>

የነበረከት ስምን  እና ታደሰ ካሳገመና ሲጋለጥ!!! (ይርጉ ፈንታ)

የነበረከት ስምን  እና ታደሰ ካሳገመና ሲጋለጥ!!!
ይርጉ ፈንታ
የድርጅቱ ትርፍና ንብረት በእንግሊዝ አገር በነ አቶ ታደሰ ካሳ ጥንቅሹና በረከት ስምኦን ወይም በእንግሊዞች አጠራር የኢትዮጵያ የንጉስ ቤተሰቦች ንብረት በሚባለው እነ ገነት ፈንቴ(የበረከት ሚስት የአሰፉ ፈንቴ እህት ወይም የታደሰ ጥንቅሹ ሚስት የነጻነት አበራ የአክስት ልጅ)ና የገነት ፈንቴ ባል አቶ መሰረት ተስፉ(በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ማሰተርስ እያለው ከህግ ዉጭ ሌላ ማስተርስ እንዲማር በበረከት አስገዳጅነት ወደ እንግሊዝ አገር ንብረቱን እንዲያስተዳድር የተላከና በዚያው እንደከዳ ተደርጎ ተመቻችቶለት የቀረ) ይህንን ሃብት በማስተዳደር ይገኛሉ፡፡
ለመሆኑ የድርጅቱን ሃብት እንዴት ወደ እንግሊዝ አገር ወዳለው ድርጅቶቻቸው ያዞሩታል የሚለውን ከዚህ በታች በዝርዝር እናየዋለን፡፡
አለ የምንለው ጥረት ግን የለሌው ገመና ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡
1.ዳሸን  ቢራ የማነው?
ዳሸን ቢራ ብዞቻችን የጥረት ይመስለናል ነገር ግን በነአቶ ታደሰ ካሳ ጥንቅሹና በረከት ስምኦን ዱየት ለተባለ ለእንግሊዝ ድርጅት ተሽጧል፡፡56 ፐርሰንት ድረሻው በዚህ ድርጅት ስም ተመዝግቦ ሲገኝ፤ቀሪው ገንዘብ በብድር መልክ ለጥረት እንደተሰጠ ተደርጎ ዳሸን ሙሉ ለሙሉ ለዱየት ተላልፏል፡፡የሚገርመው መሸጡ ሳይሆን የተሸጠበት ገንዘብ በእንግሊዝ አገር በነካሳ ቤተሰብ ወደሚተዳደር ድርጅት አካውን ገብቶ ቀርቷል፡፡
2. እውን የጥረት መኪኖች 500 ናቸው?
አቶ በረከት ከ500 መኪና በላይ በድርጅቱ ይገኛል ብሎ በአደባባይ የዋሸን ጉድ በጥቁር አባይ ትራንስፖርት የሚተዳደሩ 37 መኪኖች ብቻ በስራ ላይ ያሉና 133 ከጥቅም ዉጭ የሆኑ ናቸው፡፡በከርቻ ላይም 13 መኪኖች ብቻ ናቸው ያሉት፡፡እንግዲህ በድምሩ በ27 አመት ዉስጥ 50 መኪኖች ብቻ ነው ያሉት ሌላው መኪና በኪራይ እየገባ የሚሰራበት እንጅ የጥረት ንብረት አይደለም፡፡ታድያ አቶ በረከት 500 ያሉን አንድ ዜሮ መጨመር ችግር የለውም ብለው ይሆን?
 
