>

"ዶ/ር" ደብረጽዮን የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ የተረዳንበት መንገድ!!! (ዮናስ አበራ)

“ዶ/ር” ደብረጽዮን የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ የተረዳንበት መንገድ!!!
ዮናስ አበራ
-1-
ከይቅርታና ከምሕረት ጋር በተያያዘ በኢሕአዴግ ደረጃ ለጥፋተኞች ሁሉ ምሕረትና ይቅርታ መኖር እንዳለበት በመተማመን፣ እንዲሁም ለፖለቲካውም ይጠቅማል ከሚል እሳቤ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን ያስታወሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፣ አሁን አንደኛውን ፈትቶ ሌላኛውን ማሰር ግን አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡
በእኔ አረዳድ; የደጺን መግለጫ ወደ ኖርማል ቋንቋ ስንመልሰው “እነ እስክንድርን ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ፣ ዶ/ር መረራን ፣ በቀለ ገርባን ፣ እና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የተስማማነው ሌቦቹ ፣ ገራፊዎቹ እና ገዳዮቹ ምህረት እንደሚደረግልን ተስፋ በማድረግ ነበር” ማለቱ ነው ።
                                   -2-
‹‹አንዱን እየፈታህ ሌላውን አታስርም፡፡ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወንጀሎች በቁጥጥር ሥር የነበሩት በምሕረት ከተፈቱ በዚህ መልኩ ነገሩን እንያዘው ብለን ነበር፡፡ ካልሆነ ግን ከዚህ ቀደም የተፈቱትም ቢሆን ዳግም ሊታሰሩ ይገባል፤›› ሲሉ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡
በእኔ አረዳድ ፡ ወደ ኖርማል ቋንቋ ስንመልሰው ደጺ “እነ እስክንድር ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ዶ/ር መረራ ፣ በቀለ ገርባ ፣ እና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ተመልሰው እስር ቤት ይግቡ” ማለቱ ነው ። እንግዲህ ይሄ ምኞት ነው ።
                             3
የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ለመያዝ የተሄደበት መንገድን አስመልክቶም የሕግ የበላይነት መከበር እንዳለበት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸው፣ ‹‹ሜጀር ጄኔራል ክንፈን ለመያዝ ለመጡት የመከላከያ ኃይል አባላት እንደማንሰጥ አሳውቀን ነበር፡፡ ነገር ግን የሕግ የበላይነት መከበር ስላለበት የፍርድ ቤት ማዘዣውን ተመልክተን ለፌዴራል ፖሊስ አስረክበናል፤›› ብለው፣ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉበት ሒደት አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀድሞ የኢንሳ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ተክለ ብርሃን ወልደ አረጋይም አብረው ተይዘው የነበሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የወጣባቸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስላልቀረበ ለማሰርም ሆነ ለማስረከብ እንደማይቻል ምላሽ መስጠታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ሜጀር ጄኔራል ክንፈ በሰላም በቁጥጥር ሥር ውለው ሳለ በካቴና አስሮ በሚዲያ ማቅረብ ፖለቲካዊ ጥቃት ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ‹‹በመቀጠልም ተዘጋጅቶ የነበረን ዶክመንተሪ ማስተላለፍ ፖለቲካዊ ጥቃት ነው፡፡ ተጠርጣሪ የሚቀርበው ወደ ፍርድ ቤት እንጂ ወደ ሚዲያ አይደለም፡፡ በዚህም የሕግ የበላይነት ተበርዟል፡፡ ወደ አንድ ግለሰብ ሳይሆን ወደ ብሔርና ድርጅት ያነጣጠረ መሆኑ አደባባይ ወጥቷል፤›› ሲሉ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፡፡
በእኔ አረዳድ ፡ ከሁሉም ንግግራቸው ይሄኛው ብዙ ያስቃል ፥ ይገርማልም ። ምን ታስረክባለህ በጠረፍ በኩል ሊያመልጥ ሲል አይደል እንዴ ጋማውን ተብሎ የመጣው ?! ቀጣፊ !! ደጺ ላነሳቸው ነጥቦች መልስ ለመስጠት እነሱ ለአመታት ከሰሩት ውስጥ ጥቂት ብንቆነጥር ይበቃል ። እርሱና ግብርአበሮቹ ውስታዝ አቡበከርን በካቴና አስረው ETV ላይ ሲያቀርቡት አልነበር ወይ ? ለዚያውም ያልሰሩትን “በጋዜጠኛ” እያናዘዙ ነዋ !! ዶ/ር መረራ ጉዲናን የፊጢኝ ወደኋላ በካቴና አስረን ያሳየነው እኛ ነን ወይ?  “ኢስላማዊ ሃረካት“ የሚል ከእውነታ እጅግ የራቀ ፥ ያበጠ እና የበሰበሰ አስክሬን ሳይቀር የሚታይበት አሰቃቂ ”ዶክመንታሪ“ አዘጋጅቶ በ ETV ላይ ዜጎችን እያሳቀቀ ያሳይ የነበረው ወያኔ እንጂ ሆሊዉድ ነበረ ወይ ?!!
                                 -4-
‹‹የትግራይ ክልል ለሕግ የበላይነት ይሠራል፡፡ የፌዴራል መንግሥት ግን የሕግ የበላይነትን ጥሶ እየሄደ ስለሆነ እየተወሰደ ያለው ዕርምጃ በማንኛውም መንገድ ተቀባይነት የለውም፤›› ብለዋል፡፡
የሕግ የበላይነት ጥሰትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ዕርምጃው የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ያለበት በመሆኑ ፖለቲካዊ አንድምታው እየሰፋ መጥቷል ብለዋል፡፡
በእኔ አረዳድ : ደጺ ዛሬም ድሮ ጀምሮ ወያኔ በተደጋጋሚ እየጣለ የተበላውን የጅል ካርዳቸውን ይወረውራል ። በወያኔ ፖለቲካ የማይታይ ፥ ስሙ የማይጠራ አንድ በደፈናው “የውጭ ሃይል” የሚባል PHANTOM ጠላት SOMEWHERE ሁሌ አለ !! ባጠቃላይ ከዚህ በላይ የፖለቲካ ቆሞቀርነት በዓለም ታሪክስ ታይቶ ያውቅ ይሆን ? እንግዲህ ይሄ ሁሉ ያዙኝ ልቀቁኝ ቆለጥና ጡት በጉጠት ሲጎትቱ የነበሩና ቢሊዮኖች ብር የዘረፉ ጥቂት ወያኔዎች ስለታሰሩ ነው አይደል? ገና ምኑ ተነካና ?!!
ኢትዮጵያ ትቅደም !!
ወያኔ ይውደም !!
Filed in: Amharic