>

የባልደራስ እና የኢንጂነር ታከለ ም/ቤት ፍጥጫ!!! (ዳንኤል መኮንን)

የባልደራስ እና የኢንጂነር ታከለ ም/ቤት ፍጥጫ!!!
ዳንኤል መኮንን
በአዲስ አበባ በአሁን ሰዓት #ሁለት_ም/ቤት ያለ ይመስላል፡፡ የመጀመሪያውና ተወደደም ተጠላ ህጋዊ እውቅና ያለው የኢንጂነር #ታከለ ኡማ  አስተዳደር ሲሆን ሁለተኛው “ለኢንጂነሩና ለኦዲፒ  እንቅስቃሴዎች ምላሽ” በሚል ብሶት የወለደው የሚመስለው በባልደራስ እስክንድር የሚመራው የአ.አ የባላደራ ም/ቤት ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ሁለቱም በአዲስ አበባ ሙሉ #ህጋዊ_እውቅና_የላቸውም፡፡  ሁለቱም በህዝብ አልተመረጡም፡፡ ግን ሁለቱም ይህ ነው የማይባል #ህዝባዊ_ድጋፍ አላቸው፡፡
በሂደት ይህ የሁለቱም ም/ቤቶች ፍጥጫ  ለአዲስ አበባ ህዝብና ለኢትዮጲያ ጥሩ ያልሆነ ውጤት ይዞ የመምጣት አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ የኢንጂነር ታከለን አስተዳደር እውቅና የከለከለው የእስክንድር ም/ቤት በአዲስ አበባ  ከተማ በተለይ ኦሮሞ ባልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን (በተለይ ወጣቱን) በአንድ አሰባስቦ እና ኢንጂነሩ ላይ ከተንቀሳቀሰ አዲስ አባባ ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቅቡልነታቸው (ከአሁኑ በባሰ) ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባቱ አይቀርም፡፡  እስክንድር ከባለፈው ስብሰባ በኃላም ሆነ ትላንት ቦሌ አካባቢ በተቀሰቀሰው ግርግር የታሰሩ ወጣቶችን ለማስፈታትና ለመጠየቅ ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በአዲስ አባባ ህዘብ ዘንድ የበላይ ጠባቂነትን የሚያላብሰው ሲሆን የኢንጂነር ታከለን ተቀባይነትም ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል፡፡ እስክንድርን ግን ቀላል የማይባለው የአዲስ አባባ ኦሮሞና ዙሪያውን የከበበው ቄሮ የትም የሚያንቀሳቅሰው አይመስልም::
በሌላ በኩል ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የተለያዩ በጎ ስራዎችን የሰሩ ቢሆንም ገና የአዲስ አባበ ከንቲባ ወንበር ላይ ከተቀመጡ አንስቶ ቅሬታዎች (በተለይ ከአማራ ልሂቃን በኩል) ሲነሱባቸው ነበር፡፡ ግን ባለፉት ወራት የተነሱባቸው ቅሬታዎች አሁን ከተነሱባቸው ቅሬታዎች ጋር ሲወዳደሩ ተራ ናቸው፡፡ በተለይ በአዲ አበባ ዙሪያ በኦዲፒ የተያዘው አቋምና በጃዋር የተንጸባረቀው አቋም ለኢንጂነር ታከለ አስተዳደር ትልቅ የስጋት መንስሄ ሆንዋል፡፡
ኦዲፒ በአቋም ከኢንጂነሩም ሆነ ከጃዋር አቋም ጋር ይስማማል፡፡ ይህ ወቅት በኦሮሞ ልሂቃን ላለፉት 50 አመታት ሲናፈቅ የነበረ ወቅት እንደመሆኑ መጠን እስክንድርን በቀላሉ በአዲስ አባባ ጉዳይ አሸናፊ የማድረግ እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ኦዲፒ በቀላሉ ይህንን ወቅት በአዲስ አባባ ጉዳይ ሳትጠቀምበት አታልፍልም፡፡ ለኦዲፒና ኢንጂነር ታከለ የአዲስ አባባ ጉዳይ የመኖርና የመሞት ጉዳይ ነው፡፡ ኢንጂነር ታከለ በአዲስ አባባ ዙሪያ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቄሮ፣ ጃዋርና ስልጣን ላይ ያለው ኦዲፒ አለ፡፡  የሁለቱ ም/ቤቶች ፍጥጫ “the clash of titans” አይነት ነው፡፡
 
ታዲያ ምን ይፈጠራል?
1. የአዲስ አባባ ህዝብ ለብሔር ፖለቲካው ከሚደርስበት ጉዳት ይልቅ በኢኮኖሚ የሚፈጠረው ጉዳት ይበልጥ ያሰጋዋል፡፡ አዲስ አባባ ከሀገሩቱ የኢኮኖሚ ዋልታዎች አንዱ ነው፡፡ የአዲስ አባባ ሰው ለአንድ ቀን ያለ ስራ ቢቀመጥ ምን ያህል ኢኮኖሚው እንደሚናጋ ጠንቅቆ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ የአዲስ አባባን ወጣትም ሆነ ነዋሪ ባለፉት አመታት በሀገሪቱ ሲደረግ እንደነበረው በሰላማዊ ሰልፍ ፍላጎቴን አስከብራለው ብሎ ማለት ይከብዳል፡፡ ግን በቀጣይ ጊዜያት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎችን መመልከታችን አይቀሬ ነው፡፡
2. በአሁኑ ሰዓት ከኢንጂነር ታከለም ሆነ እስክንድር ጎን በደጋፊነተ የተቆመው በብሔርና በዜግነት በሚሉ ክፍፍሎች ቢሆንም እውነታው ግን ሁለቱም ጎን የተሰለፈው ደጋፊ ብሔርን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከተማዋን ይበልጡኑ እንዳይከፋፍላት ስጋት አለኝ፡፡
3. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዳሉት አዲስ አባባ እንደ ኢየሩሳሌም እየሆነች ያለ ይመስላል፡፡ ምን አልባት ሁለቱም ም/ቤቶች የራሳቸውን እርምጃዎች በቀጣይ የሚወስዱ ኮሆነ አሳሪና ታሳሪ መኖሩ አይቀሬ ነው፡፡
4. በአዲስ አባባ በተለይ በእስክንድር የሚወሰዱ እርምጃዎችና ጥሪዎች ከቄሮ በኩል ምላሽ ከተሰጠባቸው የአዲስ አበባ ጉዳይ አስጨናቂ ሊሆን ይችላል፡፡
#መፍትሄው
ሁለት ም/ቤቶች መካከል ያለው ግንኙነት በሂደት እየከረረ ከሄደ ለህዝቡ የማይወጣውን ጣጣ ይዘውበት ስለሚመጡ ሰከን ብሎ መነጋገርና መደራር አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ካልሆነ ግን በዚህም ተባለ በዚያ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ የአዲስ አባባ ህዝብ ነው፡፡
Filed in: Amharic