>

የኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክ ማን ነው? (መንግስቱ አሰፋ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክ ማን ነው?
መንግስቱ አሰፋ (ዶር.)
ሰው ራሱን የሚገልፅበት፣ ሌላውን የሚያይበት፣ ሀገሩን የሚወድበት የየራሱ መንገድ አለው።
ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት ባኅሪይ፣ አንድ ዓይነት ሥራ፣ አንድ ዓይነት የትምህርት መስክ እና የትምህርት ደረጃ፣ ተመሳሳይ መልክ ሊኖረው አይችልምና። አንዱ ከሌላው ይለያል እንጂ
አይበልጥም ደግሞም አያንስም።
የኛ ማኅበረሰብ በታሪክ በንጉሣዊ ሥርዓት እና ሌሎች የማኅበረፖለቲካዊ፣ ኃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ትውፊቶች በተገነባው የበላይ እና የበታች (ጌታ እና ሎሌ) ዜጋ የሚፈጥር ዕሴቶች የሞሉበት ማኅበረሰብ ነው። በርግጥ ይህ አኳኋን የኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገሮችም የተለመደ ነው።
የተወሰኑ የሥራ ዓይነቶችን ከሌሎች አስበልጦ የማየት፣ በደቦ የተወሰኑ ሰዎችን የማጀገን አባዜ ትላልቅ ሚዲያን እንኳን እስከማይቀሩት ድረስ እያጠቃ ያለ ችግር ነው።
የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከጥንትም ጀምሮ “አውቅልሃለሁ ባይነት” የተጠናወተው፣ ተማርኩ የሚለው የማኅበረሰብ ክፍል ሀገር ላይ እንደ እንጎቻ ( cake ) ሲጣሉበት ነው የኖሩት።
Elitist politics which is full of revolutionary sentiment every other time. ለዚህም ነው alternative pro poor pro development political economy
policy ላይ ከመከራከር ይልቅ እርስ በርስ በመወዳደር የምንባላው።
ይህ ደግሞ በዓለም የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት የሆኑ ሕዝቦችን የያዘች ሀገር አቃፊ እና አቻቻይ ባሕል ያለው ማኅበረሰብ (egalitarian society) መፍጠር እንዲየቅታት ሆኗል።
ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ሳይኖረን ደግሞ ዴሞክራሲያዊ የመንግሥት ሥርዓትን መገንባት አዳጋጅ ነውና።
እንደ አንድ የተረጋጋ ማኅበረሰብ ማሰብ ያለብን ነገር ቢኖር ሁሉም ሰው በራሱ ለሀገሩ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት የራሱ የማይተካ ሚና አለው።
ስለዚህ የኢትዮጵያዊነት ትልቁ ማሳያ፣ ውኃ ልኩ፣ የሀገራችን ጀግና፣ የነፃነት ታጋይ፣ የኢትዮጵያ አርበኛ ማን ነው? መስፈርቱስ ምንድር ነው?
የኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክ…የሀገር ጀግና ግን ማን ነው?
~ ብዙ ጣጣ የማያውቅ፣ የብሔር ወይም የመደብ አሊያም የውድብ ምድብ እና ጥያቄዎች እንዲሁም ውስብስብ ርዕዮተዓለማትን የማይረዳው ከጎረቤቱ ጋር በሰላም የሚኖር፣ የሀግራችን ምጣኔ ሐብት የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና ሥራ የሚሠራ ምስኪኑ ገበሬ (85% የሀገራችን ሕዝብ) ጀግና
ነው? የኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክስ ሊሆን ይችላል?
~በውዴታው ለሀገር ክብር እና ሉዓላዊነት ነፍሱን ሰጥቶ በጦር ግንባሮች ባልተመቻቸ የሕይወት ውጣውረድ ሀገሪቱን የሚጠብቃት ደጀን የመከላከያ ሠራዊት ተራ አባል?
~ጸጥታን የሚያስከብር፣ ወንጀልን የሚከለክል፣ ሲከሰት የሚመረምረው፣ የጸረ ሽብር ግብረኃይል አባሉ የኢፌዴሪው ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባል ሆኖ መስናን የሚጸየፈው፣ ሰላም ወዳዱ ተራ ፖሊስ?
~ በውድቅት ልሊት ተረኛ ሆኖ ልትሞት የደረሰችን እናት የሚገላግል፣ “ልጅም ጤና እናትም ደህና” አድርጎ የሚሸኘው የማኅፀን እና ጽንስ ሕክምና ባለሙያ?
~ጥቂት ሳምንታትን ብቻ ያስቆጠረችን ለቤተሰቧ የመጀመሪያ ሕጻን በጽኑ ስትታመም CPR ሠርቶ ከሞት አፋፍ መልሶ የወላጆችን ተስፋ የሚያለምልመው የስድስተኛ ዓመት የሕክምና
ተማሪው ኢንተርን?
~በቅንነት ነግዶ ግብርን በታማኝነት ከፍሎ ከራሱ ጋር ሌሎችን ድሆች በሰብዓዊነታቸው ብቻ ራርቶላቸው የሚረዳቸው ነጋዴስ?
~ትውልድን መቅረፅ ሀገርን መቅረፅ ነው፤ እሱም ከቤተሰብ ይጀምራል ብላ የቤት እመቤት ሆና በልጆቿ ውስጥ የሀገርን ነገ የምታንፅ እናትስ?
~በስፖርት አሸንፎ ሀገሩን የሚያኮራውስ?
~በእውነት የሚፈርደው ተራ ዳኛስ?
~በማይረባ ደመወዝ የሀገር መሪና ባለሙያን የሚያሰለጥነው በየደረጃው ያለው የትውልድ አናፂው መምህርስ?