3. በወር ሁለት ጊዜ ደሞዝተኞቹ
በድርጅቱ የተቀጠረው ሰው በሙሉ ቤተሰብ ስለሆነ በደምወዝና ጥቅማጥቅም ምክንያት ወደራሳቸው አዙረውታል፡፡
ለምሳሌ የቀን አበል በቀን 22,000 ሃያ ሁለት ሽህ ለአንድ ሰው ይሰጣል(ቀልድ ይመስላል አይደል?) በሁለት ፔሮል አንዱ እንደ ዉጭ አገር ዜጋ የነበረከት ቤተሰቦች በዶላር በፈረጅ አቆጣጠርና በኢትዮጵያ አቆጣጠር አንድ ሰራተኛ በወር ሁለት ግዜ ደምወዝ ይወስዳል፡፡
4.እንደዋዛ ወደ አካውንታቸው የተወረወሯት  11 ሚሊዮን
ደሴ ዉሃ ለማምረት ተብሎ ከደሴ ከተማ በ10 ኪ.ሜ በምትርቅ በደዶ በተባለች የገጠር ከተማ 9 ሚሊዮን የተገመተን ፋብሪካ 20 ሚሊዮን በማድረግ 11 ሚሊዮኑ ወደነ በረከት አካውንት በእንግሊዝ አገር እንዲገባ ተደርጓል፡፡
5. ሌላ  50 ሚሊዮን ዶላር
ጁቨንቲስ የተባለ የእንግሊዝ ድርጅት አብሬ እሰራለሁ ብሎ እንዲመጣ በማድረግ ያለምንም መያዣና ምንም ስራ ሳይጀምር፤ በኢትዮጵያም በንግድ ሳይመዘገብ 50 ሚሊዮን ዶላር ወይም 150 ቢልዮን ብር ወደነ ታደሰ አካውንት ከድርጅቱ ወጥቶ ገቢ ተደርጓል፡፡
6.  ኮሚሽን እንዲበላና እንዲያበላ የተጠራው ድርጅት 
በጌዳ ዲተርጀንት ተብሎ የሚጠራው ድርጅት የነታደሰ ቤተሰብ በጋራ እሰራለሁ ብሎ ያለምንም መያዣ 90 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ ተሰጥቶት ኮሚሽኑን ወስዶ ቀሪውን ወደነ ታደሰ አካውንት ገቢ አድርጎታል፡፡
7. ሌላው ኮሚሽን በሊታ የነበረከት ፌክ ካምፓኒ
የትመን ጅብሰም የተባለ ድርጅት በተመሳሳይ የነታደሰ ቤተሰብ በጋራ እሰራለሁ ብሎ ያለምንም መያዣ 90 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎ ተሰጥቶት ኮሚሽኑን ወስዶ ቀሪውን ወደነ ታደሰ አካውንት ገቢ አድርጎታል፡፡
8. ባህርዳር ላይ የ3ሚሊዮን ግምት ያለው መሬት 40 ሚልዮን እንዲገዛ የማድረግ አሻጥር
 መሬት ለዶክተር በቀለ ለልብ ሆስፒታል መገንቢያ እንዲሆነው በማለት በነጻ ከሰጡ በኋላ በ3ሚሊዮን የተገመተውን መሬት 40 ሚሊዮን እንዲገዛ በማድረግ ዶክተሩ ለራሱ የሚገባውን ወስዶ ቀሪውን ለነ በረከት ገቢ አድርጓል፡፡ ቦታውም በአማራ ለልብ ህመም ለሚሰቃዩ ሆስፒታል ይሰራበታል የተባለውን ቦታ ለመቸርቸሪያ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡
9. ለሆስፒታል የተዋጣ ገንዘብ ወደ እንግሊዝ 
 በደሴ ከተማ ሊገነባ የነበረውን የወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታደሰ ጥንቅሹ ከኅዝብ የተዋጣውን ገንዘብ እንዲሁም ከጥረት ለሆስፒታሉ ማሰርያ ተብሎ ወጭ የሆነው ገንዘብ ወደ እንግሊዝ አገር አሸሽቶታል፡፡
 
10. የዉሃ ሽታ ሆኖ የቀረው የወረቀትና ፐልፕ ፋብሪካ
የወረቀትና ፐልፕ ፋብሪካ ጭስ አባይ ላይ መንግስት ሊገነባ የነበረውን ጥረት ላስገነባ ነው ብሎ ገንዘብ ወጭ በማድረግ ወደ እንግሊዝ አገር በተመሳሳይ ሁኔታ አሸሽቶታል፡፡ ፋብሪካውም የዉሃ ሽታ ሆኗል፡፡ለአማራ እንዴት ጠላቶቹ ፋብሪካ ይሰሩለታል ታድያ፡፡
11 . ህንጻዎቹም አገር ውስጥ ቆሙ እንጂ የእኛ አይደሉም
በጥቅሉ አለ የምንለው ግን የሌለው ጥረት ሁሉም ህንጻወች ማለትም የቃሊቲ መጋዘን፤ የባህርዳር ዋናው ቢሮ ያለበት ህንጻ፤ በአዲስ አበባ ቦሌ ወሎ ሰፈር የሚገኘው ህንጻ፤ የደብረብርሃን ህንጻ፤ የጎንደር ማበጠርያ ፋብሪካ፤ ያው ዳሸን ወደ እንግሊዞች ተላልፏል።
12  ሁሉም በእዳ ተይዘዋል
 ሁሉም በንግድ ባንክ፤ በህወሓት ባንክ(ወጋገን)፤ በኦሮሞያ ባንክ በእዳ የተያዙ ናቸው፡፡እነዚህ አሉ የተባሉት ንብረቶች በረከት እንዳለው 20 ቢሊዮን ሳይሆን 5.1 ቢሊዮን ብቻ እንደሆኑና ይህም በእዳ ወይም ሊያብሊቲ እንጅ የጥረት አንድም አንጡራ ሃብት ወይንም ኦውነር ኢኩቲ(ካፒታል) የለውም፡፡ለዚህ ነው ያለ የሚመስለን ነገር ግን የሌለው ጥረት ብለን የምንጠራው፡፡
Filed in: Amharic