>

የአዲስ አበባ መታወቂያ ጉድ ! (ዳዊት ድልነሳው)

የአዲስ አበባ መታወቂያ ጉድ !
(ዳዊት ድልነሳው)
* “መታወቂያ ከተመዘገባችሁ ከሶስት ቀን በኃላ ልንሰጣችሁ ስለሆነ መጥታችሁ በብሔራችሁ ተመዝገቡ”
ሀገራችን ህመሟ እየተባባሰባት እንጂ እየተሻላት አይመስልም፡፡ “ለአዲስ አበባ ነዋሪ በብሄር ፋንታ ዜግነት የሚመዘገብበት ዲጅታል መታወቂያ ይሰጣ” እየተባለ በስርአቱ ካድሬዎች በሰፊው ሲደሰኮር ቢከርምም እውነታው ግን ወዲህ ነው።
አሁን ባለኝ ተጨባጭ መረጃ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ታክሲ ተራ አካባቢ ባለው ወረዳ የአካቢቢው ነዋሪ እንዲመዘገቡ እየታዘዙ ነው እየተመዘገቡም ይገኛሉ፡፡ አቃቂ ክ/ከተማ ተመሳሳይ አይነት ነገር ነው እየሆነ ያለው፡፡ በጣም የሚያስገርመው እና የሚያመው ዋናው ጉዳይ የሚታየው ወደ ውስጥ ሲገባ ነው ።
እኔም መታወቂያ ፈላጊ ነኝና ልመዘገብ ቦታው ድረስ ስሄድ የቀረበልኝ ጥያቄ “ብሔር ምንድነው?” የሚል ነበር እውነት ለመናገር በጣም ደንግጫለሁ ምክንያቱም ይሄ ፍፁም የበሳበት ሸፍጥ እና አይን ያወጣ አምባገነናዊ ስርዓት እንደመጣ ማሳያ ነው፡፡  “ጉራጌ ነኝ” ስላት ኧ “የጉራጌ እዛኛው ቢሮ ነው የምትመዘገበው፣ አማራ ከሆንክ እዛ ፣ ኦሮሞ ከሆንክ እዚህ እና ሌሎች ደግሞ እዚያ” ብላ የመመዝገቢያ ክፍል በብሔር መሸንሸኑን አበሰረችኝ ለምን እንዲህ እንደሆነ ስጠይቅ መታወቂያ ሊሰጥ እንደሆነ እና ሙሉ መረጃ በቅድሚያ እንዳስፈለገ ተነገረኝ፡፡
መንግስት “እኔን አይመለከተኝም” ከሚል አጓጉል የማደንዘዣ ንግግር ወጥቶ ለሀገር ዘላቂ ጤንነት ሲባል በአፋጣኝ ከእንደዚህ አይነት እኩይ ተግባር ሊቆጠብ እንደሚገባ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጮህ አለበት፡
Filed in: Amharic