሳውን በልተው አረፍ ብለው : አ/ም አድረው : በጠዋት ጉዞ ወደሐመሮች መንደር ቢያደርጉ መልካም ነው ።
በጠዋት ከአ/ምንጭ ተነስተው ጉዞ ወደ ደቡብ ኦሞ..ከ40ምንጭ ከተማ በሴቻ በኩል ወጥተው ቁልቁለቱን ጨርሰው ሜዳውን ሲጀምሩ በግራ የጫሞ ሀይቅ በግራ በኩል እንደተለመደው የሙዝና የማንጎ እርሻ እያዩ ገዝተው እየበሉ ሲጓዙ ሼሌ አከባቢ ጥንት ጎንደሬዎች የሰፈሩበት በርካታ ጎንደሬዎችን ያገኛሉ። በነገራችን ላይ አልፈን የመጣንበትም የምንሄድበትም አከባቢ ከጣሊያን ጦር ጋር እየተዋጉ ሸሽተው የመጡ : ቤቴክርስቲያን ከሚያቃጥሉ ሀይማኖት ከሚያጠፉ ከነ ዮዲት ጉዲት ታቦትና ቅርስ ይዘው የሸሹ አባቶች : በውትድርና :በማስተማር :  በንግድና በሰፈራ ምክኒያት ከመጀመሪያው ንጉስ ምኒልክ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከአማራ ክልል ወደ ደቡብ የመጡ በሚሊየን የሚቆጠሩ አማሮች በደቡብ ይገኛሉ ።
ደቡብ ትንሿ ትዮጵያ ናት የሌለ ሰው የለም ። ከሼሌ ከተማ ወጥተን ኮንሶ እንደርሳለን !! በዚህች ሀገር ላይ ሰው ሁሉ እንደ ኮንሶ ቢሠራ ሀገራችን ኢሮፕ ትሆን ነበር። ኮንሶ በእጅ ጥበብ የተሠሩ በዩኒስኮ የተመዘገቡ ቅርስ ያላትና ያን ተራራና ድንጋያማ ቦታ በእርከን ሰርተው ስትመለከቱ : በሀሪፍ ዲዛይነር የተሠራ የአምለሠትን የጥበብ ቀሚስ ይመስላል ።
 ከኮንሶ ምድር ስትለቅ ሙቀቱ እየጨመረ ወይጦ በረሀ ብራይሌ ከተማ ትደርሳለህ።እንግዲህ የአርብቶ አደር ኑሮ እዚህ በረሀ ይጀምራል ። እዚህ የተጣለለ መሬት ላይ በወይጦ ወንዝ የሚለማ ትልቅ የጥጥ እርሻ አለ። በዚህ እርሻ ዙሪያ አራት የተለያዩና የሚግባቡ አርብቶ አደሮች ( ” ጸማይ : በና : ኤርቦሬ  : ብራይሌዎች ”) ይኖራሉ።
እዚህ በረሀ ላይ  ያዬሁት ከ10አመት በፊት ቋንቋውን የሚናገሩ ባህሉን የሚያውቁ 36 የብራይሌ ጎሳዎች ነበሩ። ቋንቋቸው የጠፋው ከጸማዮች ጋር ተጋብተው ተቀላቅለው ስለሚኖሩ ነው። ብሄርብሄረሰቦች የራሳቸውን  ቋንቋ ባህል አሳድገዋል ሲባል እነዚህ ብራይሌዎች ቋንቋቸውን እንዲያሳድጉ መንግስት መስራት እንዳለበት ከዚህ በፌት አሳውቀናል። ብራይሌዎች አሁን ያሉበት ደረጃን አላውቅም….
