>
5:10 pm - Wednesday January 26, 2022

ሰዉ በአባቶቹ ሀገር "መጤ ነህ" ሲባል እንዴት አሜን ብሎ ይቀበላል? የኦሮሞ: የትግሬ : የአማራ የሚባል ምድር የለም!!! (ሸንቁጥ አየለ)

ሰዉ በአባቶቹ ሀገር “መጤ ነህ” ሲባል እንዴት አሜን ብሎ ይቀበላል? የኦሮሞ: የትግሬ : የአማራ የሚባል ምድር የለም!!!
ሸንቁጥ አየለ
 
* የጀዋር ዋና አላማዉ መሃል ኢትዮጵያን ወደ ትርምስ ከቶ ክርስቲያኑን የሸዋ ኦሮሞ ከቀሪዉ ኢትዮጵያዊ ጋር ብጥብጥ ዉስጥ አስገብቶ እሱ አክራሪ የአይ ኤስ ኤስ እስልምና ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት ነዉ!!!
—–
የአዲስ አበባ ህዝብ አራት ኪሎ: ፒያሳ: ካሳንቺስ:ቦሌ አሁን ደግሞ ለገጣፎ ታላላቅ ወንጀሎች በወገኑ ላይ ሲፈጸም ባላዬሁም ለማለፍ ቢሞክርም ከእዉነታዉ መሸሽ አልቻለም:: እያንዳንዱም ወደ እራሱ ደጅ እስኪመጣ መጠበቅን የመረጠ ይመስላል::
ከጉራ ፋርዳ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች(ህጻናትን: አዛዉንትን: ሴት ወንዱን ጨምሮ ) ሲባረር እና ሲፈናቀል የተሰጠዉ ምክንያት ልክ እንደ ለገጣፎ ህዝብ መሬት ወራሪ ናችሁ የሚል ነበር::
የህጉን ስርዓት ለመፈተን እና የስርዓቱን ዝቅጠትም በደንብ ለመረዳት ስል እኔ እራሴ ከጉራ ፋርዳ ተፈናቃዮች ጋር በመሆን በብዙ ሽህ ገጽ ሰነድ ከነዚህ ተፈናቃዮች አሰባስቤ ነበር::መሬት የገበሩበት: ለሃያ እና ከዚያም በላይ አመታት የኖሩበት: ቤት የሰሩበት: ትምህርት ቤት የሰሩበት: የልማት ተሸላሚ የሆኑበት: መንገድ የሰሩበት እና በርካታ ሰነዶችን አያይዘን በዚያ ጊዜ ለነበረዉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ: ለፌደሬሽን ቢሮ:  ለኢምባሲዎች: ለሚዲያዎች  በዞን በወረዳ እና በክልል ደረጃ ላሉ ቢሮዎች ሁሉ እንዲገባ እና ለተፈናቃዮች ፍትህ እንዲሰጣቸዉ ጥረት ተደርጎ ነበር::ወፍ የለም::አንዳንዱ ጋ መልሱ ሰዎቹን መደብደብ ማንጓጠጥ እና መሳደብ ነበር::ይሄ አይነት ነገር ከብዙ አካባቢ ላለፉት ሰላሳ አመታት ሲፈናቀሉ ዜጎች ላይ ሲከሰት ነበር::
ሂደቱ ተመሳሳይ ነዉ::ሰዎች ተፈናቅለዉ: ቤታቸዉ ተቃጥሎ: ከነበሩበት በሀይል በጠመንጃ እንደ ዝንጀሮ እየተባረሩ በጎዳ ላይ ይወድቃሉ::በበሽታ ያልቃሉ::በሞት ይቀጠፋሉ::ወገናቸዉ: የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ወይም መንግስት: ወይም የፍትህ ትቋማት ዞሮ አያያቸዉም::በጣም ከሚገርመዉ ነገር ግን ተፈናቃዮች ተስፋ የሚያደርጉት መንግስት ወይም ህዝቡ ወይም የአለም ማህበረሰብ ለእነሱ የሆነ ነገር እንደሚያደርጉላቸዉ ነዉ:: እዉነታዉ ግን የተፈናቃዮች የመጨረሻ እጣ ፋንታ በጎዳና ተበትኖ ሞት ነዉ::አሁንም የአዲስ አበባን እና የዙሪያዉን ህዝብ ጀዋር/ኦነግ/ኦዲፒ በጋራ ተባብረዉ ሊያደርጉት ያሰቡት ይሄንኑ ነዉ::ስራቸዉን በሚገባ ጀምረዋል::
ከሁሉም ከሁሉ የማዝነዉ ግን በኢትዮጵያ ህዝብ አላዬሁም አልሰማሁም ብሎ ለማለፍ ግፍን ላለመቃወም በሚያደርገዉ ሙከራ ነበር::ከዚህ የህዝቡ የግፍ ተባባሪ ባህሪ ይልቅ ደግሞ ግፍ የተፈጸመባቸዉ ሰዎች መንግስት በሚባለዉ ተቋም ላይ ያላቸዉ ተስፋ እና እምነት ይገርመኝም ነበር::
