ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ንግግር ላይ የተቀነጨበ
(በ ግርማቸው ምህረት)
“አንዳንዶች፣ እንደህዝብ እየገጠሙን ላሉት ችግሮች መፍትሄው “አንድ አይነትነት” እንደሆነ ያስባሉ፡፡ አንድ አይነት መሆን ለችግሮቻችን መፍትሄ ወይም ለጥንካሬያችን ዋስትና አለመሆኑን ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ ከጎረቤት አገራት ታሪክ ልንማር እንችላለን፡፡ ብዝሃነት፣ ፀጋ እንጂ እርግማን አለመሆኑን ሁላችንም መረዳት ይኖርብናል፡፡
“አዳዲስ ጋሬጣዎችን ለማለፍ የሀሳብ ብዝሃነት ያስፈልገናል፡፡ ሀሳባችንን አዋህደን በወፍራም ሀሳብ ጋሬጣዎቻችን ለማለፍ የምናደርገው ጥረት አገር የመሆናችንን ትርጉም ያጎላዋል እንጂ አያቀጭጨውም፡፡ በተቃራኒው በትናንሽ ሀሳቦች ስንመራ የበለጠ እንኮስሳለን እንጂ የምናተርፈው ምንም ነገር አይኖርም፡፡
ጥቂት የማይባሉ ግለሰቦች ማወቃቸውን ለማሳየት የሚጣጣሩት ከግንቡ ይልቅ ሽንቁሩን አጉልተው በመናገር ነው፡፡ ቀዳዳውን ከመድፈን ይልቅ ለማስፋት በመቆፈር ጊዜያቸውን ያጠፋሉ፡፡
“ትንሽ ማወቅ አደገኛ ነው” ይባላል፤ እውነትም ነው፣በተንሸዋረረ መንገድ የተጀመረ ማወቅ ካለማወቅ ይብሳል፤ ልዩነትን ብቻ እንድናይ ያደርጋልና፡፡ ብዙ እያወቅን ስንመጣ ግን ወደ አንድነት እንሳባለን፤ ወደ መተባበር እንመጣለን፡፡
“ውብ የሆነች ኢትዮጵያን ለእናንተ እንደምናስረክብ በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ። የቤት መፍረስ፣ ድምጸት መሰማት፣ እዚህም እዚያም ጩህት ማየት ለእኛ በእጅጉ ያበረታናል፤ እንደዛ አይነት ጉዳይ ሳይኖር ሲቀር የመዘናጋት የመተኛት ሁኔታ ስለሚያጋጥም ተግዳሮቱ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ይበልጥ ጠንክረን ህልማችንን እንድናሳካ፣ የሚያስችለን እንዳንተኛ የሚያደርገን ህብረታችንን የሚያጠነክር መልካም ሀሳብ ያላቸውን ስዎች ከዚህም- ከዚያም የሚያሰባስብ ስለሆነ፤ ከእንግዲህ በኋላ አሁን የምትሰሙት ረብሽ፣ አሁን የምትሰሙት ጥላቻ ቀጥሎ #ኢትዮጵያን ያጠባል፣ ያሳንሳል የሚል ሀሳብ በእናንተ ውስጥ እንዳይጸነስ ነው።
ተደጋግሞ እንደሚባለው፣ እውቀት ወደ አንድነት ሲመራ ድንቁርና ግን ወደ መለያየት ይወስዳል፡፡“
“እንኳን ለኢትዮጵያዊነት ቀን አደረሰን”
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ የተቀነጨበ