>

አሁን ላይ ያሉ አደጋዎች (ሚኪ አምሀራ)

አሁን ላይ ያሉ አደጋዎች
ሚኪ አምሀራ
በሰሜን ወልቃይትና እና ራይን ወሮ የያዘዉ ትህነግ ህዝባችን እየገደለ እያሰቃየ ይገኛል፡፡ ይሄን ጥያቄ አጠናክረን ስለገፋን እና ጫፍ ላይ ስላደረሰነዉ ትህነግ እኛን ለመከፋፈል እና የአላማ አንድነት እንዳይኖረን እየሰራ ያገኛል፡፡ የኦሮሞ ኢሊቶች የአማራ ፖለቲካ እየጠነከረ መምጣቱ እነሱ ላሰቡት ነገር አመቺ ስላልሆነ ጉድጓድ እየቆፈሩለን ይገኛሉ፡፡ ሁለቱ ጥንፈኞች ሚዲያወቻቸዉ በጠቅላላ አማራ ላይ እንዲያተኩር እንዲያዉም በክልሉ ዉስጥ ያልተከበሩ ንኡስ ማንነቶች አሉ በማለት  የአየር ላይ ጊዜ በማዘጋጀት ላይ ናቸዉ፡፡እስከማዉቀዉ ድረስ ግን ማንነቱ ያልተከበረለት ያለ አይመስለኝም፡፡ ትግራይ ሚዲያ ሃዉስ የሚባለዉ አሁን በወያኔ እየተቋቋመ ያለዉ ዝርዝር አላማዉን አይቸዋለዉ ሙሉ ለሙሉ እኛ ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡ የትግርኛ ፕሮገራመ እራሱ አይኖረዉም፡፡
የኦሮሞ ሊሂቆች/ብሄርተኞች አላማቸዉ እንዲሳካ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ የተሸከመዉን ቡድን ማፍረስ መፍትሄ ነዉ ብለዉ ያስባሉ፡፡ የአማራን የፖለቲካ ስነልቦና ያራምዳል ያሉትን ደቡብን መበታተን ችለዋል፡፡ ደቡብ እንደ ክልል አማረኛን የሚጠቀም እና በኢትዮጵያ ላይ የማይደራደር ነበር፡፡ እነ ኦኤም ኤን ለሶስት አመት ባደረጉት ስራ ሲዳማን ክልል እንዲሆን አስችለዋል፡፡ ሌሎችም ይቀጥላሉ፡፡ የአማራ ብሄርተኝነትን እየደገፉ የአንድነቱን ጎራ ይመቱ ነበር አንድ ሰሞን፡፡ ያኔ የአንድነቱ ጎራ ጠንካራ ነዉ ብለዉ ስላሰቡ ነዉ፡፡ የአንድነቱን ጎራም አጥፍተዉታል ማለት ይቻላል (የራሱ የገነገነ ድክመት ጋር ተጨምሮ)፡፡ አሁን ወደ አማራ ብሄርተኝነት ዙረዋል፡፡ እኛንም ለማፍረስ ማለት ነዉ፡፡አሁን ደግሞ ከላይ እና ከታች የታሰበዉ አማራን እንደ ደቡብ መሸንሸን ነዉ፡፡አዲስ አበባ እና ፌደራል ላይ የአማራን ህዝብ በወርዱ እና በአቋሙ የመወከል እና ፖለቲካን የመጫወት እንዲሁም ሀገሪቱን አዲስ ሀገመንግስት ቀርጾ የመገንባት ሃላፊነት አለ፡፡
ይህ ፈታኝ አጀንዳ እያለብን ጥይትን የማባከን ያህል እከሌ እንዲህ ነዉ እንዲያ ነዉ ምናምን ሲሉ መዋል ያበሳጫል፡፡
 
