>

የቀረው ይቅር እንጅ. .. (ሞሀመድ አሊ መሀመድ)

የቀረው ይቅር እንጅ. ..
ሞሀመድ አሊ መሀመድ
– የሀገሬ አንጡራ ሀብት በጠራራ ፀሐይ ተዘርፎ; … ያለምንም ይሉኝታ …. ዘርማንዘሩን እየሰበሰበ ሲቀራመተውና; …. ከዚያም አልፎ ወደ ዶላርና ዩሮ እየቀየረ ወደ ባህር ማዶ ሲያሻግረው ኖሮ; …. አብዛኛው ከእጅ ወደ አፍ እንኳ የሚሆን ነገር ቸግሮት. .. እሱ ግን ባማሩ ህንፃዎችና እጅግ በውድ ዋጋ በሚገዙ መኪኖች ሲንፈላሰስ … የበይ ተመልካች ሆኖ ሲያዬው የነበረ ህዝብ . ..  ወገን ያረረ ሽሮና ንፁህ ውሀ አጥቶ ፈጣሪውን ሲያማርር … እነሱ ጮማ እየቆረጡ በውስኪ ሲራጩ . .. ይሉኝታ ቢሶች አይደሉም እንዴ? … ጥረው ግረው በላባቸው ያፈሩት ሀብትና ንብረት ቢሆን ኖሮ ምን ገድዶን? … ግን ዘርፈው ነው።. .. እንዳንናገር ጠመንጃ ደግነውብን ዐይናችን እያዬ ነው የሀገርና የህዝብ ሀብት የዘረፉት. .. አሁን ምን መጣና ነው … እንዳሻቸው ሲጨፍሩባት የነበረችውን “አዱገነትን” ትተው. .. መቀሌ ሄደው የመሸጉት? … እንዴ መቀሌ ኢትዮጵያ አይደለም እንዴ? … ወይስ “የቅማል ስደት; ከራስ ወርዶ አንገት” እንዲሉ መሆኑ ነው? … ግን ግን … እንዴት ነው ምድረ ዘራፊና ወንጀለኛ እዚያ እየሄደ የሚደበቀው? … የትግራይ ህዝብስ በምን ዕዳው ነው? … “አይጥ በበላ; ዳዋው ተመታ” እንዲሉኮ ነው።
– በንፁሃን ዜጎች … በወገን ላይ. .. እግዜር ይቅር የማይለው. .. ያ ሁሉ ግፍና በደል ሲፈፀም. .. የትግራይ አክቲቪስት ነኝ የሚለው ሁሉ የት ነበር? … አብሮና ተባብሮ. .. “በለው” ሲል አልነበረም እንዴ? … የዚያ ሁሉ ግፍና ስቃይ. .. የዚያ ሁሉ አረመኔያዊ ድርጊት. .. መሪና ፊታውራሪ. .. ማን ነበር? … ለመጠየቅማ ሁሉም ይጠየቃል? … የናንተ ግን ይለያል? … animal farmን ስታነበንቡ አልነበረም እንዴ? … ወይስ ዛሬ የሸመደዳችሁት ካፋችሁ ላይ ቡን ብሎ ጠፋ…
– ዛሬ ነው እንዴ ግን እኩልነቱ የታያችሁ? … አዎ ለመጠዬቁ ጊዜ. .. ሁሉም እኩል ተጠያቂ መሆን አለበት አይደል? … ሀገር በጠራራ ፀሐይ ስትዘርፉ ግን. .. ኑ አብረን እንዝረፍ ብላችሁ ነበር እንዴ? … ያን ሁሉ መከራና ግፍ ስትፈፅሙ. .. ህመሙን ቀምሳችሁት ነበር እንዴ? … ቢያንስ እንደ ሰው ርህራሄ ነበራችሁ? … ዛሬ ስለህግ የበላይነት ስታወሩ ትናንትን አታስታውሱም እንዴ? … ቢሆንም የህግ የበላይነት መከበር አለበት… እናንተም በህግ ፊት መቅረብ አለባችሁ።. .. ቢያንስ አሁን እንኳ ስለፍትህ ማሰብ አለባችሁ።. .. ስለፍትህ ከሆነ እኛም አብረናችሁ እንቆማለን!!!
– በህግ የበላይነትና ፍትህ መደራደር የለም። የምን ሰበብ ማብዛት ነው? ፍትህ በሌለበት ሰላም አይኖርም። ሰላምን በጦርነት ማምጣት አይቻልም። የጦርነት አታሞ በመጎሸም. .. ከህግና ፍትህ ለማምለጥ መሞከር ራስን መሸወድ ነው። በዚህ መንገድ ሌላውን እንዴት መሸወድ ይቻላል? … ወይስ ጦርነት ፈርተን እንድንተወው? … እኛ እንተወው ብንልስ. .. ፈጣሪ ይቅር ይላል?
– ለህግና ፍትህማ መቅረብ ግድ ነው! … የቀረው ይቅር እንጅ. .. በዚህማ ድርድር አይኖርም!
Filed in: Amharic