>

ታደሰ ጥንቅሹና የወሎ ቴሪሸሪኬር ሆስፒታል ነገር....!!! (ውብሸት ሙላት)

ታደሰ ጥንቅሹና የወሎ ቴሪሸሪኬር ሆስፒታል ነገር….!!!
ውብሸት ሙላት
ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) የቦርድ ሰብሳቢ መሆን አንድ የማጥቂያም የመቆጣጠሪያ ስልቱም ናት። የባህር ዳር፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ የአባይ ባንክ ወዘተ የቦርድ ሰብሳቢ ነበር። የወሎ ዩኒቨርሲቲን ሲያበላሽ ኑሮ ከዚያ ሲለቅ የወሎ ቴሪሸሪኬር ሆስፒታል አሠሪ ኮሚቴ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነ። ከዚያ የተሰበሰበውን ገንዘብ እንኳን እንዳይሰጥ አድርጓል። ገንዘቡ ወደ ዩኒቨርሲቲው አልተላለፈም። እንደውም ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በአስቸኳይ ኮሚቴው ገንዘቡን ጨምሮ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ እንዲያስረክብ አቶ ደመቀ መኮንን ቢሮ ተወስኖ ነበር። ስብሰባው ላይ ታደሰ፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ፣ አቶ ገዱ …. ነበሩ። አቶ ብናልፍ አንዷለም ደግሞ አረካካቢ ሆነው ተሰየሙ። ይሄው ዛሬ እስከሚታሠሩ ድረስ አቶ ታደሰ ካሳ ለማስረከብ አልፈለጉም። ሥራ አስኪያጁም (አቶ እሸቱ አየለ) እንዲሁ ፈቃደኛ አልሆኑም።
ለማንኛውም ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ሕወሃት የአማራ ክልልን ቅኝ ግዛት ስትይዝ የቅኝ ግዛት (Colonial)  ሚኒስትር አድርጋ የሾመችው ሰው ስለሆነ ይሄው ሆስፒታሉ እንዳይሰራ አንዱ ወጥመድ ሆኖ ቆይቷል።
እንኳም ገቢ ሆነ። ስለ ሆስፒታሉ አሠራር ወይም እንዴት መገንባት እንዳለበት እና፣ ሌላም ሴራ ስለነበር፣ እመለስበታለሁ።
ሆስፒታሉንም እንሠራዋለን!
Filed in: Amharic