>

የቀለም አብዮት በትግራይ!?! (ህብር ራድዮ)

የቀለም አብዮት በትግራይ!?!
ህብር ራድዮ
ሕወሐት የጠላው የቀለም አብዮት ሰሞኑን በልዩ ልዩ መንገድ የትግራይ ወገኖቻችን በሚያነሱት የመብት ጥያቄ ፈቅሎ እየወጣ ነው።የብሄር ብሄረሰብ መብት አስጠባቂነት የሌሎችን መብት እየጣሰ የትግራይ ሕዝብን ጨፍልቆ ከ፪፯ ዓመት በሁዋላ ብዙ ርቀት የሚሄድ አይመስልም።የኩናማ ብሄር አባላት ድምጾችን ይሰማ እያሉ ነው።
ገና ብዙ ብሶቶች ወደ አደባባይ ይወጣል ።የትግራይ ሕዝብን ዘላለም ጠላት መጣልህ እያሉ ትኩረቱን በማስየር ጥቂቶች ዘርፈውም ገለውም የግልና የቡድን ስልጣናቸውን ለማራዘም የሚያደርጉት ሩጫ ከዚህ በላይ እንዳይቀጥል የትግራይ ልሂቃን ከጥላቻ ወጥተው የሕዝቡን ብሶት ማሰማት ለውጡን ለማገዝ ቢሞክሩና የራያና የወልቃይት ማንነትን በጉልበት አፍኖ መሄድ ዋጋ እንደሚያስከፍል አውቀው የሕዝቡን ማንነት ቢያከብሩ በእርግጥም ትግራይ ውስጥ ለውጡን ማፋጠን ይችላሉ።
ዛሬም ድምጾቸውን እያሰሙ ያሉ የኩናማ ብሄረሰቦችን ድምጽ እናሰማላቸው የሚለውን ተከታዩን የጥሩ ኩናማዊት ጥሪ ያንብቡት ሼር ያድርጉት
በትግራይ ክልል ዛሬም ተቃውሞው ቀጥሉል
በትላንትና እለት የጀመረው የኩናማ ብሄር ተወላጆች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል፡፡ የኩናማ ህዝብ በትግራይ ክልል መንግስት እየደረሰበት ያለው መገፋት፣ ኢ-ፍትሃዊነት፣ እስራትና ግድያን ውስጥ ለውስጥ ሲቃወም የቆየ ቢሆንም በትላንትናው እለት ግን እጅግ የሚደነቅ ሰላማዊ ተቃውሞ በኩናማ ወጣቶች አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
ተቃውሞው እጅግ ሰላማዊ ቢሆንም አፈና የለመደው የትግራይ ክልል መንግስት ላይ ግን እጅግ መደናገጥ ታይቷል፡፡ በመሆኑን ትላንት ሌሊት ከ10 ያላነሱ ወጣቶችን ወደ አልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ተከትሎ ተቃውሞው ዛሬ በጥዋት ነበር የጀመረው፡፡ (የታፈኑትን ልጆች ስም ዝርዝር የመረጃ ምንጮቻችን እያፈላለጉ ናቸው፡፡)
ረፋዱ ላይም ከክልል የመጡ ባለስልጣናት ስላሉ በሚል በርከት ያሉ ሰዎችን ሜዳ ላይ ለመሰብሰብ ሞክረዋል፡፡ እንዳገኘነው መረጃ ከሆን ከመጡት ባለስልጣናት መካከልም አቶ ሃለፎም የሚባል ይገኝበታል፡፡ እስካሁን ባለው ተሰብሳቢው ቀጥሎ ሊወሰድባቸው የሚችለውን እርምጃ በመፍራት ጥያቄያቸውን ለመጠየቅ ማመንታት ታይቷል፡፡ በስብሰባው መካከልም “ጥያቄዎቻችሁን ለሚመለከተው አካል የሚያቀርቡ ሰዎች ምረጡ” የሚል ሃሳብ ከሰብሳቢዎች ቢቀርብም ተቀባይነት ግን ማግኘት አልቻለም፡፡
በመቀጠልም አንድ ወጣትና በእድሜ ገፋ ያሉ አንድ እናት የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡
1. በኩናማ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ መቆም አለበት፣ ዲሞክራሲ የለም፣ የተማሩ ስዎችና ማህበረሰቡን ሊያነቁ ይችላሉ የሚባሉ ሰዎች እየታፈኑ ደብዛቸው ይጠፋል (የተወሰኑት በስም ቀርበዋል)፣ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት አለ፤
2. ኩናማ እራሱን በራሱ ማስተዳደር አለበት፤
3. ትላንት ሌሊት የታፈኑ ልጆቻችን ሊፈቱ ይገባል፤
በፎቶው እንደሚታየው ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ “ድምፃችን ታፍኗል፣ አፈና ይቁም” እና ሌሎች የአማራኛ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ወረቀቶችን በመያዝ ስብሰባውን እየታደሙ ይገኛሉ፡፡
****
 “ፍትህ ለኩናማና ለኢሮብ ህዝቦች”
የኩናማ ህዝብ ትግሎ እስከነፃነት ድረስ ይቀጥላል!!
Filed in: Amharic