~ሕይወታቸውን ከአደጋ ጋር እያጋፈጡ ለበሽታ በሚያጋልጡ ሆስፒታሎች የጽዳት ሥራ የሚሠሩ ውድ የሀገር ልጆችስ?
~ ….ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው እኛ ዝም ብለን
የምንመለመለከታቸው ተራ ዜጎቻችን…የኛን “ተሿሚ
ኢትዮጵያዊያን/የኢትዮጵያዊነትን የውኃ ልኮች” እንዴት ይመልከቱ?
እነሱስ “በደንብ ኢትዮጵያዊ ለመሆን” ምን ማድረግ
ይጠብቅባቸዋል?
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከተራ የሕይወት ኩነቶች እና ፀጋዎች (mundane/ordinary) ይልቅ የበላይነት እንዲሰማው፣ “የተሻለ” እኔነት እና ኅልወትን የመፈለግ ባኅርይ አለው። ራሱን
እና ወገኑን…ልጆቹን “extraordinary” እንዲሆኑ ይመኛል። ይህ ምንም ችግር የለበትም። ግን mundane is beautiful as well. We should able to to respect, cherish,
enjoy and maximize things which are mundane.
Extraordinariness is a bonus but mundane things are necessity. The quest of our existential utopia in the unattainable patriotic fantasies should not eclipse the irreplaceable nature, beauty and absolute necessity of the ordinary and the mundane.
ለዚህም ይመስለኛል አንድን ሰው በሆነ ነገር ታዋቂ፣ ተናጋሪ፣ እና በተለይ ፖለቲከኛ ከሆነ ከመሬት አንስተን extravagantly ጀግና፣ የሀገር ፍቅር እና ማንነት መለኪያ፣ ለሀገር እንደሱ ያበረከተ እንደሌለ አድርገን የምንናገርለት።
ነገር ግን እስኪ አስቡት….እከሌ የኢትዮጵያ ውኃ ልክ ከሆነ:-
~የሱ ሙያ የሌለውስ?
~ ከሱ የተለየ አስተሳሰብ ያለውስ?
~እንደሱ ያልተማረስ?
እንደው ለነገሩ የዚህስ ምደባ መስፈርቱ ምንደር ነው?
መዳቢውስ ማን ነው?
Who is more and/or less Ethiopian than any Ethiopian? Are we all obliged to endorse anyone whom the unmindful majority call “a hero”
without any tangible convincing accomplishment?
Is this not an absurdity?
According to Peter Principle of Hierarchiology ,
the unmindful mob or managers promote people to their “level incompetence”, ….and as a result,
he complains that ” … everywhere I go with few exceptions, incompetence is rampant,
incompetence is triumphant”.
ይህ አደገኛ ነገር ነው።
እኛም አንዱን ዛሬ የሆነ ነገር ስላደረገ ብቻ (በፖለቲካ ተቃዋሚ ሆኖ ዋጋ ሲከፍል ደግኖ ይብሳል) የሀገር አባት፣ የተለየ ባለውለታ፣ አልፎም የኢትዮጵዊነት ውኃ ልክ ስናደርግ ነገ ለዚያ ነገር ታማኝ እና ብቁ ሳይሆኑ መቅረታቸው ተፈጥሯዊ ነገር ነው።
ምክንያቱምን ከማንም አይበልጡምና ይስታሉ፣ ይደክማሉ።
እንደ እኛው ናቸውና! ያኔ ምን ሊሁን ነው? እኛስ የሀገር ባለውለታነትን ከመጠን በላይ በመለጠጥ “የኢትዮጵያዊነት ውኃ ልክ”
ስናደርግ ለሀገር ከመጥቀም ይልቅ እንጎዳታለን።
የቡድን ፖለቲካ የአብዛኛውን ሰው የሕይወት ዘርፉን ሲቃኝ ደግሞ ለይቶ ማጀገን አለ። የነ እንትና ጀግና የኛ ጀግና አይደለም በሚባልበት ሀገር ነገሩን ከባድ ያደርጓል።
የቡድን እንጂ የሀገር ጀግና ማግኘት ይከብዳልና። ስለዚህ በቡድን ተነሳነሳስተን የሀገር ስሜት መለኪያ ውኃ ልክ አናስቀምጥ!
ሰዎች ስላበረከቱት አስተዋፅዖ ይመስገኑ። የራሳቸው አመለካከት ይዘው ኢትዮጵያዊ ይሁኑ። ግን ዝም ተብለው በመንጋ አይጀግኑ።
“የኢትዮጵያዊነት መለኪያ ውኃ ልክ” የሚባል ነገር ግን ትክክልም ጠቃሚም አይደለም። ሁሉም ሰው እንደ ብር ኖቶች አንድ ዓይነት ይሁኑ ማለት አዋቂነትም ለሀገር አሳቢነትም አይደለም።
ይልቁንም የትውልዶች ፍሰት ያለማቋረጥ በዘመናት
የሚቀርፀውን አንድን ማኅበረሰብ ማንነት (ኢትዮጵያዊነት) በአንድ ጊዜ እና ቦታ በኖረ አንድ ወይም የተወሰኑ ግለሰቦች መለኪያ ውኃ ልኩን መለከት ኢትዮጵያዊነትን መውደድ እና
ማክበር ሳይሆን በተቃራኒው ነው።
ሁላችንም ለኢትዮጵያዊያን እኩል እናስፈጋታለን።
እስኪ ተራ ሥራ ሠርተው ኢትዮጵያን የሚያኖሩዋትንም ተራ
ሰዎች ጀግኖች እንበላቸው!
Filed in: Amharic