>

" ብቀላ በባህር ማዶ " (አለባቸው ደሳለኝ)

” ብቀላ በባህር ማዶ “
አለባቸው ደሳለኝ
*ህዝቡ የኢትዮጵያን ባንድራ ይዞ እንዳይገባ ኮንቴነር ውስጥ እንዲጥል ተደርጎ የኦነግ የትግል አርማ ለምን በማዳበሪያ ከረጢት ውስጥ ገብቶ እንዲታዱል ተደረገ :: ብቻ ይህን በመሰለ አሳዛኝ ሁኔታ ኦነግ እና  ትሐት በመተባበር ባህር ማዶ ተሻግረው የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን  ተበቅለዋቸዋል!!!
 
አንድ ሰው በጥላቻና አፍራሽ በሆኑ ስሜቶች ተሞልቶ እንዴት ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል ባይገባኝም እንዴት እንደሚበቀሉ  ለወራቶች እንቅልፍ አጥቶው  መኖራቸው ይገርመኛል ::
ሰዎች በግላቸው ፍላጎት በሚመኙትና በተመቻቸው ሁኔታ በግልብ ስሜት ሲያብዱ ስሜታቸውን  በጠባብ ዘረኝነት ላይ የአስተሳሰብ  ሚዛናቸው ሲቃወስ እውነቱን መናገር ምን ያህል አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ሳልረዳ ቀርቼ አይደለም ::
ሆኖም ግን ጉዳዩ የጋራ ጉዳያችን የኢትዮጵያ ክብር የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰብዕና የሚጎዳ በአደባባይ በፍራክፈርት እስቴድዮም ሲፈፀም አይተን ዝም ብለን ማለፍ ተገቢ ነው ብየ  ስለማላምን እንዲህ ባለ ጊዜ ደግሞ መባል ያለበትን ለማለት መደረግ ያለበት ለማለት ድፍረቱ እያነሰን በህብረተሰቡና በጋራ ሐገራችን ላይ.ከፍተኛ የጋራ ችግር ሲደርስ ዝም ብለን የምናልፈው ጉዳይ አይሆንም ::
ዛሬ የማተኩረው በጀርመን ፍራክፈርት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አቀባበል ላይ  ብቀላ እንዲፈፀም በማድረግ ሐላፊነቱን የሚወስዱት የበርሊኑ አምባሳደር ኩማ ደመቅሳና የፍራንክፈርቱ ቆንስል ጄኔራል ምህረት አብ ሙሉጌታ ናቸው ::
 እነዚህ ግለሰቦች መንግስት በሰጣቸው ኃላፊነት በመጠቀም እራሳቸው ባስመረጧቸው ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር በአውሮጳ የሚገኙት ኢትዮጵዬውያን ስሜት በጥልቀት የሚጎዳ ሳቦታጅ ሰርተዋል ::
ከዚህ ውስጥ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ድርጊት የአብይ ወደ አውሮፓ እንደሚመጣ ሲታወቅ ማለት  አንድ ወር ሲቀርው የይስሙላ ኮሚቴ ፍራክፈርት ላይ ተመሰረተ ተባለ :: ከአመሰራረቱ ጀምሮ ችግር የገጠመው ኮሚቴ አስራ አምስት ቀን የእውር ድንብሩን ሲያንቀላፋ ከርሞ ወደ ተለያዩ የአውሮፖ ኢንባሲዎች ኮሚቴ እንዲያዋቅሩ መልዕክት ያስተላልፋሉ :: አብይ ፍራንክፈርት ለመምጣት አስራ አምስት ቀን ሲቀራቸው  እኛም በለንደን ኢንባሲ አማክኝነት  በብዙ ውጣ ውረድ ኮሚቴ አቋቁመን መንቀሳቀስ ጀመርን ::
በሁለት ሳምንት ውስጥ ለንደን የሚገኘውን ህብሩተሰብ ይዞ ወደ ፍራክፈርት መጏዝ የማይታሰብ ቢሆንም  አቅማችን በሚችለው  መጠን መቀስቀስ ጀመርን :: ነገር ግን ጀርመን ከሚገኜው ዋና ኮሜቴ የሚመጡ ውሳኔዎችና መልእክቶች በተዋረድ በኢንባሲው ተወካይ አማካኝነት ይገለፅልን ነበር ::  ኮሚቴው ከሚያስተላልፈው ማሳሰቢያዎች ውስጥ  ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በእጅ ከሚያዘው ውጭ እረጃጅም ሰንደቅ አላማዎች እንዳይሰሩ ወደ ሜዳውም እንዴይገቡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጭምር መስተላለፉና ማገድ ተጀመረ ::
 የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ  የኮሚቴውን ውሳኔ እጅግ አድርጎ ተቃውሟል ::
ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመጥን የአቀባበል ስነስርአትም እየተደረገ ስለመሆኑ ይግል ጥርጣሬውንና  የሚደረገውም የአቀባበል ዝግጅት ውጤታማ እንዲሆን የማፈልጉ ግለሰቦችም ሆነ  ኢንባሲዎች እንዳሉ ጥርጣሬውን በመግለፅ ውሳኔውም ተቀባይነት እንደለለውና በቃለ ጉባኤ እንዲያዝለት ጭምር ጠይቆ ተቃውሞውን አስመዝግቧል ::
ሆኖም ግን ከተወሰኑት የኮሚቴ አባላት ጋር በመነጋገር እረጃጅም ሰንደቅ አላማዎችን አሰርተን በድብቅ ይዘን ወደ ፍራንክፈርት ተጏዝን ::
ፍራንክፈርት እንደገባን  አቶ ምህረት አብ ሙልጌታን ቆንሲል ጀኔራል ከለንደን የአብይ አስተባባሪ ኮማቴ እና አርቲስቶች እንደመጣን ማንን ማግኜት እንደሚኖርብን ከኢንባሲ የስም ዝርዝራችንን የያዘ ደብዳቤ እንደለን ፣ አሁን ሆቴል ውስጥ እንደምንገኝ ገለጥንላቸው  ::
አቶ ምህረት አብ በቁጣ ለመሆኑ ማነው ስልኬን የሰጣችሁ ደግሞስ በዚህ ስዓት ለምንድ ነው የደዎላችሁት ብለው አካኪ ዘራፍ በማለት አላናግርም ብለው በሀይለ ቃል ገሰፁን :: ተስፋ ባለመቁረጥ ስልኩን እንዳይዘጉና እንዲያነጋግሩን ይህን የማያደርጉ ከሆነ ሀላፊነቱን እሳቸው እንደሚወስዱ እኛም ወደ ለንደን እንደምንመለስ ነገርናቸው ::
ጧት ሁለት ስዓት ኢንባሲ እንድትመጡ ብለው ቀጠሩን ካረፍንበት ሆቴል እሰከ ኢንባሲው የተከራየነውን መኪና እያሽከረከርን አንድ ስአት ከአስር ደቂቃ በፈጄ ጊዜ ኢንባሲ ስንደርስ ቢሯቸውን ቆላልፈው የሉም
ያገኜነው አንድ ግለሰብ ምንም የሚውቀው ነገር እንደለለና ሊረዳን እንደማይችል ነግሮን የሚሙለከታቸው ባለስልጣኖች   ስልክ ቁጥሮች እየደወለ  ሞክሮ ሁሉም ዝግና ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው ነገረን ::
በዚህ ችግር ውስጥ ሆነን የለንደኑ ምክትል አምባሳደር  አቶ አባቡ መጡ :: የሙዚቀኞቹ ልብስና የሙዚቃ መሳሪያዎችና ሙዚቀኞቹ  ተዘጋጅቶላችዃን የተባለው የመግቢያ ባጅ አለማግኜታችንና ትጠይቃላችሁ የተባለው አምስት ጥያቄ በኮሚቴው መከልከልን፣ ሁለት ጥያቄ  ብቻ መፈቀዱን ነገርናቸው ::
ምክትል አምባሳደሩ ያደረጉት ጥረት ሁሉ አልሳካላቸው ብሎ እሳቸውም እንደኛው ውጭ ቆሙ : በመጨረሻም ይመለከታቸዋል የተባሉትን ባለስልጣኖች በሙሉ እስቴድም ውስጥ በዲፕሎማት ይለፍ  ገብተው ሊያገኟቸው  ባለመቻላቸው አራት ስአት ሙሉ ከስቴድዮም ውጭ ተቀምጠን ::
በመጨረሻም አቶ ምህረት አብ ሙልጌታ ለግዜው ስማቸውን ካልያዝኩት የሐገር ባህል  ልብስ ከለበሱ  ሴት ወይዘሮ ጋር እየተንጎራደዱ አልፈውን ሊገቡ ሲሉ በስልክ እንዳነጋገርናቸውና በቀጠሩን ስአት ቢሯቸው ሔደን እንዳጣናቸው ነገርናቸው :: ታዲያ እኔን ምን አድርግ ነው የምትሉት ሒዱና ኮሚቴውን ጠይቁት ብለው ጥለውን  ሔዱ ::
በምሐሉ የሾሻል ሚዲያው አክቲቢስት ቶለሳ ኢብሳ የተፈጠረውን ሁኔታ ይሰማና  ችግር እና የብሔር ብሔረሰቦችን ትርኢት ለማሳየት የተዘጋጁ አርቲስቶች መከልከላቸውን ኢንባሲውንና ኮሚቴውን በቪድዮ ማጋለጥ ጀመረ ::
