>

ከደርቡሽ ይልቅ ህውሓትና ግብረበላዎቹ አፄ ዮሐንስን ድጋሚ የገደሉበት መንገድ  ያማል!!! (ዘመድኩን በቀለ) 

ከደርቡሽ ይልቅ ህውሓትና ግብረበላዎቹ አፄ ዮሐንስን ድጋሚ የገደሉበት መንገድ  ያማል!!!
ዘመድኩን በቀለ 
አፄ ዮሐንስ ከሞቱ ከ130 ዓመት በኋላ በዛሬው ዕለት ንጉሠ ነገሥቱ በቆረቆሯት በመቀሌ ከተማ ላይ በልጅ ልጆቻቸው አማካኝነት በድጋሚ የተገደሉ ያህል ተሰማኝ።
 
~ ከደርቡሽ ይልቅ ህውሓት አፄ ዮሐንስን የገደለችበት መንገድ አንጨርጭሮኛል። ከምር እርር ነው ያልኩት። ደግሞም እኮ የሚከፋው ነገር ህዝቡንም አስጨንቃ አብሮ ድንጋይ እንዲወረውርና ንጉሡን በድጋሚ እንዲገደሉ ማድረጓ ነው። 
 
★ Thank you Sudan የሚል ባነርም በድፍረት ተይዞ  አደባባይ እስመውጣት ተደርሷል። ” የጨነቀለት” አለ አዝማሪው። 
 
★ ሌላው አስቂኙ ነገር በዛሬው እለት ፎቶአቸው የመቀሌውን ሰልፍ ያደንቀው አልበሽር በጅማ ከአብይ ጋር ሽር ብትን እያሉ መታየታቸው ነው።
በኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት በአፄ ዮሐንስ ፬ተኛ በሚመራው የኢትዮጵያ ጦርና በዛኪ ቱማል በሚመራው የሱዳኖቹ የደርቡሽ ጦር መካከል የዛሬ 130 ዓመት በወረራ በተያዘችውና የኢትዮጵያ ግዛት በሆነችው በጎንደሯ የመተማ ከተማ ላይ ጦርነት ተከፈተ።
የጦርነቱ መነሻ የደርቡሾች ወረራ ነው ቢባልም እዚህ ላይ ግን “ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ዮሐንስ በእንግሊዞች ምክር፣ ራስ አሉላ አባ ነጋን የቁም እስር አስረው፣ የገበሬ ጦራቸውንም በትነው እነ ጣሊያን በኤርትራ ምድር እንደልባቸው እንዲፈነጩ ካደረጉ በኋላ ነፃነቱን ለመግፈፍ ከመጣው ወራሪ የእንግሊዝ ቅኝ ገዢ በሆነችው የግብፅ ጦር ጋር ለነፃነቱ ሲል በመፋለም ላይ ከነበረውና  የሱዳና የግብፅን ጥምር ኃይል ከነፃነት ፈላጊው የሱዳን ደርቡሾች የጦር ከበባ  የእንግሊዝ ጦር ለማዳንና በሰላም ወደ ምፅዋ ለመሸኘት ነበር የዘመቱት” የሚሉም የታሪክ መዛግብት አሉ።
የሆነው ሆኖ ንጉሠ ነገሥቱ ይህን አሰቃቂ ጦርነት ከማድረጋቸው በፊት በንጉሠ ነገሥቱ አፄ ዮሐንስ ትዕዛዝ የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ሠራዊታቸውን ይዘው ከዚህ የደርቡሽ ጦር ጋር በመግጠም  ለመፋለም ሞክረው ነበር። የጐጃሙ ንጉሥ ጦርም ሳር ውኃ በተባለው አካባቢ ከደርቡሾቹ ጦር ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ ቢያደርግም ድል ስላልቀናው ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ራሳቸውንና ከጥቂት ሠራዊቶቻቸው ጋር ሆነው ሲያፈገፍጉ ቁጥሩ ብዙ የሆነ የጎጃም ጦር ሠራዊት ግን ለከፋ ሞትና ለምርኮ ተዳረገ። የተማረኩት፣ የቆሰሉት የሠራዊቱ አባላትም በማራኪዎቹ የሱዳን ጦር በአሰቃቂ ሁኔታ ታረዱ።
የኢትዮጵያኖቹን መሸነፍ፣ መማረክና በጭካኞቹ የደርቡሽ ጦር መታረድን የሰሙትና ያዘኑት አፄ ዮሐንስም ከጣልያኖች ጋር በምፅዋ ጉዳይ ሰሃጢ ላይ የነበራቸውን ፍጥጫ አቁመው ወደ መተማ ለመዝመት ተገደዱ።
ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ወደ መተማው የጦር ሜዳ ሲሄዱ ለውጊያ የሚሆን አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ የጦር ሠራዊትና ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን አስከትለው ነበር የዘመቱት።
ሱዳኖቹ የኢትዮጵያው ንጉሣችን አፄ ዮሐንስ ለእንጊሊዞቹ ተደርበውና አግዘው ጎረቤት ሀገር የሆነችውን ሱዳንን ለመውጋት መምጣታቸው ክፉኛ እንዳበሳጫቸው ይነገራል። መበሳጨት ብቻ ሳይሆን ደማቸውን አፍልቶ ነበር የጠበቋቸው የሚሉም አሉ። ለዚህም ነው በዛኪ ቱማል የሚመራው የሱዳን ጦር በመተማ ላይ ጠንካራ ምሽግ ሠርቶ፣ ዙሪያውንም በሹል እንጨትና በድንጋይ አጥሮ ወደ 80 ሺህ ይደርሳል ተብሎ የተገመተውን የተቆጣ ሠራዊት አዘጋጅቶ የጠበቃቸው፡፡
መጋቢት 1 ቀን ጠዋት ላይ ከማኅበረ ሥላሴ ገዳም ማዶ ጦርነቱ ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በጀግንነት እየተዋጋ የመጀመሪያውን የዛኪ ቱማልን ምሽግ ጥሶም ገባ፡፡ ድል ለኢትዮጵያውያን የቀረበ መሰለ። በተለይ በሳር ውኃው ጦርነት የሞቱትንና በየሥፍራው የወደቀውን የጎጃሙን ንጉሥ ተክለሃይማኖት ሠራዊት የሆኑ ዜጐቻቸውን አስከሬን ባዩ ጊዜም ንጉሡ ቁጭት ገባቸው። በንዴትና በወኔም አፄ ዮሐስን ራሳቸው እንደ አንድ ወታደር ሆነው በየጦር ግንባሩ ገብተው ይዋጉም ያዋጉም ጀመር።
በሁለቱ መካከል የነበረው ጦርነትም በሰፊው ቀጠለ። የኢትዮጵያ ሠራዊት ድል ለማድረግ በተቃረበበትና የሱዳን ሠራዊት ከምሽጉ ወጥቶ ለመሸሽ በተዘጋጀበት ወቅት አፄ ዮሐንስ እጃቸው ላይ ቆሰሉ። እንዲያም ሆኖ ግን ንጉሡ ከጦርነቱ መሃል ሳይወጡ በውጊያው ገፉበት። ጦርነቱ ቀጠለ። አሁንም በድጋሚ እንደገና ንጉሠ ነገሥቱ በግራ እጃቸው አልፋ ወደ ደረታቸው በዘለቀች ጥይት ተመተው ቆሰሉ። አጃቢዎቻቸውም ወደ ድንኳናቸው ወሰዷቸው፡፡
የአፄ ዮሐንስ መቁሰል እንደተሰማ በኢትዮጵያኖች ዘንድ ድንጋጤን ተፈጠረ፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊትም የያዘውን ምሽግ እየለቀቀ መውጣትና መሸሽም ጀመረ። ሠራዊታችን ዝብርቅርቁ ወጣ። አዛዥ ጠፋ። መሪም ጠፋ። ጭራሽ ሠራዊቱ ወደ ኋላው በማፈግፈግ ከዐውደ ውጊያው ራቀ።
በተቃራኒው ደግሞ ሽንፈት እየገጠመው ለመሸሽ በመዘጋጀትና ለመሮጥ በማኮብኮብ ላይ የነበረው የዛኪ ቱማሉ የደርቡሽ ጦር ከመከላከልና ከመሸሽ ይልቅ የበመሸሽ ላይ የነበረውን ኢትዮጵያኖቹን ጦር እግር በግር እየተከታተለ ጥቃት ማድረሱን ቀጠለ፡፡
አፄ ዮሐንስም በቆሰሉ ማግስት መጋቢት 2/1881 ዓም መተማ ላይ አረፉ። የዛኪ ሠራዊትም የንጉሠ ነገሥቱ አስከሬን ያለበት ድንኳን ጋርም ደረሰ። ከበባቸውም፡፡ የንጉሠ ነገሥቱ ታላላቅ የጦር መኮንኖቻቸውና በርካታ ታማኝ ሠራዊቶቻቸውም የጌታችንን አስክሬን አናስማርክም ብለው ከደርቡሾቹ ጋር ፅኑ ውጊያ አደረጉ። ብዙዎችም በንጉሠ ነገሥታቸው አስከሬን ዙሪያ እንደ ቅጠል ረገፉ፡፡
