>

‹‹ ብርቱካን እንደዓርማ!››  (በፍቃዱ ሞረዳ)

‹‹ ብርቱካን እንደዓርማ!›› 
በፍቃዱ ሞረዳ
እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር 1992 በነበረዉ ምርጫ ላይ ወረዳ 12 እና 13ን በመወከል የፓርላማ ተወዳዳሪ ነበረች፡፡ አይሱዙ መኪና ተከራይታ ‹‹ ጭራን ምረጡ!›› እያለች ስትቀሰቅሰን ነበር፡፡በሻለቃ አድማሴ ቦታ ይመስለኛል የተወዳደረችዉ፡፡ የምርጫ ምልክቷ ጭራ ነበር፡፡ እልኋ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
አንድ ቀን በተፈራ ዋልዋ ሥልጣን ዘመን የአዲስ አበባ መስተዳድር የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ ይሰራ ከነበረዉ ከአቶ ሚሊዮን አሰፋ ( ጠበቃዉ ሚሊዮን አሰፋ አይደለም) ጋር ጋዜጣችን ቢሮ መጣች፡፡ በንግግራችን መሐከል ‹‹ድንገት ሳላስበዉ›› አንድ ነገር ከአፌ ወጣ፡፡ ከእርሷም አፍ አንድ ነገር ወጣ፡፡ ታስቦበት፡፡ አቋሟ ስለሆነ ግድ አልነበረኝም፡፡ ያንን ነገር አሁን ለመተረክ ጊዜዉ አይመስለኝም፡፡ አንድም አልፎበታል፤ ወይም ገና ነዉ፡፡
እነስዬ በእርሷ ችሎት ይዳኙ በነበረበት ጊዜ ከችሎቷ ሥር አልጠፋም ነበር፡፡ በቅንጅት ጊዜም …እምም…
ስደት ከገባሁ በኋላ በነበረዉ ዓለም አቀፍ የ‹‹ ብርቱካን ትፈታ›› ዘመቻ ላይ ፣ ‹‹ ብርቱካን እንደዓርማ›› የሚል ረጅም ግጥም አፅፋኛለች፡፡በሚቀጥለዉ ዓመት ይታተማል፡፡ አሁን ዛሬ ተሾመች አሉ፡፡በተመራጭነት ሳይሆን በአስመራጭነት፡፡ አዘንኩላት፡፡ ፅናቱን ይስጥሽ!
Filed in: Amharic