ከኢትዮጵያ ተነስቶ ታንዛኒያ የምገባውን የስምጥ ሸለቆውን  ሰንሰለታማ ተራራን በተመስጦ የፈጣሪን ስራ እያያችሁ በረሀውን : እያቆራረጣችሁ ስትጓዙ የወይጦ በረሀ ትጨርሱና ቀያፈር ከተማ ትገባላችሁ። ከከቀይ አፈር ስትወጡ አረንጓዴውንና ነፋሻውን አየር በተፈጥሮ ውበት ጋር የታደለችውን ከአ/አ 730km አዝናኝ ጉዞ በሇላ 16ቱ ብሄረሰብና የተለያዩ ኢ/ያዊያን የሚኖሩባት ውቧ ከተማ ጂንካ ደርሰው  አረፍ ይላሉ።
  ጂንካ በጃንሆይ ጊዜ በወታደሮች የተመሠረተች ከተማ ሲሆን ቀድሞ ከሚንሊክ ጀምሮ የነበረው ከተማ ባኮ ነበር።ዛሬም በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠሪያው ባኮ ነው ።
የጂንካ ከተማ በዙሪያዋ ባሉ ጠንካራ ገበሬ የአሪ ማህበረሠቦች ሲኖሩ ጄንካና አከባቢዋ በፍራፍሬ : በቡና: በኮረሪማና ከፍተኛ የበቆሎ ምርት ያለበት በርካታ የቱሪስት መስህብ ያለባት ና የቱሪስት መዳረሻ ከተማ ናት ።
ከጂንካ ከተማ በስተ ደቡብ ስትወጣ አለም እንደተፈጠረች ልብስ የማይለብሱ የሙርሲ : የቦዲና የባጫ አርብቶ አደር የሚኖሩበትና ሁለት ትልልቅ የማጎና የኦሞ ብሄራዊ ፓርኮች ከከተማው ውጭ ይገኛሉ ።:የዲሜ ና በሚኒልክ ግዜ ከጎጃም የመጡ አማራዎችና የኮንሶ ሰፋሪ ጎበዝ ገበሬዎች የሚገኙበት ዲመ ገርፋ ወይም ሀና ከተማ ዙሪያ የሚኖሩ ሲሆን በአከባቢው  በጣም ብዙ የብረት ማእድን ክምችት ይገኝበታል ። አሁን ላይ በሀገሪቱ ትልቁ የኦሞ ወንዝን መሠረት ያደረገ የስኳር ፋብሪካ በመሠራቱ በዞኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ለስራ የመጡ ማህበረሰብ የሚገኝበት አከባቢ ነው ። በጂንካ ከተማ ልታወራለት የምትችለው ልማት በአካባቢ የለም በከተማው ያሉ ትልልቅ ሆቴል : የመንስግት መስሪያ ቤትና የጋራ መኖሪያ ቤት የተሠራው በደርግ ነው።
ካለው የልማት መስፋፋትና የቱሪስ መዳረሻ ከተማ ከመሆኗ አንጻር ዶ/ር አቢይ ምርጥ የጠረፍ የእንዱስትሪና የቱሪስት ከተማ እንደሚያደርጋት ተስፋ አደርጋለሁ።
ጉዞ ወደ ሐመር
ጂንካ አረፍ ብላችሁ ከጂንካ ከተማ ወደሇላ በመመለስ የሐመር ወንድም የሆነውን የበና ማህበረሰብ የሚኖርበትን ቃቆና ቀያፈር ከተማን አቋርጣች ወደ ሐመሮች መንደር ዳመካና ቱርሚ ስትደርሱ ከጂንካ 128km ከተጓዛችሁ በሇላ ከቡስካው በስተጀርባ ከዘርሲዎች ፍቅር መንደር ትደርሳላችሁ።እኝህን የማህበረሰብ ክፍል ስታዩ የአለም መሪዎች: የፊልም አክተሮች :የአለም ቢሊየነሮች ከውጭ መጥተው እንዲጎበኙ ያደረጋየቸው አንዱ መገለጫቸው  ለሰው ልጅ ያላቸው ክብርና ፍቅር ነው።
ሐመረ 
ጀግናም ምሁርም የምታገኝበት አከባቢ ሐመር! 
ሰውን የሚወድ ባህሉን የሚያከብር ሐመር 
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከሄደ የማይመለስበት
በፍቅራቸው የምትማረክበት : የፍቅር ሀገር ሐመር!!!
