>

የህግ የበላይነት የሠፈነባት አገር እንዴት እንመስርት? (ሰይድ የሱፍ አሊ)

የህግ የበላይነት የሠፈነባት አገር እንዴት እንመስርት?
ሰይድ የሱፍ አሊ
27 አመት ትልቅ አገር መርታችሁና እንደፈለጋችሁ ፎልላችሁ ለስልጣን ያበቃችሁን ህዝብ የእዝጌር ውሃንኳ በወጉ ሳትሰጡት የትግራይ ህዝብ ሆይ አንተ  የምትጠቀመው ከኢትዮጵያ ስትገነጠል ነው እያላችሁ ለሌላ መከራ ስታዘጋጁት አይቀፋችሁም? ከአገር ቤት ውጭ የሠለጠነ አለም ቁጭ ብሎ ወተት በቧንቧ ቢጠይቅ ሊመጣለት በሚችልበትና በሞቀ ክፍል ተትኝቶ ስለ ትግራይ ከኢትዮጵያ መገንጠል መንደቅደቅ ቀላል ነው ።
ለተቀማጭ ሰማይ ብርቁ ነው ።በ5 ሚሊየን ህዝብና ይሄነው የሚባል የሚያኩራራ ሪሶርስ ሳይዙ ..ላንድ ሎክድ የሆነች አዲስ ሚጢጢ አገር እንመሰርታለን እያሉ መፎከር ምን ማለት ነው? ጆግራፊ የተማረና የሠለጠነ አለም ውስጥ የሚኖር ይቺን አለማወቁ የአእምሮ ችግር ይመስለኛል።
እኛ ስልጣን ላይ ከሌለን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚለው ማስፈራሪያ አጼ ሀይለስላሴም ፤ ደርግም ፤ ጃዋርም ሲለው የነበረ ተራ የህጻን ማስፈራሪያ ነው ። ከዚያ ውጡና በተጨባጭ አመክንዮ የአብይን ቀሽምነትና የፖለቲካ አቅጣጫ ተግትጉት። የድርጅታችሁ ህወሃትን በሌብነትና በዘረኝነት አሮንቃ ውስጥ የተዘፈቁትን ሽማግሌ ታጋዮች ገለል አድርጉና በአዳዲስ ወጣቶች በመተካት ታገሉና መሪነትን ቀሙ ።እንዳያችኋት ኢትዮጵያ ቢዘርፏት የማታልቅ ፤ ቢከፋፍሏት የማትወድቅ ለሚሊዮኖች ሳይሆን ለቢሊዮን ህዝብ የምትበቃ ጉደኛ አገር አገር ነች ።
  እንኳን የሌብነት አመል ኖሮባቸው ይቅርና ሰው እድሜው ሲጨምር ገንዘብ ወዳጅና ስስታምነቱ ይጨምራል ። ስለዚህ ህወሃት የመልአክት ስብስብ ነው አብይ ሊያጠቃን ፈልጎ ነው ወዘተ  ተረተረቱን ተውት ። ለነገሩ ያለ ልፋት የምትሞላቀቁበት ከዝርፊያ የሚወረወርላችሁ ስለሆነ ያ እንዳይቋረጥ ትግል ላይ ናችሁ ።
 ሌላ 60 ሺህ የትግራይ ወጣት ተቀርጥፎም ቢሆን  ሀገረ ትግራይ እንድትመሠረት ፌደራሊዝሙ ከፈረሰ…ህገመንግስቱ ምንትሶ ከሆነ እያላችሁ ዘራፍ የምትሉት የትግራይ ህዝብ በቀላሉ ይሸወዳል ብላችሁ ነው?…በደርግ ግፍ ተንገፍግፎ ለትግል ሲወጣና ደርግ ሲወድቅ ወተት በቧንቧ ቤቱ እንደሚገባለት ነበር ሰበካችሁ።ያ አይነት ሰበካ ዛሬ እንደማይሰራ አለማወቃችሁ ይገርማል ። ውጊያን በፊልምና በኮምፒዩተር ጌም የምታውቁትና በሌብነት ከበሰበሰው የህወሃት ቡድን ጋር ቅርርብ ያላችሁ አክቲቪስቶች ለሌባ ከለላ የመስጠት ጫጫታውን ተውት።
ይልቅ የአሁኑም አመራር  በተራው እንደናንተ በዘር ተቧድኖ አገር እንዳይዘርፍ ምን እናድርግ ? የወንድ ብለት የማይኮላሽባት፤ሴሰኛ ሹም ሴት እህቶቻችንን ስልጣኑን በመታከክ እንዳይደፍር ምን እንስራ? የህግ የበላይነት የሠፈነባት አገር እንዴት እንመስርት? በሚለው ሞግቱን ።
Filed in: Amharic