ይህ ሁሉ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እስቴድዮም ሊደርሱ አስራ አምስት ደቂቃ ሲቀራቸው ተፈቅዶልን ወደ እስቴድዮሙ ገባን ::
 ውድ የሐገሬ ልጆች በቅድሚያ የተፈቀደልን  አብይ  በሚገበበት በር መግቢ ላይ በመቆማችን ብቻ ሲሆን እስቴድዮም ከገባን በዃላ ያየሁት የሰማሁት ብነግራችሁ ለዚህ ፅሁፍ የማይሙጥን ሁኖ ስላላገኜሁት ትቸዋለሁ :: እጅግ ግን ያዘንኩት ፎቶግራፈር ጋዜጠ ኛ እንደመሆኔ መጠን አይኖቼን እንደንስር አሞራ ሁነው እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ተከታትየ ለታሪክ ቀርጨ አስቀምጫቸው አለሁ ::
ኮሜቴውም ሆነ የኢንባሲው አባሳደርና ኩማ ደመቅሳና ምህረት አብ ሙልጌታ እንዴት የኢትዮጵያን ህዝብ ቢንቁ ነው ? ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ከፍተኛ የሐገር ውስጥና የውጭ ድፕሎማቶች  የተቀመጡበት መድረክ በኦነግ የትግል ምልክት እንዲቀባ የተደረገው :: ይህን ኮማቴውም ሆነ አምባሳዳሮች ሳይተባቡሩ ተሰርቷል ቢባል የማይታመን ነው ::
ሌላው የዝግጅቱ ፕሮቶኮል አምባሳደር ብርቱካን እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለመን ችላ ኡሉት ?
ህዝቡ የኢትዮጵያን ባንድራ ይዞ እንዳይገባ ኮንቴነር ውስጥ እንዲጥል ተደርጎ የኦነግ የትግል አርማ ለምን በማዳበሪያ ከረጢት ውስጥ ገብቶ እንዲታዱል ተደረገ ::
ብቻ ይህን በመሰለ አሳዛኝ ሁኔታ ኦነግ እና  ትሐት በመተባበር ባህር ማዶ ተሻግረው የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን  ተበቅለዋቸዋል ::
ህዝቡን በቅጡና በወጉ ሳያስተባብሩ ከመቶ ሽህ ህዝብ በላይ የሚይዝ እስቴድዮም በብዙ ሽህ ኢውሮ ተከራይተው ባዶ እስቴድዮም ይዘው ጠብቀዋቸዋል :: ይህ ሊሰጥ የሚችለውን ትርጉም የሚያውቁት የፍራክፈርቶቹ ሕውሐትና የዳዊት ኢብሳ ኦነግ ብቻ ናቸው :: ለኛ ግን አብይ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ልጆች ከጎ ናቸው እያሉ  ደጋፊ እና ተቀባይነት የለላቸው ለማስመሰል የተደረገ የጅላጅል ድርጊት ኮንንነው ብቻ የምንልፈው ሳይሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆነ የጠቅላ ሚኒስትሩ ፅፈት ቤት አስቸኳይ ምርምራ እንዲያደርግል በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን :: በመጨረሻም ከለንደን የሔደው  የአብይ አስተባባሪ ኮሜቴ ሁኔታዎችን ከገመገመ በዃላ የወሰደውን እርምጃ  በመድረኩ ላይ በአለባቸው ደሳለኝ አማካኝነትየተፈፀመውን አሳዛኝ ድርጊት በድፍረት አጋልጦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ታላቋ ብርታንያ እንዲመጡ ጋብዞ  በሰላም  ተሙልሷን ::
በዚህ አጋጣሚ ግን ለቀን ጅቦች ለመንጋ ጭፍን ፖለቲከኞች ለሜንጫ አብዮተኞች ፣ ሁላችንም እንደ ቅጠል ተቀንጥሰን እንረግፋለን እንጅ አብይ አህሙድ የሚመሩትን የለውጥ ሂደት ለአንድ ሰከንድ ልታቆሙት አትችሉም ::
Filed in: Amharic