>

መሬት የቸበቸቡ ካድሬዎቹን እየሾሙ ድሆች ላይ በግሬደር መዝመት ምን ይሉታል!?! (ሳምሶን ሚሀይሎቪች)

መሬት የቸበቸቡ ካድሬዎቹን እየሾሙ ድሆች ላይ በግሬደር መዝመት ምን ይሉታል!?!
ስም ስም ሚሀይሎቪች
የኦሮሞ ብሄረተኞች በአዲስአበባ ጉዳይ ከሚያሰራጩት ትርክት ውስጥ የኦሮሞ አርሶ አደሮች መሬት ነጠቃ ጉዳይ ነው። ጉዳዩን እስቲ እንየው
፩ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የኦሮሞ ገበሬን መሬት ከህወሃት የመሬት ደላሎች ጋር ሆኖ የቸበቸበው የራሱ የኦህዴድ ካድሬ እንደነበር ይሰመርበት ። ስለዚህ በድሀ አርሶአደሮች ህይወት ላይ የቆመሩት ጊዜ የሰጣቸው የኦሮሞ ብልጣብልጦች እንጄ ሌላ ማንም አይደለም። የአዲስአበባ አስተዳደር እጁ ነበረበት ከተባለ ከኩማ ደመቅሳ ፣ ድሪባ ኩማ ጀምሮ እጁ ያልተነካካ የኦህዴድ ሰው አልነበረም። የአባዱላ ልጆች ቡራዮ፣ ሰበታ ፣ ኮተቤ ፣ ቃሊቲ ፣ ቦሌ ቡልቡላ ወዘተ በመሬት ሽያጭ በአንድ ሌሊት ሚሊየነሮች ሲሆኑ እንደነበር ይህ ነውር አሁንም እንደቀጠለ ልብ ይባል ።
፪ ዛሬ የለገጣፎ አስተዳደር ከ 12 ሺ በላይ ዜጎችን በህገወጥ ነዋሪነት ስም ቤታቸውን የማፍረስ ዘመቻ መጀመሩን አሳውቋል። የኦሮሞ አክትቪስቶች እልልታቸውን መቆጣጠራቸውን አልቻሉም ፣ ተፈናቃዮቹ እነርሱ ‘ሰፋሪ’ የሚሏቸው ወገኖች ይሆናሉ በሚል ግምት። ነገ ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎች ናቸው ቢባል ይሄ እልልታ ወደ ኡኡታና ኦሮሞ ተፈጀ ዜና ይቀየራል። የገዛ ዜጋህ ከመኖሪያው ሲፈናቀል “እልል” የሚያሰኝ ነውረኛ ባህሪ ከየት መጣ ? ትናንት ገበሬዎች ከመሬታቸው ተፈናቀሉ ሲሉ ሲጮሁ የነበሩ ብሄረተኞች በምን ሂሳብ እነዚህ ወገኖች ላይ ለጭካኔ ተጣደፉ ?
፫ ለገጣፎ ላይ ቤት ሰርተው ለአመታት የኖሩት ወገኖች መሬቱ የተሸጠላቸው በአካባቢው ሰዎች ግብርም ለከተማው አስተዳደር ሲከፍሉ የኖሩ ናቸው። መሬት ሻጮቹም ፣ የሽያጭ ሂደቱ ውስጥ የነበሩ የአካባቢው ፓለቲከኞች ዛሬ ከዳር ቁጭ ብለው እየሳቁ ይሆናል ። ይህም ብቻ አይደለም ትናንት መሬቱን የሸጡ ሰዎች ዳግም መሬቱ ይለገሳቸው አልያም የበለጠ ለሚከፍል እንደገና ለመሸጥ ሁለተኛ ዙር ድለላም ለመጀመር ሴራው ተጠናቆም ይሆናል !
ኦዴፓ ድፍረቱ ቢኖረው ድሆች ላይ በግሬደር እንደዘመተው ሁሉ መሬት ሽያጭ ላይ የተሰማሩትን የራሱን ካድሬዎች ይዘምትባቸው ነበር። በብሄር ፓለቲካ ይሄ ከሚሆን ግመል በመርፌ ቀዳዳ …
Filed in: Amharic