>

የአቢይ የረጅም ጊዜ እቅድ ኢትዮጵያዊነት ላይ መስራት እንደሆነ ያመላከተው የዳኛዋ ሹመት!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

የአቢይ የረጅም ጊዜ እቅድ ኢትዮጵያዊነት ላይ መስራት እንደሆነ ያመላከተው የዳኛዋ ሹመት!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ላለፉት 27 አመታት ወያኔ አሻንጉሊቶቿን ዘፍዝፋበት የህዝብ ድምፅ ስትቀሽብበት የኖረችውን ምርጫ ቦርድ  ለብርቱካን ሚደቅሳ መሰጠቱ ሲረጋገጥ የእነ ጃwarና ኦነግ ካምፕ  እየተንጫጫ ነው።
” ለምን እኛን አላማከሩንም? ” የሚል አስቂኝ አስተያየትም እየሰማን ነው።
እነሱ ታከለ ኡማ የሚባል  አምጥተው የአዲስ አበባ ከንቲባ አድርገው ሲሾሙ መንግስት እኛን አማክሮን ነበር ወይ?
የጃዋር አላማና ታክቲክ ግልፅ ነው ኦሮሚያ ላይ የአቢይን ኦዴፓን  ጃዋር ከኋላ ሆኖ እንደ ጆተኒ በሚጫወትበት በበቀለ ገሪባ  ጠራርጎ ካሸነፈ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ከአቢይ መውሰድ ኢትዮጵያ በማያቋርጥ የግጭት ማእበል ማናወጥ ነው። ይሄን እቅድ ለመፈፀም በነፃ የምርጫ ሜዳ ማሸነፍ ስለማይችሉ ለጃዋር የሚታዘዝ አሻንጉሊት ምርጫ ቦርድን እንድቆጣጠር ይፈልጋሉ።
በመሰረቱ እኔ  የክቡር አቶ ሚዴቅሳ ልጅ  ብርቱካን  መጣች  ሎሚ ሄደች የሚለው ዜና ባይሞቀኝም ባይበርደኝም የእነዚህን ሰዎች የልብ ውፋሬ ፣ከይሉኝታ መሰናበትና የሃፍረትን የመጨረሻ ድንበር መጣስ ሁሌም ይገርመኛል።
በመሰረቱ በአንድ አገር የመንግስት ስልጣን ውስጥ ስትራቴጂክ የስልጣን ቦታዎችና የሰርቪስ ቦታዎች የሚባሉ  አሉ ።
ስትራቴጂክ የሚባሉት የስልጣን ቦታዎች ~ ውጭ ጉዳይ ፣ ደህንነት ፣ፖሊስ ፣መከላከያና ኢኮኖሚ የመሳሰሉት  የስልጣን ቦታዎች ሲሆኑ እነዚህን ከሞላ ጎደል ኦሮሞዎች ተቆጣጥረዋል። እነዚህን ስትራቴጂክ ስልጣኖች የያዘ የአገሪቱን ፖለቲካ ይወስናል።
..
በሌላ በኩል ሰርቪስ ሴክተር ~ የሚባሉት ትምህርት ሚ/ር ፣ትራንስፖርት ሚ/ር ፣ ጤና ሚኒስቴር የመሳሰሉት ናቸው ።እነዚህ ቦታዎች ልክ ካፌ ወይም ሱቅ ከፍታችሁ ለደንበኛ አገልግሎት እንደምትሰጡት ሁሉ መንግስት ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቦታዎች ስለሆኑ ከፖለቲካ አንፃር ሲታዩ እዚህ ግባ የማይባሉ ቦታዎች ናቸው። እነዚህን ሰርቪስ ሴክተሮች ማን እንደተቆጣጠራቸው ብአዴን አዴፓን መጠየቅ ነው።
አሁን በአቢይ አህመድ Long run strategy  ላይ የመሰለኝን ልበል ።እርግጥ የኖቤል ተሸላሚውና  አለም አቀፉ ኢኮኖሚስት Keynes አባባል << In the long run we all are  dead >>  ( በLong run ሁላችንም ተለቃቅመን ሟቾች ስለሆንን)
“በLong run አቢይ ስትራቴጂ ” በማለት መተንተን ስሞክር ዊርድ ነገር እንዳይሆንባችሁ።
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ  የብሄርተኛ ፓርቲ የሆነው የኦዴፓና የኢህአዴግ ሊቀመንበር ቢሆንም ውስጡ ግን ወደ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት  ሲንሸራተትበት ብዙ ጊዜ ማስተዋል ይቻላል ። በተለይ በኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች ዘንድ ጠ/ሚ  አቢይን በጥርጣሬ የሚመለከቱት ይሄን የተደበቀ ኢትዮጵያዊነት ብሄርተኝነት አለው ብለው ስለሚሰጉ ነው።
 ከሰሞኑ የአቢይ ስልጣን አሰጣጥ ሂደት ስንመለከት  “ብሄር አደለንም ኢትዮጵያዊ ነን ” የሚሉትን ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ፣ መአዛ አሸናፊ ፣ ብርቱካን ሚደቅሳና  ለሰብአዊ መብት የታጨውን አቶ ዳንኤልን ማቅረቡ የአቢይ የረጅም ጊዜ እቅድ ኢትዮጵያዊነት ላይ መስራት እንደሆነ መገመት ይቻላል።
Filed in: Amharic