>
7:48 am - Tuesday December 6, 2022

ከህወሓት ሰፈር አስገራሚ የመደራደሪያ ሀሳብ ተሰንዝሯል!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ከህወሓት ሰፈር አስገራሚ የመደራደሪያ ሀሳብ ተሰንዝሯል!!!
ሀብታሙ አያሌው
1.ህወሓት ጌታቸው አሰፋን አሳልፌ የምሰጠው አቶ ገዱ  አንዳርጋቸው ከታሰረ ነው ብላለች!
 
 2. የአ/አበባ ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አልታሰረም ይልቁንም የለውጡ አመራር ቀኝ እጅ ከሚባሉት አንዱ ነው!
የሰሞኑን የእስር ዘመቻ ተከትሎ ከህወሓት ሰፈር አስገራሚ መደራደሪያ ተሰንዝሯል። “ጌታቸው አሰፋን አሳልፈን የምንሰጠው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው  በቅማንት ላይ የዘር ማጥፋት ፈፅሟል ተብሎ ከታሰረ ብቻ ነው”  የሚል አስገራሚ መከራከሪያ።   ከዚህ ጎን በጎን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ  በቁጥጥር ስር ውሏል የሚል መረጃም መሰራጨት ጀምሯል።
ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ የለውጡ አመራር ቀኝ እጅ በመሆኑ በቅርቡ ከኢሚግሬሽን ፋይናንስና አስተዳደር ኃላፊነት ተነስቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተደርጎ የተሾመ ነው።  ዘላለም መንግስቴ አዲስ አበባ ቅድስተ ማርያም አካባቢ ተወልዶ ያደገ አባቱ ዛሬም በትውልድ ቀያቸው በላስታ በግብርና የሚተዳደሩ፤ ወላጅ እናቱም የላስታ ሰው ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚኖሩ ናቸው።
ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ  በቅርቡ ከዳያስፖራ ወደ አገር ቤት የገቡ የፓርቲ መሪዎችን አክቲቪስትና ጋዜጠኞችን ደህንነት በቅርበት ሲከታተል እና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ሲያደርግ እንደነበረም እማኞች ያስረዳሉ።
የለውጥ አመራሩ ከሚተማመንበት አጋዥ ሃይል አንዱ እንደሆነ እና ከአፍ መፍቻ ቋንቋው ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮሚኛ፣ ትግሬኛ ፣ ሶማሌኛ ፣ አረብኛ አቀላጥፎ የሚናገር የተማረ ሰው እንደሆነ የቅርብ ሰዎች ያስረዳሉ።
በተለይ ከአዲስ አበባ ወጣቶች መታሰር ጋር ሆን ብሎ ስሙን ለማገናኘት  የተደረገውን ሙከራ ውድቅ የሚያደርጉት ለመንግስት የቀረቡ አካላት ከሹመት በኋላ ቆይታው ለልዩ ስልጠና በአሜሪካ እንደነበረም አረጋግጠዋል።
Filed in: Amharic