>

በዶክተር ዐቢይ አመራር ህጉ "የቆመላቸው" እና ህጉ "የቆመባቸው" ወገኖች!?! (ከድር እንድርያስ)

በዶክተር ዐቢይ አመራር ህጉ “የቆመላቸው” እና ህጉ “የቆመባቸው” ወገኖች!?!
ከድር እንድርያስ
ዶክተር ዐቢይ ባላዬ ባልሰማ ያለፋቸው የሕግ ጥሰቶች
1. ሕወሓት የቅማንት ኮሚቴዎችን እያስታጠቀችና ትጥቅ እየላከች አማራን ስታስጨፈጭፍ
2. ሕወሓት በወንጀል የሚፈለጉትን ሰብስባ መቀሌ ስትደብቅ
3. ሕወሓት የፌደራል ፖሊሶችን መቀሌ ላይ ስታስር; መከላከያ እንዳይንቀሳቀስ ሲታገድ
4. ኦነግ የ4 የወለጋ ዞኖችንና ሁለት የጉጂ ዞኖችን ፖሊስና ሚሊሺያ ትጥቅ እያስፈታ ሲወስድ
5. ኦነግ የ17 ባንኮችን ገንዘብ ሲዘርፍ
6. ኦነግ የመንግሥት መዋቅርን ሲያፈራርስ
7. የጂግጂጋና ቡራዩ ነዋሪዎች ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲጨፈጨፉ ሲዘረፉና ድርጊት ፈፃሚዎች በሰላም ከሀገር ሲወጡ
8. በአዋሳ በሻሸመኔ ቄሮና ኤጄቶ ግድያና ዝርፊያ ሲፈፅሙ
9. ስምንት መቶ ሺ ጌዲዮ ከጉጂ ሲፈናቀል
10. በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማሮች ሲፈናቀሉ
11. ትግራይና ኦሮሚያ ለማእከላዊ ገበያ ይቀርብ የነበረውን ወርቅ ሲያስቀሩ
በሌላ በኩል” የሕግ የበላይነት ለማስከበር” በሚል አፋጣኝ እርምጃ የወሰደባቸው
1. በአዲስአበባና ድሬዳዋ በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄ የጠየቁ ትምክህተኞችን በጅምላ ማፈስና እንደቄሮና ኤጄቶ እኩል ወጣ ወጣ እንዳይሉ በአጭሩ መቅጨት
2. በለገጣፎ ቤት የገነቡ “ሕገወጦችን” (አብዛኞቹ ትምክህተኞች) ቤት በማፍረስ ቅስማቸውን መስበር
3. በኦሮሚያ ሶማሊ ክልል ድንበር የተፈናቀሉ ኦሮሞዎችን በአዲስ አበባና ዙሪያው ማስፈር
በተጨማሪም አዲስ አበባ ላይ ጎዳና ተዳዳሪዎች እንዲነሱ የሚደረገው ቀድሞውንም ሕወሀት ሲያደርግ እንደነበረው  አመፅና ሰላማዊ ሰልፍ ሲነሳ ጥቃት ይፈፅማሉ የአመፁ መሪ ይሆናሉ በሚል ነው እንጂ ለእነሱ ታስቦ አመስለኝም::
 ሕወሓትም ኤልሻዳይ የተባለ አጭበርባሪ NGO በመክፈት የአዲስ አበባ መንገዶችን ለመቆጣጠርና ከጎዳና ተዳዳሪዎች ለማፅድት ስትሞክር ነበር:: ግን ልጆቹን ለመርዳት ሳይሆን እነሱን ከአዲስአበባ ለማራቅ ነበርና የሚፈልጉት ልጆቹን በየበረሃው ሲያንከራትቷቸው ቆይተው መንግሥታቸው ሸርተት ሲል አውላላ ሜዳ ላይ በትኗቸዋል።
Filed in: Amharic