>

ድምጻዊት ማርታ ሀይሉ አረፈች!! (ዳንኤል ገዛህኝ)

ድምጻዊት ማርታ ሀይሉ አረፈች!!
ዳንኤል ገዛህኝ
ለረጅም አመታት ነዋሪነትዋን በእንግሊዝ ሀገር ያደረገችው ድምጻዊት ማርታ ሀይሉ ትላንት ሌሊት ተኝታ ህክምና ትከታተልበት በነበረው ሆስፒታል ውስጥ በሀገረ-ሎንዶን ህይወትዋ ማለፉ ተሰምቶዋል::
ድምጻዊት ማርታ ሀይሉ ለወራቶች በካንሰር ህመም ምክንያት ጥብቅ የህክምና ክትትል ብታደርግም መትረፍ አልቻለችም::
ከረሜላ…አብ አስመራ…ዝማምዬ በሚሉት እና በሌሎችም ዜማዎችዋ በተለይም በ1980ዎቹ በለገሀር ሙዚቃ ቤት አሳታሚነት በሰራችው አልበምዋ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፋ ቆይታለች:: በሌላ በኩል ከድምጻዊ ደረጀ ደገፋው ጋር በሰራችው አልበም በቅብብል የሚያቀነቅኑት ላሉማዬ የተሰኘው ዘፈን ማርታ የምታወቅበት እና ተወዳጅ ስራ ነው:: ድምጻዊት ማርታ ሀይሉ ከጥቂት አመታት በፊት አለማዊ ሙዚቃ በማቆም ሙሉ ለሙሉ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ያሬዳዊ ዜማዎችን በማዜም ቤተክርስትያንን በእንግሊዝ ሎንደን ስታገልግል ቆይታለች:: በተለይ በእንግሊዝ ሎንደን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጋር አባል በሆነችበት ማህበር ሎለንደኑ ደብረ ምህረት ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል ማቁዋቁዋሚያ ገቢ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የመዝሙር ኮንሰርት መርሀ-ግብር ላይ አባል በመሆን በዝማሬ የበኩልዋን አስተዋጽኦ አድርጋለች:: ድምጻዊት ማርታ ሀይሉ ከተለያዩ ድምጻዊያን ጋር ተግባብታ በመስራት የምትታወቅ ጸባየ መልካም የተመሰገነች ድምጻዊት ስትሆን በሙያ ባልደረቦችዋ ዘንድም ተወዳጅ ነበረች::
ለቤተሰቤችዋ ለወዳጆችዋ እና ለሙያ ባልደረቦችዋ መጽናናት ይሁን::
Filed in: Amharic