>

"ከአማራዎች ይልቅ ሱዳኖች ይሻሉናል!!!"   ዶ/ር ደብረ ጺዮን (ትርጉም ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ)

“ከአማራዎች ይልቅ ሱዳኖች ይሻሉናል!!!” 
 ዶ/ር ደብረ ጺዮን
ቀጥተኛ ትርጉም ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ
በፍርሀትና ተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ የተደረገ ንግግር!!
ትላንት ሮብ ህዳር 12/2011 ዓ.ም ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን በተላለፈ የትግርኛ ፕሮግራም አማካኝነት ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ተስፋ መቁረጥና ፍርሀት የተንጸባረቀበት ንግግር ሲያደርግ ሰማሁት፡፡
ንግግሩን ያደረገው የምዕራብ ትግራይ ዞን ባዘጋጀው የአባላትና ደጋፊዎች ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ ነው፡፡ በዚህ ንግግሩ ውስጥ ካስተላለፋቸው በርካታ መልዕክቶች መካከል በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
• የእብደት አስተሳሰብ የያዙ ሰዎችና መሪዎች የሚፈጥሩት ችግር ነው (ከ30 ጊዜ በላይ ብሎታል)፣ ከአማሮች ይልቅ ሱዳኖች ተሸለውናል፣ ምክንያቱም ቀደም ሲል በትግሉ ወቅትም ሆነ አሁን የእኛን ችግር ተረድተው ተፈናቃዮቻችንን ተንከባክበው ነው የያዙልንና ልናመሰግናቸው ይገባል፣
• ይኸ የእብደት አስተሳሰብ የፌዴራሉን መንግስት መሪዎች ጨምሮ በሁሉም ደረጃዎች በግልጽ እየተንጸባረቀ ነው፣ አንዳንዶቹን ደጋግመን የማረክናቸው ናቸውና ያውቁናል፣
• እነዚህ በየሜዳው የሚፎክሩ ሰዎች ወደ ክልላችን ቢገቡ ኖሮ እናሳያቸው ነበር፣ ከፈለግን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ልክ እናስገባቸዋለን (በሳቅ ታጅቦ ጊዜውን አስረዘምሁት እንዴ)!
• የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የሚባሉት አጭበርባሪዎች ናቸው፣ የግዛት ማስፋፋት ህልማቸውን በተዛዋሪ መንገድ ለማሳካት በማንነት ስም የሚነግዱ እንደሆኑ መታወቅ አለበት፣
• ይኸ ሁሉ ስራ የሚሰራው ትግራይን ከበባ ውስጥ በማስገባት አንገቷን ለማነቅና የትግራይን ህዝብና አመራር ለማንበርከክ ታስቦ የተደረገ ነው፣
• ህገ መንግስት ይከበር ስላልንና ከሚገባው በላይ ስለታገስናቸው እንጂ እንደነሱማ ቢሆን ጦርነት ውስጥ ያስገቡን ነበር፣ ሆኖም መታገሳችንና ደጋግመን መምከራችን ተገቢ ነው፣
• ይህም ሆኖ ያን ያህል የሚያስፈራ ነገር ስለሌለ እንቅልፍ አልባ ሆነን ማደር የለብንም፣ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ግን ተገቢ ዝግጅት ማድረግ ይኖርብናል፣ እንቅልፍ ማጣት ያለባቸው እነሱ እንጂ እኛ መሆን የለብንም፣
• የመገናኛ ብዙሀኑም ቢሆኑ ካበደው ጋር ነው የሚያብዱት፣ የአመራሩን ስሜትና ፍላጎት እያዩ ይዘግባሉ፣ በዚህም ህግን ይጥሳሉ፣ የሞራል ድጋፍ የሌላቸውን ዘገባዎች ያስተላለፋሉ፣
• ሰብአዊ መብት የጣሱና በሙስና ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎችን የመያዙ እርምጃ በሁሉም ላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፣ የተወሰኑትን ብቻ ይዞ ከቆመ ግን ችግር አለ ማለት ነው፣
• ጀነራል ክንፈ ዳኘውን በካቴና አስሮ በግልጽ በሚዲያ ማቅረብ ሆን ተብሎ የተደረገና ትግራዮችን ለማናደድ ስለተፈለገ ነው 
(በዶ/ር መራራ ጉዲና፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፣ እጅ ላይ ካቴና ባስገቡ ጊዜስ ማንን ለማናደድ ተፈልጎ ነበር የሚለውን ቢያስታውሱ መልካም ነበር)፣
• በአጠቃላይ ይኸ ሁሉ ፍከራና ጭፍራ የትግራይን መሬት ለመቀራመት ስለተፈለገ ብቻ በዚህም በዚያም ሊያዋክቡን ይሞክራሉ
(የተገላቢጦሽ ነው የሚባለው፣ ተገምጡልኒ)፣
Filed in: Amharic