>

ህግ አክባሪው ህዝብ ገዳዮቹን "አትግደሉን" ብሎ ሰልፍ ወጥቷል- ነገስ...?!? (አቻምየለህ ታምሩ)

ህግ አክባሪው ህዝብ ገዳዮቹን “አትግደሉን” ብሎ ሰልፍ ወጥቷል- ነገስ…?!?
አቻምየለህ ታምሩ
 
ከፋሽስት ወያኔ ባልተናነሰ  ኢትዮጵያን የአማራ መታረጃ ቄራ ያደረጓት ኦነጋውያንና ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ  የኦሮሞ ብሔርተኞች ጭምር  ናቸው። በወያኔ ላይ በተመሳሳይ  ስዒረ መንግሥት ያሰቡትንና ይከታተላቸው የነበሩትን እነ ጀኔራል ከማል ገልቹን ወደ ኤርትራ እንዲያመልጡ  አድርጎ እነ ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ግን ለእርድ ያቀረበው የፋሽስት ወያኔ የጃሚንግና የስልክ ጠለፋ አዛዥ  የነበረው ዐቢይ አሕመድ ነው።
ስለዚህ የአማራ ሕዝብ በመላው ኢትዮጵያ በጭካኔ እየተገደለና በግፍ እተፈናቀለ  ያለው በዙፋኑ በተሰየሙት ገዳዮቹና የድሀ ቤት አፍራሾች እውቅናና አቀነባባሪነት  ስለሆነ ለሚገድሉትና ለሚያፈናቅሉት በሰልፍ ሊያሳውቃቸው  የሚችለው  የማያውቁትና ያላስፈጸሙት ግድያና መፈናቀል ባለመኖሩ  በዛሬው የአማራ ልጆች  ሰልፍ  ላይ  ተይዘው  በአደባባይ የታዩት  እነዚህ ከታች የታተሙት  መፈክሮች  የሰልፉ የአቋም መግለጫ ዋና መልዕክት መሆን አለባቸው።
ማንኛውም ፍጡር መሰሉን ሲወልድ ቢደሰትም ኦነጋውያንና ህወሓታውያን ግን በአማራው ብሄርተኝነት ደስተኞች አይመስሉም። የሆነው ሆኖ ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚኖሩ አማራዎች ላይ የደንጋይ ዘመን ዘግናኝ ድርጊት ሲፈፀም ኦነግና ህወሓት በደስታ ሲፍነከነኩ ከሰነበቱ በኋላ ዛሬ ተጠቂው አካል አፀፋ ሲመልስ ለቅሶ ተቀምጠዋል። በዛሬው ቀን በአማራ ክልል በሚካሄዱ ሰልፎች ላይ ጥቅም ላይ የዋሉ መፈክሮችንም ፎቶሾፕ በመስራት የሰልፈኞችን ጥያቄ በማጠልሸት ላይ ተጠምደዋል።
ሲጀመር ማንም ሰው ሊሞት አይገባም። ማዘንም ሆነ ማውገዝ ለሁለቱም ወገን ሊሆን በተገባ ነበር። አስቂኙ ነገር የዝንጀሮ ፖለቲካ እስካልቆመ ድረስ መሰል እልቂቶች እንደሚቀጥሉ ቢታወቅም ህወሓታውያንናኦነጋውያን ግን የዝንጀሮ ፌደራሊዝሙ አሁንም ተመችቶናል እያሉ ነው።
ሰብዓዊነት ይቅደም የሚሉ በርካታ ድምፆች በተደጋጋሚ ቢሰሙም እነዚህ ኃይሎች ግን ዝንጀሮነት ይቅደም በሚለው አቋማቸው እንደፀኑ ነው። ዝንጀሮነትን ደግፈህ የዝንጀሮ ስራን መንቀፍ አትችልም።
Filed in: Amharic