>

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተከፈተው ዘመቻ፤ዘመን ያስቆጠረ ኢትዮጵያዊ ተቋማችን እንዳያሳጣን…(መንገሻ ዘውዱ ተፋራ)

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተከፈተው ዘመቻ፤ዘመን ያስቆጠረ ኢትዮጵያዊ ተቋማችን እንዳያሳጣን….

መንገሻ ዘውዱ ተፋራ

ወያኔዎች ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ፤የመጀመሪያ ኢትዮጵያን የማጥፋት ዘመቻቸውን ያደረጉት፤ የአትዮጵያ መለያ የሆኑ፤ተቋማትን ማጥፋትና፤በዘር፤የተመሰረተ ልማት ማህበር፤የገንዘብ ተቋም ወዘተ ማቋቋም ነበር። በዚህ መልክ ካጠፉአቸው ኢትዮጵያዊ ተቋማት ጥቂቶቹን ለማስታወስ፤ቀለሙና አንበሳው፤ልዩ መልዕክት የነበረው፤አገር አቋራጭ አንበሳ አውቶብስን፤ብዙ ድሃ ኢትዮጵያዊያንን፤ባለ ቤት ያደረገው፤የቤቶችና ቢዝነስ ባንክንና፤ሌሎች ናቸው። በአነዚህ ደግሞ የተተኩት፣ኢፈርት፤ጉና፣ ጥረት፤ዲንሾ፤ወጋገንና፤እነሱን ተከትለው፤በዘር የተፈለፈሉ፤ ተመሳሳይ፤ተቋማት ብዙ ናቸው። አዚህ ላይ በደንብ ልብ ማለት ያለብን፤የወያኔ ጥላቻ፤ ኢትዮጵያ ከምትባለው ቃል ነው።ምክንያቱም ለወያኔዎች ኢትዮጵያ ማለት አማራ ነው ብለው ሰለደመደሙ ነው።

ከነዚህ የጥፋት ዘመቻ ከተደገሰባችው፤ተቋማት አንግዲህ አንዱ ይኸው መጠፊያ ጊዜው የደረሰ የሚመስለው፤የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው። ወያኔዎች አሁን ከምንሰማው በባሰ እስከ አሁንም፤ድረስ አንደፈለጉ እየተጠቀሙበት አንኳን፤ከብር ምስጋና ይግባቸውና፤በጠንካራ ኢትዮጵያዊያን ፍቅርና ጥረት፤ቢያንስ ኢትዮጵያዊነት ሰሙን፤ይዞ ተርፎ ነበር።
እንደነዚህ ያሉ ኢትዮጵያዊ የሀገር ሀብቶችን የማጥፊያ ስልታቸውም፤በእነዚህ ኢትዮጰያዊ ተቋም ውስጥ፤ህዝብን የሚያነሳሳና፤በህዝብ የሚያስጠላ ስራ መስራት ነው። ለዚህ ደግሞ የመጀመሪው ተግባራቸው፤ተቋሙን በእራሳቸው ዘርና አንደሚፈልጉት በሚያስሽከርክሩአቸው ሆድ አደሮች መቆጣጠርና፤ህዝቡን የሚያነሳሳ፤ልክ አንደ አሁን፤ኢ ፍትሃዊ የሆነ፤የሀብት ክፍፍል ስህተት መስራት ነው። እኛም በብስለትና በብልሃት ተመስርተን፤ጉዳትና ጥቅሙን አመዛዝንን፤ወንጀል ሰሪዎቹን፤ለይተን አንደ መታገል፤በብስጭት የጎዳናቸው እየመሰለን የምንሰጠው አፀፋዊ መልስ፤የእነሱን ድብቅ ዓላማ ያሳካል። የእራሳችን ሀብትና፤መለያችንም ያሳጣናል።

