>

"ባለአደራ ምናምን የሚባለው ነገር ለኔ ትክክል አይመስለኝም!!!"  (ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ለOBN)

“ባለአደራ ምናምን የሚባለው ነገር ለኔ ትክክል አይመስለኝም!!!”
 ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ለOBN
* መልካም የመሻገር ዘመን ከታኬ ጋር ክቡርነትዎ!
የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሚመራውን የአዲስ አበባ ሕዝብን ድምጽ ለማሰማት የሚንቀሳቀሰውን ባላደራ ትክክል አለመሆኑን በገዢው ኦሮሞ ብሮድካስቲን ኔትወርክ (OBN) ቀርበው ለሰጡት ቃለ መጠይቅ ገለጹ።
ፕ/ር ብርሃኑ የአዲስ አበባን ጉዳይ በዝምታ ለማለፍና ለማድበስበስ ሲሞክሩ መቆየታቸው ሲያስወቅሳቸው ቆይቶ እነ እስክንድር ነጋ የጀመሩት ሕዝባዊ እንቅስቃሴን ተከትሎ ድርጅታቸው የት ሄደ የሚል ወቀሳ ሲደመጥብየቆየ ሲሆን “ባለአደራ ምናምን የሚባለው ነገር ለኔ ትክክል አይመስለኝም። አቶ ታከለ ይሄን የማሸጋገር ሂደት በሚመለከት በትክክል ያልሰራው ነገር አለ ከተባለ ሂስ ማቅረብ ጥሩ ነው።”
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ባላደራ የሚባል ጦርነት ውስጥ ያስገባናል” ማለታቸው ሰፊ ተቃውሞን እንዲያስተናግዱ ምክንያት ሲሆን የቀድሞ የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪን ዶ/ር አክሎግን ጨምሮ ከ40 በላይ ምሁራን የእነ እስክንድር ጥያቄ አግንምባብ መሆኑን ጠቅሰው አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ መሆኑዋን መግለጾቸውና ለዶ/ር አብይ ግልጽ ደብዳቤ መጾፋቸው ይታወሳል።
ባልደራስ ቅዳሜ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
ገፅ ለ ገፅ ፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ጋር የተደረገ ውይይት::
Filed in: Amharic