በመጨረሻም በሱዳኑ የዛኪ ቱማሉ የሚመራው የደርቡሽ ሠራዊት ድል በማድረግ የኢትዮጵያዊውን ንጉሠ ነገሥት የአፄ ዮሐንስን አስክሬን ማረከ፡፡ ማርኮም አልቀረ ወስዶ አንገታቸውንም ቆርጦ ወሰደው። በካርቱም የገበያ መሃልም እያዞሩ ፎከሩበት። በመጨረሻም አንገታቸውን በሙዚየም አስቀመጡት። ይኸው እስከዛሬም ድረስ የንጉሠ ነገሥቱን ተቆርጦ ሱዳኖች የሚጎበኙት የተቆረጠ አንገት በክብር ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ለማድረግ የሞከረ የለም።እዚያው ካርቱም ሱዳኖች ይዘባበቱበታል።
ይኸው ንጉሠ ነገሥቱ ካረፉ ከመቶ ዓመት በኋላ የአፄ ዮሐንስ እትብት ከተቀበረበት ከትግራይ ምድር የተነሱ የፅዮን ልጆች ኢትዮጵያን የመግዛት ዕድል አገኙ። ይህቺ ታላቅ ሀገርም በእጃቸው ወደቀች። ባለጊዜዎቹም ሀገሪቱን በቁሟ በሏት። ህዝቡንም በዘር ከፋፍለው እሳትና ጭድ አደረጉት። መርከብና አውሮጵላን የሚሰርቁ ጉደኞችም ሆነው ተገኙ። ብልት መኮላሸት፣ በእስረኞች ላይም ግብረ ሰዶም መፈጸም ከፅዮን ደብር የመጡ ነውረኞች ነውረኛ ተግባር ሆኖ በታሪክ ተመዘገበ።
አሁን ነውረኞቹ ከመሃል ሀገር ሸሽተው የትግሬ ህዝብ ቀሚስ ስር ተደብቀዋል። ይተማመኑበት የነበረው ሁሉ ከድቷቸዋል። አማሪካም እግዚአብሔርም፣ ዲያብሎስም ፊት ነስተዋቸዋል። ይተማመኑ ይመኩበት፣ ጀግንነቱንም አብዝተው ያወሩለት የሌባ አቀባዩ ወዳጃቸው የመብራት ኃይል ሠራተኛው የሱማሌው አብዲ ኢሌም ቀን ጥሎት ቂሊንጦ ወረደባቸው። የጋምቤላው ታዛዥ አመራራቸውም ተሸቀንጥሮ ወርዷል። መሬት ተቀራማቾችም ጉዳቸው ፈልቷል። ይመኩበት የነበረውና አፈናቅል ሲሉት የሚያፈናቅለው፣ ግደል ሲሉትም የሚገድለው የደቡቡ ሽፈራው ሽጉጤም ድራሹ ጠፍቷል። ቤንሻንጉልም ተጠርንፏል። ሽንፍላው ብአዴን ባይጠራም አብዛኛው የህውሓት ኔትወርክ ተበጣጥሷል። የቀረው አፋር ነበር እሱም ሰሞኑን ልሳኑ ተዘግቷል። አሁን ህወሓቶች ይመኩበት ይኮሩበት ፓርቲም ሆነ ድርጅት ከኢትዮጵያ ምድር ድራሹ ጠፍቷል።
እናም ህውሓቶች ነፍስ ውጪ ነፍስም ግቢ ላይ ናቸው። 27 ዓመት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሰለፍ ከዳር ቆመው ያዩ የነበሩ ትግሬዎችም አሁን የጊዜ ጉዳይ ሆነና ወጉ ደርሷቸው በሳምንት ሦስቴ መላቅጡ የጠፋው ሰልፍ አይሉት ደርፊ ብቻ አደባባይ ወጥቶ ውሎ ማደር ሆኗል ሥራቸው። ሠልፉ ግን ህውሓትን የሚያድናት አይመስልም። ሠልፍ መሪን የሚያድን ቢሆን ኖሮ ጋዳፊና ሳዳም ሁሴን በአድናቂዎቻቸው ሰልፍ ከጉድጋድ ወጥተው ከመዋረድ በተረፉ ነበር። ለውጡ የግድ፣ ደግሞም የምር ከሆነና በኃያላኑ የተወሰነ ከሆነ የቀን ጉዳይ እንጂ ለህውሓት እንደሌሎቹ ስሟንም ጾታዋንም መቀየሩ አይቀርላትም። ዓረናም ቤተመንግሥት ውሎ ወደ መቀሌ ከተመለሰ በኋላ የልብልብ አግኝቶ ያለቅጥ የሚፎክረው የሰማውና ያረጋገጠው ነገር ቢኖር እንደሆነ ይነገራል። እናም የሆነ ቀን ህውሓት ይወርዳል፣ መውረድ ብቻ አይደለም እንደ ናዚ ፓርቲ ከምድረገጽ ስሙ ይደመሰሳል። ወንጀለኞቹም ሁሉ ከተደበቁበት ጉድጓድ ወጥተው ማንቁርታቸውን እየታነቁ ለፍርድ ይቀርባሉ። ሣልሳይ ወያነ፣ ራብአይ ምናምን አይሠራም። ፉከራና ሽለላ ቀረርቶም አያድንም። አከተመ።