ለ አ.ዴ.ፓ
አ.ዴ.ፓን መቀጥቀጥ ባለበት ሰአት ቀጥቅጠነዋል፡፡ ጸረ አማራን እንዲያባር አድርገናል (ከሞላ ጎደል)፤ አልፎ አልፎ የምንፈልጋቸዉን ሰወች ተቀብሏል (እነ አሳምነዉ ጽጌ፤ እነ አህመድ፤ ዶ/ር ስዩም እሁን ደግሞ እነ ዘመነ ካሴ፤ ከአዴሃን ደግሞ እንዲሁ)፤ ከሞላ ጎደል እኛ ስናራግብ የነበረዉን አጀንዳ አስገድደን እንዲቀበል አድርገናል፡፡ ይሄም ሆኖ ድርጅቱ በምንፈልገዉ ፍጥነት እየሄደ አይደለም፡፡ ነገር ግን አሁን መቀጥቀጥ ሳይሆን Push ማድረግ አቅጣጫ ማሳየት እና የአማራን ህዝብ በሚገባ ወክሎ በሃገር ደረጃ መጫወት ያለበትን ሚና እንዲጫወት ገንቢ አስተያየት መስጠት፤ ሲያጠፋ ደግሞ መቆጣት ነዉ፡፡ ሪፎርሙን በፍጥነት ወደ ወረዳወች እና ክልሎች እንዲያደርስ መገፋፋት ነዉ፡፡ከዛ ዉጭ እከሌ እዚህ ጎጥ ስለሆነ እከሌን እንዲህ አደረግዉ እከሌ እዛ ጎጥ ስለሆነ እያላችሁ የምትጽፉ ሰወች አዴፓን ከፋፈለን ብላችሁ ስንሰራበት የኖርነዉን ህዝባችን እየከፋፈላችሁ እና ከላይ  አደጋ ብየ ላስቀመጥኳቸዉ ሰወች ጥሩ መንገድ እየከፈታችሁ መሆኑን እወቁ፡፡ ይሄን የጎጥ ነገር እዛዉ አዴፓ ዉስጥ እንዲራገብ የሚፈልጉ ሰወችም አሉ፡፡ ጉዳቸዉን በጎጥ ለማስታከክ የሚሞክሩ፡፡ ይሄን እኛ ከፍተን መስጠት የለብንም፡፡ አንዳንድ ሰወች ከአዴፓ መረጃ እንገኛለን ብላችሁ የምታወጡትን ነገር ከመለጠፋችሁ በፊት ለአማራ ህዝብ ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል ብላችሁ ፊልተር ማድረግ አለባችሁ፡፡ እንደወረደ እና ከፋፋይ በሆነ መንገድ ማስተላለፍ ህዝበቻን ይጎዳል፡፡እራሳችን ለመከላከል ሚዲያ እንኳን ሳንይዝ የምናደርገዉን ነገር በጥንቃቄ ማየት አለብን፡፡
 
የክልሉ አመራሮች የአሜሪካ ጉብኝት
—–
የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ፤ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀ አና የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር አምባቸዉ ወደ አሜሪካ ተጉዘዉ የአማራን ተወላጆችን ያገኛሉ፡፡ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነዉ፡፡ ለረዥም ጊዜ በህዝባችን ጉዳይ ላይ እንዳይመክር ወያኔ እና ኢምባሲዎቹ ጥለዉት የቆየዉን እቀባ ይገፋል፡፡ በመሆኑም እነ አቶ ገዱን በሚገባ ተቀብላችሁ በፖለቲካዉ በተለይ በኢንቨስትመንት ዙሪያ በደንብ መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም የአማራ ተወላጅ ስብሰባወች ላይ ተገኝነቶ ዉይይት ማድረግ አለበት፡፡
ስለ ናማ
——
ናማ ባይኖር የኢትዮጵያ ፖለቲካ boring ይሆን ነበር፡፡ ይሄ ፓርቲ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እስከ ኤርትራ ድርስ አረ አልፎ እስከ ብራሰልስ ድረስ አነቃቅቷል፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ፓርቲዎች ይሄን ፓርቲ ሊያመሰግኑት ይገባል፡፡ አስፈላጊዉን ጫና በመንግስት ላይ እያደረገ ያለዉ ይህ ፓርቲ ነዉ፡፡ ህዝቡን አነቃቅቶት ያለዉ ይህ ፓርቲ ነዉ፡፡ እጅግ በጣም ደስ የሚል ስራ እየሰሩ ነዉ፡፡ ፓርቲዉ ተራማጅ ነዉ፡፡ ለአማራ ህዝብ ከሚሰራ ሰዉም ሆነ ድርጅት ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ ቤንሻንጉል ክልል የአዴፓ ተወካይ እና የናማ ተዋካይ በአንድ ቢሮ ዉስጥ ሲሰሩ ማየት ያስደስታል፡፡ ቀጣይ አቅጣጫዉ ፖሊሲ እና ስትራቴጅን በመቅረጽ በሃገሪቱ የፖለቲካ debate እንዲጀመር ማድረግ አለበት፡፡ ያዉ ሌላ ፓርቲ ይሄን የሚያደርግ ስለሌለ ከናማ ነዉ የሚጠበቀዉ፡፡
Filed in: Amharic