>

ለነገው ትውልድ ነፃና የተሻለች ኢትዮጵያን እንፍጠር!!!  (ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና)

ለነገው ትውልድ ነፃና የተሻለች ኢትዮጵያን እንፍጠር!!!
 ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ላለፉት 50 ላላነሱ  ዓማታት በብዙ መከራና ስቃይን አይቷል የተሻለ  የፖለቲካ ስርአትን ተመኝተህ፣  ከዛ የባሰ የፖለቲካ ስርአት እያገኘህ ፣መከራ ስታይ  ፣ልጆችህ ሲጨፈጨፉና በየእስር ቤቱ ሲንገላቱ፣ በደምና በዕንባ ስትራጭ ኖረሃል ፡፡
ስለዚህ ይህ ለውጥ የመጨረሻ እድላችን የተሻለ እንዲሆን፣  በሙሉ ልብህ፣  ከቀልባሽ ሀይሎችምና ለስልጣን ብለው ከሚልከሰከሱ  ሀይሎችም፣  በመጠበቅ ትግሉን  የተሻለ እንዲሆን ፣ ለነገው ትውልድ ነፃ ኢትዮጵያ እንድትፈጠር፣ሁላችንም በእኩልነት  የምንኖርባት ብቻ ሳይሆን  ልጆቻችንም   የሚኖሩባት፣ የተሻለች ኢትዮጵያን እንድትፈጠር፣ አንተም የፖለቲካ ሀይሎችም አቅጣጫ እንዲይዙ ፣ የመቻቻል  ፖለቲካ እንዲፈጠር ፣ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ በሀገራችን እዲሰፍን፣  በዚህ  ነፃና ፍትሀዊ ምርጫም ድሞክራቲክ ኢትዮጵያ እንድትወለድ፣  የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዚህ አስተዋፅኦ እንድታደርጉ አደራ እላለሁን ፡፡
Filed in: Amharic