እኔን የገረመኝ ግን ሰልፋቸው አይደለም። መሰለፉን ይሰለፉ። ሰልፉ ግን አሳዛኝና አሳፋሪ ሰልፍ ነው። የሚከነክንና የሚያንገበግም ሰልፍ ነው። ለሌባ፣ ለገዳይ፣ ጥብቅና መቆማቸው ሳያንስ በዛሬው የመቀሌ ሰልፍ ላይ ንጉሥ አፄ ዮሐንስን በድጋሚ መግደላቸው ነው። ህውሓቶቹ የአያታቸውን የአፄ ዮሐንስን አንገት ቆርጣ የወሰደችውንና እስከአሁን ድረስም የንጉሠ ነገሥቱን አንገት በሙዚየም አስቀምጣ መሳቂያ መሳለቂያ እያደረገች ያለችውን የሱዳንን ባንዲራ፣ ሰንደቅ ዓላማዋንም ይዘውና ተሸክመው አደባባይ መውጣታቸው ነው። በእነሱ ቤት ኢትዮጵያውያንን ማብሸቃቸው ነው። በጣና መብራት ደምቀው በሱዳን ይኮራሉ። በፌደራል መንግሥቱ በጀት እየተዳደሩ ኢትዮጵያን ይጠላሉ። ለሱዳን ያሸበሽባሉ።
እናም አፄ ዮሐንስ ከሞቱ ከ130 ዓመት በኋላ በዛሬው ዕለት ህዳር 29/2011 ዓም በትግራይ ክፍለ ሀገር በመቀሌ ከተማ በድጋሚ በራሳቸው የልጅ ልጆች እጅ ይገደላሉ። እነሱ ይፈነጥዛሉ እኛ ግን እናዝናለን። እናለቅሳለንም።
የዛሬው የመቀሌ ሰልፍ የህውሓት የመጨረሻዋ የአደባባይ ሰልፍ ይሁን። አሟሟቷን አያሳምርላት። ተዝካሯም ይሁን። ኢትዮጵያን በዘር እንደከፋፈለች ዕጣ ፈንታዋ ዕድል ተርታዋ ይከፋፈል። መታሰቢያዋ በምድር አይገኝ። ከታሪክም ከትውልድም ይደምሰስ። ድቅድቅ ጨለማም ይወጣት። ህዙቡን ግን እግዚአብሔር ይድረስለት። ከህውሓት የሱዳን መተት ይገላግለው። አሜን።
እኛ ግን የግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱን የአፄ ዮሐንስን
 ” የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት። ሁለተኛ ዘውድህ ናት። ሦስተኛ ሚስትህ ናት። አራተኛ ልጅህ ናት። አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናትን ፍቅር፣ የዘውድን ክብር፣ የሚስትን ደግነት፣ የልጅን ደስታ፣  የመቃብር ከባድነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።” የሚለውን ወርቃማና ዘመን አይሽሬ ንግግራቸውን እያስታወስን እንፅናናለን።
አፄ ዮሐንስ ” ከኢትዮጵያዊው ዐማራ ይልቅ፣ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ጠላትን ለመደምሰስ አብሮ ከዘመተው፣ በንጉሡ አስከሬን አጠገብም እንደ ቅጠል ከረገፈው ኢትዮጵያዊ ይልቅ ሱዳኖች ይሻሉናል አሉ የተባለውን የትግሬዎቹን መሪ የደብረ ጽዮንንም ቃል እንኳንም አልሰሙ።”
#ማስታወሻ | ~ ለማንኛውም የከፋው ጥቁር ቀን ከደጃችን ቆሟል። እናም ወደ ፈጣሪ መጸለዩን፣ ንስሐ መግባቱንም አንዘንጋ። ” ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። “ማቴ 24፣ 42-44 ።
ሻሎም !  ሰላም !
ሕዳር 29/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic