>

የመቀሌው ጩኸትና የኛ ጉልበት (ምሕረቱ ዘገዬ)

የመቀሌው ጩኸትና የኛ ጉልበት

ምሕረቱ ዘገዬ አዲስ አበባ

ከመቀሌ የሚሰማው ጩኸት፣ ዛቻና ማስፈራሪያ ያላንዳች ፋታ መቀጠሉ ግልፅ ነው፡፡ የወያኔ ደጋፊ ነን የሚሉና ሥርዓቱ ጥቅሙን ለማስከበር አደራጅቷቸው የቆዩ አካላትና ግለሰቦች ሁሉ በአዲስ አበባ ጭምር በጋራ እየተገናኙ በትላልቅና ትናንሽ የመዝናኛ ሥፍራዎች ሣይቀር በግልጽም በኅቡዕም እየተገናኙ እንደሚዶልቱ ለተራው ህዝብ ሣይቀር ግልፅ እየሆነ መጥቷል፡፡ እነዚህ አካላትና ግለሰቦች የይቅርታ እጁን የዘረጋን መንግሥት ከማናናቅ አልፈው ግፍና መከራ የደረሰባቸውን ወገኖቻችንን ዋይታና ሥቃይ በአንደበትም በማኅበራዊ ገፆችም እያጥላሉና እያላገጡባቸው መሆኑ የክፋትና የንቀት ጣሪያቸው የት እንደደረሰ ያመለክታል፡፡ ከዚያም ባለፈ የስቃይ ሰለባዎች በወያኔ የእስር ቤት ባለሟሎች የደረሰባቸውን ግፍና በደል ለምን ለሕዝብ ይፋ አደረጉ በሚል ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲሁም አካላዊ ጥቃት ለማድረስ እየተጋበዙ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡

ምንም እንኳን መንግሥት የራሱን ምላሽ በተለያየ መልክ እየሰጠ ቢሆንም የወያኔን ግፍ ተቃዋሚ የሆነው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ግን በአብዛኛው መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ከመወትወት ያለፈ ተግባር ሲፈጸም አይታይም፡፡ የራሱን አቅምና ጉልበት ረስቶ ዛሬም ወደላይ እያንጋጠጠ ነው፡፡ በወያኔ ዘመን ያለአግባብ ባለሀብት የሆኑ ሁሉ ከኛ ኪስ በሚገኝ ገንዘብ ዛሬም እየበለፀጉ መልሰው ሀገሪቷን ወደ ዕልቂት ጫፍ ሊወስዷት የቀቢፀ ተስፋ ሙከራቸውን እያጧጧፉ ይገኛሉ፡፡

የእነርሱ የመዶለቻ ሆቴሎች፣ ዕቃ መሸጫ ሱቆች፤ የሚከራዩ ህንጻዎች፤ የንግድ መደብሮች ዛሬም ያላንዳች ማስተዋል የምናደርግላቸው ግብይት ለወገኖቻችን ጥቃትና ዕልቂት የእጅ አዙር ዕርዳታ እያደረግን ያለነው እኛው መሆናችንን ማስተዋል እንኳን አቅቶናል፡፡ ዛሬም የወያኔን ዕኩይ ተግባር ከሚቃወሙ የትግራይ ወገኖቻችን ጋር መቆምና የዐረመኔው ሥርዓት እንዲመለስ በትጋት የሚሠሩ ግለሰቦችንና ተቋማትን መለየትና መከታተል፣ ለተገቢው አካልም መጠቆም አለብን፡፡ በተጨማሪም ለነዚህ ወያኔያዊ ግለሰቦችና ተቋማት ጥበቃና ከለላ ማድረግ ቢገባንም የኪሳቸው መደለቢያ ላለመሆን በግልና በጋራ ማድረግ  ያለብንን ሁሉ እንፈፅም፡፡

የህዝብ ጉልበት ከመንግሥት ጉልበት የላቀ መሆኑን ለማሳየት የህንድና የደቡብ አፍሪካ ትግሎች በቂ ማሣያ ናቸው፡፡ የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንዳይደናቀፍ የእያንዳንዳችን ጠብታ ጥረት ብቻ ነው ወሣኙ መፍትሔ፡፡ በአስተውሎት እንራመድ፤ እንደራጅ፣ ተገቢ በሆነ መንገድ ሁሉ ለውጡን እንጠብቅ፡፡ የእያንዳንዳችን አነስተኛ አስተዋፅዖ ለውጡን ለመጠበቅ ከፍተኛ ኃይል እንዳለው አንዘንጋ፡፡ ለጠላት ምቹ ሆነን አንገኝ፡፡ በጠላት የሽያጭ መደብሮች የምናወጣ እያንዳንዷ ሣንቲም የጠላትን ዕድ እንደምታረዝም እንረዳ፡፡ ስለዚህ በኢኮኖሚው ረገድ የምናፈረጥምላቸውን አቅም እናቁምና በጤነኞችና ሀገር ወዳዶች መዝናኛዎችና መደብሮች እንዲሁም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንገልገል፡፡ እኛን የሚያጠቁበትን የመግደያ መሣሪያውን እኛው ራሳችን ከማቀበል እንቆጠብ፡፡ ይህም አንዱና ትልቁ ራስን ከጠላት የመከላከያ ዘዴ ነውና በቶሎ ተግባራዊ እናድርገው፡፡

Filed in: Amharic