>

 ሀገሪቱን ለመበተን የሚሯሯጡ አካላት ምን እስኪያደርጉ ነው የሚጠበቁት?! ? (ውብሸት ሙላት)

 ሀገሪቱን ለመበተን የሚሯሯጡ አካላት ምን እስኪያደርጉ ነው የሚጠበቁት?! ?

 

ውብሸት ሙላት
የፌደራል መንግሥት ቀንደኛ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ካላዋለ በአገሪቱ ዉስጥ ግጭት፣ መፈናቀል፣ ሞት መቀጠሉ አይቀሬ ነዉ። በርካታ ወንጀል ዉስጥ ተዘፍቀዉ የነበሩ፣ ከአቅማቸው በላይ ሃብት ያጋበሱ ተሿሚዎችን ከሥልጣን አስወግዶ፣ ወንጀል እንደፈጸሙ በዐደባባይ እያወጁ ነገር ግን በቁጥጥር ሥር አለማዋል ትርፉ ግጭትና ትርምስን መጋበዝ ነዉ።
 መረጃ ከሰበሰቡ በኋላ በቁጥጥር ሥር ማዋል ማለት የተጠርጣሪን ማንነት ለሕዝብ ይፋ ማድረግን አይጨምርም። እንኳንስ ሕዝብ እንዲያውቅ ይቅርና ተጠርጣሪውም ቢሆን ማወቅ የለበትም። ካወቀም መረጃ እንዳያጠፋ፣ ሌላ የወንጀል ተግባር እንዳይፈጽም ማድረግ አስፈላጊ ነዉ።
በአገሪቱ ግጭቶች እየበረከቱ ነዉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይን ለመግደል የወንጀል ድርጊቱን አቀነባብሯል ተብሎ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይፋ  ከተደረገ በኋላ እንኳን በቁጥጥር ሥር አለማዋል ሽብር እንዲነዙ፣ ግጭት እንዲቀምሩ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነዉ።
እነ በረከት ስምኦንም ሆኑ የሴራና የዝርፊያ ጓዶቻቸው በወንጀል ሊጠየቁ እንደሚችሉ በአዋጅ እየለፈፉ በቁጥጥር ሥር አለማዋል አንድም ከነበረከት፣  የእነ ጌታቸው አሰፋ፣ ታደሰ ካሳ፣ አቦይ ስብሃት፣ አባይ ጸሀዬን ጥርሳቸውን የነቀሉበትን ኢትዮጵያን የማውደም ተልእኮ (ፍላጎት) አለመረዳት ነው። በተለይ ከእነዚህ ሰዎች ቂምም ጥላቻም የሚገነው አማራ ላይ ስለሆነ የክፋትና የአልሞትባይ ተጋዳይነት የጥፋት መረባቸዉ የሚያርፈው አማራ ክልል ላይ ነው።
ስለሆነም የፌደራል መንግሥት በአፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል። ንጹህ ሰዉ እየሞተ ለወንጀለኞች የሚደረግ እንክብካቤ ሊቆም ይገባል። የትግራይ ክልልም ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆነ የፌደሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክልሉን መንግሥት በማገድ (በመበተን) ክልሉ በፌደራል መንግሥት እንዲተዳደር በሕገ-መንግሥቱ እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 መሠረት ውሳኔ ማሳለፍ ይጠበቅባቸዋል።
Filed in: Amharic