ሰው ከተፈናቀል እና ቤቱ በላዩ ላይ ከፈረሰበት ብኋላ እንዴት ንዴት እና ቁጣ በዉስጡ አይነድም? እንዴትስ ወደ በቀል ለመግባት አይነሳሳም?  ሰዉ በአባቶቹ ሀገር ላይ እንዴት መጤ ነህ ተብሎ ሲነገረዉ አሜን ብሎ ይቀበላል? የኦሮሞ: የትግሬ : የአማራ የሚባል ምድር የለም::ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ነች::ነጻዎቹ ነገስታት በነጻነት ያስተዳደሩት ህዝብ እንዴት እንዲህ በጥቂት አመታት ዉስጥ እራሱን ለባርነት አስተሳሰብ አሳልፎ ሊሰጥ ቻለ::መጤ ነህ ያለዉን ባለስልጣን ስሩን መንቀል ይገባል እንጅ እንዴት ሰዉ መጤ ነህ ሲባል ዝም ይላል::ኢትዮጵያ የአባቶችህ ሀገር መሆኑን እስክታምን የሀገር ባለቤት አትሆንም::የሀገር ባለቤት ካልሆንክ ደግሞ ቤትህን እያፈረሱ በጎዳና ላይ ሲበትኑህ ለመቀበል የተዘጋጀ ልብ ይኖርሃል::
አሁንም ከለገጣፎ የተፈናቀሉ ዜጎች ከቢሮ ቢሮ ቢሮጡ መፍተሄ የለም:: ኢህዴግ እንደ አጠቃላይ እንዲሁም ኦነግ በተለዬ መልኩ ፍትህ እና ሰላም አይገባቸዉም::
መፍትሄዉ አጠቃላይ ህዝቡ ዉስጥ ዉስጡን በመደራጀት እንዲህ አይነት ግፎችን መቃወም  ብቻ ሳይሆን ግፈኞችን መቅጣትም መቻል አለበት::አሁን ኦህዴድ /ኦነግ የጀመሩት ወንጀል እና ግፍ አጠቃላይ አዲስ አበባን እና አዲስ አበባ ዙሪያዉን ሳያጠፋ አይቆምም::በዚህ ግን አይቆምም::ወደ መላዉ ሸዋ ይዛመታል እንጅ::ሸዋ ቁርጥህን እወቅ::ጀዋራዉያን/ኦነጋዉያን የአባቶችህን የሽህ እና ሽህ ዘመናት መሬት እና ሀገር የአንተ አይደለም ነዉ የሚሉህ::
የጀዋር ዋና አላማዉ መሃል ኢትዮጵያን ወደ ትርምስ ከቶ ክርስቲያኑን የሸዋ ኦሮሞ ከቀሪዉ ኢትዮጵያዊ ጋር ብጥብጥ ዉስጥ አስገብቶ እሱ አክራሪ የአይ ኤስ ኤስ እስልምና ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት ነዉ:: ለዚህም ዋና ስትራቴጅክ ቦታ ሆኖ ያገኘዉ አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ነዉ::አሁን ይሄን እዉነታ ክርስቲያን ኦሮሞዎች አልተረዱትም:: ጀዋር አጀንዳዉ የኦሮሞ ጥቅም አይደለም::የጀዋር አጀንዳ ክርስቲያኑን ኦሮሞ መጀመሪያ ከቀሪዉ ኢትዮጵያዊ ጋር ማፋጀት ነዉ::ከዚያም ብኋላ ክርስቲያኑን ኦሮሞ እራሱን በአክራሪ የአይ ኤስ ኤስ አንገት የመቅላት ስልት ወይ በግድ ያሰልመዋል አለዚያም ይጨፈጭፈዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብም አያገባኝም ብሎ ለጥ ብሏል::በተለይም የአዲስ አበባ ህዝብ ለራስህ ከራስህ በላይ መድሃኒት የለህም::እድልህ በራስህ እጅ ነዉ::እነ ጀዋር/ኦነጎች የሚሉት የአዲስ አበባን ህዝብ ጠርገን እናስወጣዋለን ምክንያቱም መጤ ነዉና የሚል ፉከራ አላቸዉ::
እንጅ አጠገብህ የተኛዉን ሰዉ እግር ጅብ እየበላዉ ሳለ አንድ እግሬን ጅብ እየበላኝ ነዉና ዝም በል ቢልህ አትስማዉ::የሚጎዱትም: የሚፈናቀሉትም ከማልቀስ በዘለለ ተቆጥተዉ መብታቸዉን ወደ ማስከበር መንቀሳቀስ እስኪጀምሩ ፍትህ ቀርቶ ወፍ የለም::
Filed in: Amharic