ፍቅረማርቆስን ከጎጃም ምድር በፍቅራቸው ያንበረከኩት ሐመሮች : ዛሬም ድረስ ባህላቸውን ጠብቀው : ከቀያቸው ወጥተው  ለዘመናዊ ትምህርም ሆነ ለስራ ውጭ ሀገር ቢሄዱም ተመልሰው በሬ ዘለው ትዳር የሚመሠርቱ ወግባህላቸውን አክብረው የሚኖሩ ሀመሮች ለሰው ልጆች ክብር ያላቸው በመሆኑ ባህላቸውን አክብረህ ከኖርክ: በባህላቸው መሠረት : አብረሀቸው እንድትኖር ለልጆቻቸውን አጋብተው ያኖሩሀል ።
ከሀመር ፍቅር ይዞት ማግባት የፈለጉ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና የውጭ ዜጎች ትዳር መስርተው : ልጅ ወልደው በሐመር የፍቅር መንደር የሚኖሩ በርካታ ናቸው ።
በኢትዮጵያ ታሪክ ሁለት የአፍሪካ ሀገር ኬኒያና ሱዳን አዋሳኝ ሆነው : እስከዛሬ የሀገር መከላከያ ሳይኖር ወራሪንም : ሌባንም የሀገራቸውን ዳር ድንበር አስጠብቀው : መክተው የሚኖር ማህበረሰብ ነው ። በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ለውጭ ሀገር አዋሳኝ ኖሮዋቸው የሀገር መከላከያ ስራዊት በክፍለ ጦር በብርጌድ በሻለቃ ዳር ድንበራችን ሲጠበቅ የደቡብ ኢትዮጵያን ከወራሪም ከሰርጎ ገብም ጠብቀው የኖሩት  በኬኒያ በኩል ሐመር :ካሮና የዳሰነች አርብቶ አደሮች ሲሆኑ በሱዳን የኛንጋቶም : የቦዲና የሙርሌ አ/አደሮች  ናቸው ።
 የመሀል ሀገር ሰው ቁጥሩ ቀን በቀን ሲጨምር : የመሀል ሀገር ሰው ሲማር ሲሰለጥን : እነሱ ግን ዛሬም አለም እንደተፈጠረች ይኖራሉ ። ከሰርጎገብ ድንበር ገፊና ዘራፊዎቾ የኬኒያና ከደቡብ ሰዳን ጋር እየተዋጉ ህይወታቸውን ንብረታቸውን እስካሁን ሲያጡ ኖረዋል ። ባጋጣሚ የተማሩትም : ከዚህ አከባቢ  የሚወጡትም ጎበዝ እንግሊዝኛ ተናጋሪና ውጤታማ በመሆን ሀገራቸውን ያገለግላሉ ።
መልእክት ለዶ/ር አቢይ
1) አርብቶ አደሩ የተረጋጋ ሰላም አግኝቶ እንዲኖር:በዘመናዊ መልኩ ከብቶችን እንዲያረባ ሲባል መሀል ሀገር ያለ መከላከያ ወደ ሁለቱ አዋሳኝ አከባቢ እንዲሰፍር
2) በእውቀታቸውም በእንግልዘኛ ተናጋሪነታቸው ጎበዝ የሆኑ : በቁንጅናም ቆንጆ የአርብቶ አደር ሴቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ እንዲካተቱ ! የሚገርመኝ አየርመንገዳችን  ውስጥ የአርብቶ አደር ልጆች አለመኖር : እንግሊዝኛ ቋንቋም ጎበዝ ናቸው ።ይታሰብበት
3) በእውቀታቸው ጎበዝ የሆኑ የአርብቶ አደር ልጆችን በክልልና በፌደራል መንግስት ወደ አመራርነት ማምጣት
4) ሰፋፊ መሬቶች በመኖራቸው ለልማት ምቹና የልማት ኮሪደር  ስለሆኑ መሠረተ ልማት እንዲሟሉ ማደርግና እንደውጭው አለም ምርጥ የመዝናኛና የፋብሪካ ከተማ መመስረት
5) በርካታ ብሔራዊ ፓርኮች ያሉ ሲሆን የዱር እንስሳት በህገወጥ አዳኞች እየጠፋና ያለ አግባብ የተለጠጠው የስኳር ፕሮጀክት እርሻ ምክኒያት ደኖች እየተጨፈጨፉ:እየተቃጠሉ ስለሆነ በጥናት ላይ የተመሠረተ ቅደም ተከተል ተጠብቆ እርሻው ቢታረስ። ለእንስሳቱ ማምሻም እድሜ በመሆኑ
በርግጠኝነት ዶ/ር አቢይ ይህ መልእክት ከደረሳቸው ይተገብሩታል! !!!
ክብር ለደቡብ ኦሞ አርብቶ አደሮች! !
ኢትዮጵያን ፈጣሪ አብዝቶ ይባርክ!!!
Filed in: Amharic