በአንድ ህዝብንና ሐገርን፤መሰረተ ባደረገ መንግሥት፤ብሔራዊ ባንክ ባለበት፤እንዴት በአደራ የተቀመጠ፤የህዝብ አንጡራ ሀብት፤ገንዘብ፣ያለ አደራ አስቀማጩ ወይም ገንዘቡ ባለቤት ውሳኔ፤ይነካል? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤አንዱና ዋናው ኃላፊነቱስ፤ይህን በአደራ የተቀመጠን የህዝብ ገንዘብ፤ያለ አስቀማጩ ፈቃድ፤አንዳይንቀሳቀስ መጠበቅና፤ቁጥጥር ማድረግ፤ገንዘቡ መከፋፋል ካለበት ደግሞ፤ፍትሐዊነት በተላበሰ የኃብት ክፍፍል፤ለሁሉም አንደየ ድረሻውና አስተዋፅኦው፤እንዲከፋፈል ማድረግ አይደል እንዴ? ታዲያ ይህ አይነት ኢ ፍትሃዊ የገንዘብ አወጣጥንና፤ተቆንጥሮ ለተፈለገው ሲታደል፤ዝም ብሎ ያያል? በዚህ አይነትማ፤ነገ ያስቀመጥነውን ገንዘብም አላየንም ብንባልም፤ዝም ብሎ ሊያየን ነው ማለት ነው። ሌላ አጅግ አሳፋሪ፣አስደንጋጭና፣ አስጊ ክስተት። ህግ ይከበር ሲባል አኮ፤አንዲህ አይነቱ በቡድን ተደራጅቶ የሚፈፀም፤አጉራ ዘለለ ተራ ውንብድና አይታይ ነው።

አሁንም፣ይህ በወያኔ፤የተተካው፤የወያኔን ፈለግ እየተከተለ ያለ ሰብስብ፤ከወያኔ የተረፉትን፤የኢትዮጵያዊነት መለያ የሆኑትን ተቋማት ለማጥፋት፤ቀይሶ የሚንቀሳቀስ በተንኮል የተመሰረተ ይሽታል። ታዲያ አንደስጋታችን ከሆኖና፤ነገ ደግሞ፤በኢትዮጵያ አየር መንገድ፤አሁን በንግድ ባንክ አንደተሰራው ኃላፊነት የጎደለው ሥራ ቢሰራ፤አየር መንገዱ የእኛ አይደለም ብለን፤የጎጣችን አየር መንገድ ልንፈጥር ነው? ወይስ የአየር ላይ ጉዞን ሰርዘን፤በእግር በፈረስ ወደ ውጭ ሐገርም ጉዞ ልንጀምር ነው? እዚህ ላይ ነው፤በተቻለ መጠን፤አዕምሮን ሰላ፤ልብን ሰፋ አድረጎ ማሰብና፤የምንወስዳቸው እርምጃዎች አነሱ ከሚወስዱት የተሻለ፤ጠንካራ ማድረግ የሚጠይቀው።

በመሆኑም፤አርምጃው፤በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤በኢትዮጵያዊ ስሙና፤በግዑዙ ላይ ሳይሆን፤ያለ አግባብ በንቅለ ተከላ፤በዘር ተሰባስበው፤ባንኩን በተቆጣጠሩት፤አንዲህ ያለ ኢ ፍትሃዊ ውሳኔ ባሳለፉት፤አንቀሳቃሾች፤software (humans)፤ሰዎች ላይ፤በሰላማዊ ትግል በህግ፦ ከሥራ እንዲታገዱ። አሁንም ለወሰኑት ህዝብን ለአስከፋ ውሳኔ አንዲጠየቁ። ያለ አግባብ በኢ ፍትሃዊ የወጣው የህዝብ ገንዘብም ወደ ነበረበት እንዲመለስ። ወደፊትም ያለ ህዝብ ውሳኔ እንዲህ ያል ስህተት አንዳይሰራ። ካስፈለገም፣በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተጀምረውን ዘመቻ ሆን ተብሎ የኢትየጵያ ንግድ ባንክን ለማጣፋት፤በዘር በተመሰረቱት ባንኮች ላይ እቀባ በመጣል። ልክ በአዲስ አበባችን ላይ ድርድር አንደሌለን፤ሁሉ በዚህ ከ50 ዓመት በላይ ባስቆጠረው፤አባቶቻችን ጠብቀው ባቆዩን መለያ፤ኢትዮጵየዊ ባንካችን፤የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም፤የማንደራደር፣መሆኑን ማሳየት ነው አንጅ፤አነሱ በቀደዱልን፤የተደበቀ አላማቸው፤ቦይ ፈሰን፤በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተከፈተው ዘመቻ፤ዘመን ያስቆጠረ ኢትዮጵያዊ ተቋማችንና በዓለም የምንታወቅበትን መለያችን፤እንዳያሳጣንና፤ነገ ሁሉም ሲስተካካል እንዳንፀፀት በጥንቃቄ ቢታይ።

ማሳሰቢያ፤ አስተያየቱ ማንንም የማይወክል የግሌ አንደሆነ እንዲወሰድልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ኢትዮጵያ በከብር ለዘላላም ትኑር

Filed in: Amharic